በእኛ ድክመት ሀገራችንን እንዲህ ይከፋፈሉ ዘንድ እድሉን የሰጠናቸው ጠላቶቻችን እየተገለጡልን ነው


ይህኛው ደግሞ ሄርማን ኮኸን ይባላል። የሰማንያ ሰባት ዓመት አዛውንት ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያስታውሰው በእንግሊዞችና በአሜሪካኖች ተቀነባብሮ በአቶ ሄርማን ኮኸን አጋፋሪነት/“ሽምግልና፡ ከሦስት ተገንጣይ ብሄራዊ ድርጅቶች (EPLF, TPLF OLF )ጋር እ... 1991 .ም ላይ በለንደን የተደረገዉ ስብሰባ በዋናነት ፀረ ኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎችን ለስልጣን የሚያበቃና ጥቅም የሚያስጠብቅ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሃገራችን እንድትበታተን የሚያስችል ስትራተጂ የተነደፈበት የኢትዮጵያውያን የጨለማ ቀን ነበር። ኢትዮጵያን በብሔር የሚከፋፍለው ሕገመንግስት ለእነዚህ ተገንጣይ ድርጅቶች የተሰጠው በዚሁ ወቅት ነበር።

የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር /ር ሄንሪ ኪሲንጀር በኦሮሞዎች የሚመራውን የፀረ–ክርስቲያኑን የደርግ መንግስት ሥልጣን ላይ ለማውጣት እንዲሁም እነ /ር አምባሳደር ሄርማን ኮኸን የኢሃዴግና ኦነግ ፀረ–ተዋሕዶ መንግስትን ለማደራጀት ትልቅ ሚና ተጫውተው ነበር። (ዶክትሮች)

አሁን ከ፳፰ ዓመታት በኋላ ሁለተኛው የሉሲፈራውያኑ ልሳን (አንደኛው ቪ. . . ነው) ቢቢሲ ወስላታውን ሄርማን ኮኸንን ሊገቡ ከተጋጁብት የሲዖል ደጃፍ መልሰው በመጥራት ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያን በመርዛማ ትንፋሻቸው አፍነው ለመግደል ሲሞክሩ ይሰማሉ። 
/ር ሄንሪ ኪሲንጀር

ተዋሕዶ የሰሜን ሰዎች ሥልጣን ላይ እንዳይወጡ ሁሉም ጠላቶቻችን እንደሚሹ ይህ ቃለመጠይቅ ጥሩ ማስረጃ ነው። ቢቢሲን ጨምሮ (የአጠያየቃቸውን ስልት እንታዘብ)በጄነራሎቻችን መገደል ሁሉም እንደረኩና ስልጣን ላይ ያስቀመጡት ገዳይ አብዮት አሕመድ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን ማስወገዱ ትክክል እንደሆነ በድፍረት/በግልጽ እየጠቆሙን ነው። የሚፈልጉት ይህ ነውና! አዎ! ጭራቅ አብዮት አሕመድ ከ666ቱ ነው።

በመካከለኛው አሜሪካ፤ በኒካራግዋ ኒካራግዋንን ሲጨፈጭፍ የነበረው አምባገነናዊ ፕሬዚደንት ሶሞዛን የወቅቱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ለፕሬዚደንት ሩስፌልት “ሶሞዛ እኮ ጭራቅ ነው” ብሎ ሲነግራቸው፥ ፕሬዚደንት ሩስፌልት፤ “አዎ! ግን የእኛ ጭራቅ ነው” በማለት መልሰውለት ነበር።

አሁን ገዳይ አብዮት አህመድ የእነርሱ ጭራቅ ነው ማለት ነው።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment