ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከመቶ ዓመታት በፊት ሁለት ሚሊየን አርሜናውያን ክርስቲያን ወገኖቻችንን የጨፈጨፈችው ቱርክ ዛሬም አርሜኒያን በማሳደድ ላይ ነች። የገዳይ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ አጋር የሆነው የቱርክ ፕሬዚደንት ኤርዶጋን አሥር ሺህ ኪሎሜትር ያህል ተጉዞ ወደ ደቡብ አሜሪካ በመሄድ አርሜኒያ ተብላ በተሰየመችው የኮሎምቢያ ከተማ አንድ የቱርክ ኃውልትን ለመትከል በቅቷል። ይህ በጣም የሚገርም ነገር ነው።
እንደምናየው ቱርክን የክርስቲያን ሰማዕታት ደም በጣም ያቁነጠንጣታል ያለው። ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት አክሱምን ለመቆጣጠር በመሻት ግራኝ አሕመድን በመልመል በሀገራችን ላይ ብዙ ጥፋቶችን አስከትላ ነበር። ዛሬም እኛ በጉለሌ ጉዳይ እርስበርስ ስንባላ ለስለስ ባለ መንገድ በሐረር በኩል በመግባት ላይ ናት። በአንድ በኩል፡ ትምህርት ቤቶችን፣ የባህል ማዕከላትን፣ ምግብ ቤቶችንና መስጊዶችን ልስራ እያለች ሰላማዊ በሆነ መልክ ሰተት ብላ ስትገባ ፥ በሌላ በኩል ደግሞ በሶማሊያ ከፍተኛ የጦር ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች። የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ደም ጠምቷታል፤ ስለዚህ ለአርሜኒያ ያሰበችው ለኢትዮጵያም ይሆናል። ከመቶ ዓመታት በፊት በዘመነ ግራኝ አሕመድ ከሶማሌዎች ጋር ጥብቅ ግኑኝነት የነበራት ቱርክ ዛሬም በዳግማዊ ግራኝ አሕመድ ዘመን ለሶማሌዎች ያላት ዲያብሎሳዊ ፍቅር በጣም ጥብቅ ነው። ዓይናችንን በተለይ በቱርክ ላይ ይሁን!
ሁለቱ ጥንታውያን ክርስቲያን ሀገራት ለቱርክ ውድቀት ምክኒያት ይሆናሉ። ታዋቂው የግሪክ ኦርቶዶክስ አባት ፓይሲዮስ እንደተነበዩት ከሆነ ቱርክን በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እርዳታ የምታጠፋት በዛሬው ታሪካዊ ዕለት የመከላከያ ሮኬቶችን ለቱርክ የሸጠችላት ኦርቶዶክስ ሩሲያ ናት። Elder Paisios' Amazing Prophecies About Constantinople ከቱርክ ጋር የሚያብር፣ ለቱርክ የሚሠራ የሀገረ ኢትዮጵያና አምላኳ ጠላት ነው፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው። ተዋሕዶ መሪዋ ክርስቶስ ይባላል፤ ኢትዮጵያን(ኃይማኖቷን ተዋሕዶን)የነካ ሐያሉ አምላክ ይገስፀዋል።
Blogger Comment
Facebook Comment