ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከትናንትበስትያ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሳሳተና ተቀባይነት የሌለው የአፍሪካን ካርታ በድረ ገፁ ላይ በመጠቀሙ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሶማሊያ የሌለችበት የአፍሪካ ካርታ መጠቀሙንና በምትኩ ሶማሌ ላንድ ራሷን የቻለች ሀገር አድርጎ አቅርቧል ሲል ሚሞ የተባለው የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን ድርጊቱን ኮንኖታል።
መሥሪያ ቤቱ ካርታውን የተጠቀመው ባለፈው ቅዳሜ የተከበረውን የአፍሪካ ቀንን አስመልክቶ በፃፈው ጽሁፍ ላይ ነበር።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኦፊሴላዊ ኅዋ ሰሌዳው (website) የተጠቀመው የአፍሪካ ካርታ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ግዛት እንደሆነች ተደርጎ ቀርቦበታል።
በካርታው ላይ በሶማሌ ላንድ የምትገኘው ሃርጌሳ አስተዳዳር ራሷን የቻለች ሀገር እንደሆነች አሳይቷል።
ካርታው በማህበራዊ ኅዋ ሰሌዳዎች ከተዘዋወረ ከሰዓታት በኋላ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ካርታውን ከገፁ ላይ ያጠፋው ሲሆን በኢፌዴሪ አርማ(666) ተክቶታል።
ስህተቱ በፈጠረው ውዥንብር መፀፀቱን የገለፀው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ቡድኑ የኅዋ ሰሌዳን ደህንነት ለማረጋጋጥ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ኮሎኔል ዐቢይ አሕመድ ጦርነት በጣም ናፍቆታል። የሲ.አይ.ኤ አምባሳደር ሆኖ በብዙ መቶ ሺህ ተዋኅዶ ኢትዮጵያውያን መገደል ምክኒያት በሆነው፤ ለባድሜው ጦርነት ወደ ሰሜን ዘምቶ የነበረው ይህ ሰው የተዋኅዶ ኢትዮጵያውያን ደም አሁን ጠምቶታል። ለዚህም የግብጹ አል ሲሲ አምባሳደር በመሆን አንዴ ከኢሳያስ አፈወርቅ ጋር፣ ሌላ ጊዜ ከሶማሊያ፣ ጂቡቲ እና ኬኒያ መሪዎች ጋር በመምከር በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጦርነት ለመቀስቀስ እየተወራጨ ነው። በኢንጂነር ስመኘው ቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ("እንትና የሚባል ሰው ተገድሏል አሉ" ነበር ያለው አሜሪካ ሆኖ፤ አይደል?) አለመገኙትን የመረጠው ዶ/ር አብዮት አሕመድ ሞኙ የሰሜን ሕዝባችንን እርስበርስ ለማባላት ምኞቱ መሆኑ ግልጽ ነው፤ ራያ፣ ወልቃይት፣ ቤኒሻንጉል እያለ እሚቀበጣጥረውም ያለምክኒያት አይደለም።
የሱዳን አዲሱ ወታደራዊ መንግስት መሪዎች ሰሞኑን ከግብጹ አልሲሲ ጋር መገናኘት አዘውትረዋል። ግብጽ ዳግማዊ ማህዲን ካርቱም ላይ ለማስቀመጥ ወደ ሱዳን ወታደሮቿን ለመላክ በመዘጋጀት ላይ ናት።
የኢትዮጵያ ሠራዊት በዋቄዮ አላህ ልጆች፣ በሰዶማውያን እና በሴቶች መሪነት እንዲዳከም እና ሕዝቡም እራሱን ለመከላከል እስከማይችል ድረስ እርስበርስ ተባልቶ እንዲኮላሽ ከተደረገ በኋላ ከተደረገ በኋላ በዙሪያችን ባሉ ጎረቤት ሀገራት ያጠናከሯቸውን ሠራዊቶች ወደ ኢትዮጵያ መላክ ይጀምራሉ፤ ልክ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በግራኝ አሕመድ ወረራ ዘመን እንደነበረው።
ዛሬ ኢትዮጵያ እንዲህ ነው የተከበበችው፦ በኤርትራ ሳውዲ አረቢያ እና ኤሜራቶች፣ በሱዳን ግብጽ፣ በሶማሊያ ቱርክ፣ በጂቡቲ አሜሪካ፣ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ስፔይን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ጃፓን፣ ህንድ እና ቻይና በመጠጋጋት ሠፍረው "ታላቁን ቀን" በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ ግን በቀድሞዋ ግዛቷ ከኢምባሲ በቀር እና ለወደብ ከመክፈል ሌላ ምንም ነገር የላትም።
Blogger Comment
Facebook Comment