መጽሐፈ አክሱም | የአክሱም ጽዮንን ታሪክ እና የርስት ጉልቷን ሥሪት የሚናገር

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

📖 “መፅሐፈ አክሱም” በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን በአክሱም ንቡረ-ዕድ የተፃፈ መፅሐፍ ነው።

መጽሐፈ አክሱም፤ የአክሱም ጽዮንን ታሪክ እና የርስት ጉልቷን ሥሪት የሚናገር ሲሆን ስለ ቅ/ያሬድ ዜማ ድርሰት ይናገራል። እንዲሁም በድርሳነ ዑራኤል የተገለጸውን ታሪክ (እመቤታችን ተገልጻ ቅ/ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን “ዜማ እንዲደርስልኝ ውዳሴዬንና ቅዳሴዬን ለያሬድ ስጡት” ያለችውን) መዝግቧል።

“መጽሐፈ አክሱም” ትውፊትንና ታሪክን መሠረት አድርጎ የአክሱምን አመሠራረትና ታሪካዊ እድገት፣ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ማዕከልነት ይናገራል፡፡ ስለ አክሱም አመሠራረት፣ ሰፊ ትውፊታዊ ትንታኔ ይሰጣል፡፡ የአኹኖቹ የግሪክ እና የሮም ከተሞች እጅግ ሰፊ የነበረው የግሪክ ወሮም ግዛትና መንግሥት ታሪክ ማሳያዎች እንደመኾናቸው፤ የአኹኗ አክሱምም፣ ምሥራቅ አፍሪቃን ከደቡብ ዓረብ አጣምራ ትገዛ ለነበረችው የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ (ዘመነ አክሱም) ታሪክ መዘክር ነች፡፡

'ኢትዮጲስ' በመጽሐፈ አክሱም ዘንድ ኑቢያን የመሠረተው የካም ልጅ ኩሽ ልጅ ነበር። በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ የሚኖሩት ኩሺቲክ ብሔሮች አባት በመሆኑ ሀገሩ 'ኢትዮጵያ' መባሉ እንደሚገባው ይታመናል።

በመጽሐፈ አክሱም መሠረት ኩሽ የርስቱን ድርሻ ለማመልከት የአክሱምን ታላቅ ኃውልት እንዳቆመ፣ ልጁም ኢትዮጲስ በዚያ እንደተቀበረ ይታመናል። ዘራፉው የስኮትላንድ ነፃ ግንበኛ/ፍሪሜሰን ጀምስ ብሩስም በኖረበት ዘመን ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ከክብረ ነገሥት ጋር እኩል ሆኖ እንደ ከበረ ጽፎ መሰክሯል።

👉 ማሳሰቢያ

ይህን መጽሐፍ ዋቢ በማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች የተዳቀሉት የዋቄዮ-በዓል-አላህ-ባፎሜት-ሉሲፈር ባሪያዎች/ እባቦች እና ደቡባውያን አጋሮቻቸው ታሪክን እየበረዙ የአክሱማዊቷን ኢትዮጵያ ማንነትና ምንነት ብሎም ግዛታዊ አንድነትን ለመጻረር/ለመዋጋት በመታገል ላይ መሆናቸውን ልብ እንበል።

እነዚህ ሰዎች ናቸው በተለይ 'ኢትዮጵያዊ' የተሰኘውን ማህበረሰብ እንደ በሬው ሳሩን እያሳዩ ወደ ገደል በመውሰድ ላይ ያሉት። ለዚህም ነው ይህ 'ኢትዮጵያዊና ክርስቲያን ነኝ!' የሚለው የወደቀ ወገን ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ቀንደኛ ጠላቶች ጋር አብሮ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለመጨፍጨፍ፣ ለማስራብ፣ ለማፈናቀልና ለማሳደድ ወደ አክሱም ጽዮን የዘመተው። ይህ እጅግ በጣም አስገራሚና አሳዛኝ የሆነ ታሪካዊ ስህተት ደግሞ ጠላቶቻችንን እንኳን ሳይቀር ያስገረመና ያበረታታ ነው። እንደ ዓይኑ ብሌን ሊንከባከባት በሚገባው በአክሱም ጽዮንን ላይ ከእስማኤላውያኑ የክርስቶስ ተቃዋሚ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሆኖ ዘመተባት። ከአምስት መቶ ዓመታት በፊትም የግራኝ ቀዳማዊ ጂሃዳዊ ጦር ከሐረር ኤሚራት ተነስቶ እስከ አክሱም ጽዮን ድረስ ሊገባ የቻለው በእነዚሁ ዲቃላዎች ተመሳሳይ ክህደት ስለተፈጸመ ይሆን? ይመስላል!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment