በጥቁር ህዝቦች ላይ የሚፈፀም ሴራ!!!

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ


በኡጋንዳ፤ አንድ የአሜሪካ ፓስተር በፋብሪካ ከሚገኝ ማቅለጫ ዱቄት "ተአምረኛ ፈውስ" ነው፤ "ከወባና ኤች አይ ቪ ያድናል" እያለ በመስጠት ኃምሳ ሺህ ኡጋንዳውያንን መርዟቸዋል፤ ጨቅላ ሕፃናትን ሳይቀር።


52 ዓመት ዕድሜ ያለው አሜሪካዊው ሮበርት ቦልድዊን "ሉላዊ ፈዋሽ ሚንስትሪ" በተባለው ቸርቹ አማካኝነት በጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ልብሶችን ለማገርጣት የሚጠቀሙትን ኬሚካል "ፈዋሽ ጠበል" ነው እያለ ዳንኪራ በሚደረግበት ቸርቹ ውስጥ ኡጋንዳውያንን ለመመረዝ በቅቷል።በዚህ ዲያብሎሳዊ ዕቅዱ ላይ ለተሳተፉ ደሀ ኡጋንዳውያን ስማርት ስልኮችን እየሸለመ በመደለል የቀመመውን መርዝ በፈቃዳቸው እንዲወስዱ አታሎአቸዋል።

በሌላ በኩል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ በዛምብያም አንድ አፍሪቃዊ ፓስተር ተመሳሳይ መርዝ "ጋኔን ያወጣል" እያለ ለዛምብያውያን በመስጠት ሃያ ሰባት ሰዎችን ገድሏል፤ ብዙዎችንም ክፉኛ አሳምሟል።

እነዚህ የአፍሪቃውያንን ሕዝብ ቁጥር በተለያዩ መንገዶች (ክትባት በመውጋት፣ በመመረዝ፣ በሳተላይት ጨረር በመቀቀል፣ በማኮላሸት፣ ሕፃናትን በማስወረድ፣ በማስራብ፣ ግጭቶችንና ጦርነቶችን በመፍጠር ወዘተ.) ከመቀነስ ወደ ኋላ አይሉም። ከፍተኛ ፀረ–አፍሪቃውያን ወይንም ፀረ–ጥቁር ሕዝብ ሤራ በምዕራቡ ዓለም በመጧጧፍ ላይ ነው። "አፍሪቃውያኖች የሚበሉት የላቸው ዝም ብለው ይፈለፍላሉ" በሚል ከንቱ ቅስቀሳ ሕዝቦቻቸውን ፀረ–አፍሪቃ የሆነ አቋም እንዲይዙ አድርገዋል። በአሁን ጊዜ ሰማንያ በመቶ የሚሆኑት ነዋሪዎቻቸው "ጥቁር ሕዝብ" ከፕላኔቷ ዕልም ብሎ ቢጠፋ አንዲት እንባ እንኳን አያነቡም፤ እንዲያውም "ለፕላኔታችን የተሻለ ነው" ነው የሚሉት።

ዕቅዳቸውም ወይም ዓላማቸው ከእንስሳቱ በቀር አፍሪቃውያንን ሙልጭ አድርጎ በማጥፋት እነርሱ ወደ አፍሪቃ መጥተው መስፈር ነው። ከኑክሌር ጨረር ወይም የተፈጥሮ ለውጥ ከሚያስከትሏቸው ክስተቶች (ቅዝቃዜ፣ የውቂያኖስ ጎርፍ፣ ሙቀት…) ጋር በተያያዘ፡ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና እስያ ሰው–አልባ የመሆን እድል አላቸው። ብቸኛ ተስፋቸው በተፈጥሮ ኃብት የታደለችው አፍሪቃ ናት። ተማሪዎቻቸው በየትምህርት ቤቱ ስለዚህ ክስተት እየተማሩና እራሳቸውንም እያዘጋጁ ነው።

እንደምናየው ይህን አስመልክቱ አፍሪቃውያኑ እውቀቱ እንዲኖራቸው አይፈቅዱላቸውም፤ በተቃራኒው ይኮንኗቸዋል፣ እራሳቸውን እንዲጠሉ ይገፋፏቸዋል፣ ዛሬ ቢነቁ እንኳን ነገ መልሰው ያስተኟቸዋል፣ የተፈጥሮ ኃብቱን እንዳይነኩ/እንዳይጨርሱባቸው እርበርስ እንዲባሉ፣ እንዲሰደዱና ጠፍተው እንዲቀሩ ይተናኮሏቸዋል።

የዛሬይቱን ኢትዮጵያን እንደ ምሳሌ ብንወስድ፤  "ረጅም እድሜ የሚያስገኘው የመጠጥ ውሃ የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው" በማለት ጥንታውያን ግሪኮች ይናገሩ ነበር።  የስነ ሕይወት / የብዝሕ ሕይወት ሊቅ እና ዓለማቀፋዊ አሳሽ የነበረው እውቁ የሩሲያ ተወላጅ ቨላድሚር ኒኮላይ ቫቪሎቭ፤ "ኢትዮጵያና አፍጋኒስታን የሰው ልጅ ስልጣኔ ምንጮች ናቸው" ሲል ከመቶ ዓመታት በፊት ጠቁሞ ነበር።

እስኪ አሁን እራሳችንን እንጠይቅ፤ ለምንድን ነው ብርቅና ልዩ የተፈጥሮ ኃብትና ሥልጣኔ ባላት ኢትዮጵያ ይህን ያህል የውዳቂዎች መጫዎቻ የሆነችው? ለምንድን ነው እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የውሃ ሃብት ባላት አገራችን፤ ሕዝቦቿ ውሃ ላይ ተኝተው ሁሌ የሚጠሙት?


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment