ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከሳምንታት በፊት እነ ጄነራል አሳምነውን ባሕርዳር ላይ ሲገድሏቸው፤ እስክንድርንም እዚያው ባህር ዳር ላይ ለመግደል ዕቅድ እንደነበር እስክንድር ሰሞኑን ካደረገው ቃለ–መጠይቅ( አሥራት ሚድያ )በደንብ ለመረዳት ይቻላል። ይህን ግድያ ያቀነባበረው ገዳይ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ እንድሆነ እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል። ሰውዬው በአጋንንት የተለከፈ እርኩስ ወሮበላ ነው።
ተከታዩም የትናንትናው ድራማ በገዳይ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ የተቀነባበረ እንደሆነ አያጠራጥርም። ሰውዬው እንደ እስክንድር፣ ጄነራሎች ሰዓረና አሳምነው ለኢትዮጵያ በቆሞ አገር–ወዳዶች ላይ ከፍተኛ ጥላቻና ፍራቻ አለው። ስለዚህ እንደነርሱ ያሉትን ግለሰቦች ፈጥኖ ማስወገድ እንዳለበት አምኖበታል።
በትናንትናው ዕለት የታየው ነገር እንደሚከሰት አስቀድሞ ጠቁሞን ነበር፤ ከወራት በፊት እስክንድር እና የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) በራስ ሆቴል ያቀዱት ጋዜጣዊ መግለጫ በጸጥታ ኃይሎች መከልከሉን እናስታውሳለን። በዚያ ወቅት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት “ከበላይ አካል በመጣ” ትዕዛዝ ጋዜጣዊ መግለጫውን ከመስጠት መከልከሉን እና “ሊበጠብጡ የሚችሉ ኃይሎች ስለሚኖሩ ሆቴል መግባት አይፈቀድም… ቅብርጥሴ” ብለውት ነበር።
በትናንትናው ዕለት ፍዬሎቹ ቄሮዎች (ሊበጠብጡ የሚችሉ ኃይሎች) ከውጭ የሉሲፈራውያኑ ኮከብ የወደቀበትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ፥ በኮታቸው ውስጥ ደግሞ ጩቤና ሰንጢ በመያዝ ወደ እስክንድር እንዲሄዱና ጥቃት እንዲፈጽሙበት ትዕዛዝ ተሰጣቸው (የግራኝ ዐቢይ አሕመድ ስክሪፕት፥ መጽሐፉን አንብቡት)።
እንግዲህ የእነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች ዕቅድና ተግባር በጣም ግልጽ ነው፤ ታዲያ አሁን ከሁሉም አቅጣጫ በሀገረ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት በታወጀበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያውያን ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል? በጣም ብዙ ነገር! በእነ እስክንድር ላይ ጥቃት እስኪፈጽሙ መጠብቅ የለባቸውም! ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፦ ለኢትዮጵያ የቆሙትን የጦር–ሠራዊቱንና የፖሊስ ኃይል አባላት (በጣም ብዙ ናቸው፣ ብዙ ሰዓረዎች፣ ብዙ አሳምነዎች አሉ) በመቀስቀስ የኢትዮጵያ ጠላቶች በሆኑት የውጭ ኃይሎች የተማመኑትን ገዳይ አል–አብይንና ከሃዲ አጋሮቹን በፍጥነት ማንበርከክ ይኖርበታል። ቆራጥነት ብቻ የሚጠይቅ ቀላል ጉዳይ ነው! ጀግናውን ራስ አሉላ አባ ነጋን እናስታውስ!
[መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፫፥፩፡፰]
“ ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤ ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።“
Blogger Comment
Facebook Comment