በአባታችን በንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ፦
“እግዚአብሔር አሁን በኛ ዘመን ኃጢአት እጅግ በነገሠበት ወቅት ደግሞ አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን)ሠራዊት በዐይን ቅጽበት ዉስጥ ማርገፍ የሚያቅተው ይመስላችኋልን? እናንተ ሆናችሁ በዓለም ዉስጥ ያለው ትዉልድ ማንም ይህን ማን በዓመፃዉ ከጸናና እጁን ለእግዚአብሔር አልሰጥ ካለ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ አመጸኛ ትዉልድ ረግፎ እንደ ኖኅና ቤተሰቡ ቅንነት፥ የዋህነት፥ እዉነተኛነት የተላበሱትን ሰዎች ብቻ የማያስቀር ይመስላችኋልን?
ስለዚህ “ሠራዊቱ፣ ድኅንነቲ፣ ጠባቂዬ፣ ዘሬ፣ ጎጤ ኃያላን መንግሥታት፤ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት…ወዘት” የሚባሉት እንኳን እናንተን ራሳቸውንም ማዳን እንደማይችሉ በዚሁ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። ከእግዚአብሔር ቁጣ ሊድኑ የሚችሉት በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ሲሰጡና በኢትዮጵያ በቅርቡ እግዚአብሔር ለሚዘረጋው መንግሥቱ ለሥጋዊዉም ለመንፈሳዊዉም ሥርዓት ተገዥ ሲሆኑ ብቻ ነዉ። በተቀረ ግን የዓመጻ፣ የክህደት፣ የርኩሰት ጽዋቸዉን እያንዳንዱ መንገሥት፣ ቡድን ፣ ድርጅት፣ ግለሰብ እየጠጣ ነጻነቱ ተገድቦ ወደሚኖርባትና እንደ ዓመጻው ደረጃ ፍዳዉን ወደሚቀበልበት ቦታ መሄድ ነዉ የሚቀረዉ። ይህን ሁሉ የተናገርነዉ መቺስ እጃችሁን ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ ብለን በማሰብ ሳይሆን የእናንተ ልበ ደንዳናነት ቢታወቅም ባለማወቅ በቅንነትና በየዋህነት አብሮዋችሁ የተሰለፉ ሰዎች ካሉ ከዛሬ ጀምሮ ከእናንተ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲፈጥሩ፣ እንዲሁም በእዉነተኛ ንስሐ እንዲመለሱ ለማሳሰበ ነኡ።” በማለት ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የተመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁል በላይ ደግሞ የእመቤታችን አስራት አገር ስለሆነች እንኳን በአገር ዉስጥ ለጥፋቷ የተሰለፉ አይደለም፤ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የዉጭ መንግሥታት በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጣ ይጠፋሉ፤ ከምድር ይጠረጋሉ። እርሷ ግን በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች። ታዲያ አሁን ቢሆን “የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” እያሉ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያላግጡ ሆኑ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች እንዲሁም መንግሥታትና ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳይሉ በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ቢሰጡና ወደማንነታቸዉ ወይንም ወደ ኢትዮጵያዊነታቸዉ ቢመለሱ የሚበጃቸዉ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ መልእክቱን አቀርባለሁ።”
የአባታችንን ነፍስ ከቅዱሳን አበው ነፍስ ጋር ይደምርልን!
Blogger Comment
Facebook Comment