የኢትዮጵያውያን ግለኝነት (privacy) የሚደፍረው ኢንሳ (INSA) ደካማነት!!!

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 


የውጭ ሀገራት ጠላፊዎች የ142 ኢንሳ ወኪሎችን ኢ–ጦማር (email) አድራሻዎችን እና የይለፍ (የምሥጢር) ቃላትን በቀላሉ ለመጥለፍ ችለዋል። ምክኒያቱ፦ የኢንሳ ወኪሎች አስቀድሞ ሊተገበር የሚችልና አሰቱማማኝ ያልሆኑ የይለፍ ቃላትን ለመጠቀም በመምረጣቸው ነው።

ይህን መረጃ ያቀረበችልን ባለሙያ፡ አሳፋሪ ስለሆነ ክስተት እንዲህ ብላለች፦


""The passwords we discovered in use by INSA were basic (and hackable) beyond belief."


"በ ኢንሳ ጥቅም ላይ የዋሉት የይለፍ ቃላት ለማመን እስኪከብድ መሰረታዊ (እና የሚጠለፉ) ናቸው።"


"As the most tech-savvy people in Ethiopia, whose entire careers literally revolve around online and national security, their lack of secure passwords is absolutely shocking"


"እጅግ በጣም በተራቀቀ ቴክኖሎጂ ላይ እድሜ– ልካቸውን ለመሰማራት የመረጡና በብሔራዊ ደህንነት ላይ ያተኮሩ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች አስተማማኝ ያልሆኑ የይለፍ ቃላትን መጠቀማቸው በጣም አስደንጋጭ ነው።"


ኢትዮጵያ ለሀገራችንን እንደ ክፍት መጽሐፍ ማንም ያነባታል ማለት ነው። ምስጢር የሚባል ነገር የለንም፤ ጠላቶቻችን ሁሉ ስለ ሀገራችን የሚፈልጉትን መረጃ ሶፋቸው ላይ ቁጭ ብለው በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።


ለነገሩማ ተቋሙ በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገና ተልእኮው ሀገራችንን ብዙ ከሆኑት የውጭ ጠላቶቿ ለመመከት ሳይሆን፥ በማኅበራዊ ኅዋ ሰሌዳዎች (Website) ላይ ኢትዮጵያውያንን ማሸበርና፣ የህሊና ታጋዮችን ማሸማቀቅ ነው። እውቀታችንን፣ ጊዚያችንን እና ገንዘባችንን ኢትዮጵያን ከውጭ ጠላት በመከላከል ሥራ ላይ ከማሰማራት ኢትዮጵያውያኑን እየመታንና እያዳካምን ሀገራችንን ለጠላት አሳልፈን ለመስጠት እንሻለን። ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚጠቁሙን፡ ልዩ ፍተሻ የሚካሄድባቸው መንገደኞች ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች አፍሪቃውያን ብቻ ናቸው፤ ነጩ ሰተት ብሎ ይገባል/ይወጣል። ምን ዓይነት ዘመን ነው?! ምን ዓይነት ከሃዲ ትውልድ ነው!?


ይህ አሁን የተከሰተው ነገር፡ ምናልባት ኢትዮጵያን የሚጠቅም አጀንዳ ስለሌላቸው ሤራቸው ይጋለጥባቸው ዘንድ የተፈጠረ በጎ ነገር ሊሆን ይችላል። ፀረ–ኢትዮጵያ ሴራቸውማ ፈጠነም ዘገይም በሚገባ መጋለጡ የማይቀር ነው።

በነገራችን ላይ ጦር ሠራዊቱም ተመሳሳይ ክስተት ይታይበታል፤ ስለዚህ እነ አረቢያ እና ግብጽ አዲስ አበባ ድረስ፣ የሕዳሴው ግድብ ድረስ ሰተት ብለው መግባት ይችላሉ ማለት ነው። እጅግ በጣም ያሳዝናል!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment