ሳልሳዊ ቴዎድሮስ ማን ነው?


✍ አየነው ገብረመስቀል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ስለ ሳልሳዊ ቴዎደሮስ በተለያየ መፅሃፍ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ለማስታወስ ያክል ድርሳነ ኡራኤል ላይ “ከንጉሱ ናኦድ ወገን የሆነ የስሙ ትርጉም “ቴ” የተባለ ይነግሳል” ይላል፡፡በሰማእቱ ፊቅጦር ገድል ላይ ደግሞ ሰማእቱ ለእናቱ “እናቴ ሆይ በኋለኛው ዘመን እግዚያብሄር ለኢትዮጵያዉያኖች ደግ ንጉስ ያስነሳል በዚያን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በአለም ላይ ታብባለች…….” ብሏታል፡፡ ፉካሬ ኢየሱስ ላይ ደግሞ “ታሪካዊ እና ደገኛ ንጉስ ይነግሳል በዚያን ጊዜ የአንድ ላም ወተት የአንድ በሬ እሸት ይበቃል” ይላል፡፡ሰማእቱ ቴዎድሮስ ገድል ላይ ደግሞ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መደሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ቴዎድሮስ ሆይ እኒህን የሮም ነገስታት ላጥፋቸውና አንተን ላንግስህ ወይስ በኋለኛው ዘመን በስሜ ያመኑትን የሚሰበስብ በስምህ የሚጠራ በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ላስነሳ አለው፡ቅዱሱም ጌታዩ ሆይ በስሜ የሚጠራ በስምህ የፀኑትን የሚሰበስብ በነፃ አውጭ ሃገር ኢትዮጵያ አንግስ አለው፡፡“በገድለ ተክለ ሃይማኖትም ቅዱሱ የንግስና ቅባት፤ ከነይኩኖ አምላክና ዘርአያእቆብ ቀጥሎ በ8ተኛው ሽህ ለአንድ ሰው ብቻ እንዲፈላ ተቀምጧል፡፡ ክብረ ነገስት ላይ ጠቢቡ ሰለሞን 3 ልጆችን ወለደ አንዱም በኢትዮጵያ(ቀዳማይ ምኒልክ)፤አንዱ በሮማ(መስቀለ ክርሰቶስን ያወጣች የእሌኒ ልጅ የቆስጠንጢኖስ እጅግ ቅድመ አያት)፤አንዱ ደግሞ በእስራኤል ላይ የነገሰው ሮብዓም እሱም የማሪያም ልጅ ሁሉን ቻይ ከዚህ የዘር ግንድ በስጋ ተወለደ) አነገሳቸው ይላል፡፡ከነዚህም ይህ ቀዳማይ  ምኒልክ በሃገራችን የሰለሞናዊ ስርዎ መንግስትን ከ980ዓ.ዓ-920 ዓ.ም የልጅ ልጆቹ በኢትዮጵያ አሰፋፍተው ሲገዙ ኖሩ፡፡ቀጥሎ ከ920-1270 (የመራ ተክለ ሃይማኖት የልጅ ልጆች ቅዱስ ይምርሃነ፡ቅዱስ ሃርበይ ወይም ገ/ማሪያም፡ቅዱስ ላሊበላ ፡ቅዱስ ናኩቶለአብ) የዛግዌ ስርዎ መንግስት ቢያስተዳድርም በፃድቁ ተክለ ሃይማኖት በኩል መልሶ ሰለሞናዊ አስተዳደር መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጠረ፡፡በታሪክ እንደምታውቁት ይኩኖ አምላክ ነገሰ፡፡በዚህ የነገስታት ታሪክ የምኒልክ የዘር ግንድ የሆነ በኋለኛው ዘመን እንደሚነሳ በመጠኑም ቢሆን ተዘግቧል፡፡

ዳግማዊ ቴዎድሮስም በአፈ ታሪክ ደረጃ ሲውራ ስለሰማ እሱ ራሱ መስሎት ነው ራሱን ቴዎድሮስ ብሎ የተነሳው፡፡ እናም ይህን እንደመነሻ ያነሳሁት ስለ ሳልሳዊ ቴዎድሮስ ምልክትን ለሚሻ ለዚህ ለስምነተኛው ሽህ ትውልድ መፅሃፎቹን በመፈለግ እንድመረምሩ ለመጠቆምና ሙሉ ፅሁፉን እንድታነቡት እንድሁም ሁሉንም የአባቱን የክቡር ዳዊትን 7 ቱን ሃብታት የተሰጠው ቅዱስና ንጉስ፡ነብይና ካህን የሆነውን ሳልሳው ቴዎድሮሰ ጊዜው ገና መስሏችሁ ሳታውቁት እንዳታገኙት፤እኔም ስሙና ተልእኮው ስላስቀናኝ ብቻ፤ እንኳን መፃፍ መናገር የማልችል ድዳ በዚች በተቆራረጠች ፅሁፌ ለመግለፅና(…) ወደድኩ፡፡

የተከበራችሁ ኢትዮጵያዉያን ሆይ የሰነፉ ባለፀጋና የባህራን ታሪክ በናንተ ላይ እንዳይፈፀምባችሁ አእምሮ ቀሊላን አትሁኑ፡፡ሄኖክ እንዳለ እንደ ባለአእምሮ አብርሃም አስቡ፣ፈልጉ፤አምልኩም፡፡አለም በኖህ ዘመን ዉሃው እየሞላባቸው ያገቡ ይጋቡ ነበር፡፡ከበሮውንም ከፍ አድርገህ ምታ ይል ነበር፡፡ታሪክ እራሱን ይደግማል የሴት ልጆች ምድርን ገነት አደረግናት ይላሉ ወደ ሰማይ የሚያርግ የላቸውምና፡፡እነኝህ ሆዳቸው አምላካቸው፡ ክብራችው በነውራቸው ነውና እንደሚታረድ በግ እረኛቸው ሞት(ድያብሎስ)ይዟቸው ሲኦል ሊወርድ 11ኛ ሰዓት ላይ እንገኛለን፡፡

………….ስታነቡ እንዳይበዛባችሁ እዚህ ላይ ለዛሬ ያዝ ላድርገውና ወደፊትም የዚችን አለም የዉሸት ብርደልብስ ራሱ ሳልሳዊ ቴዎድሮስ እስኪገልፀው ድረስ እኔን  የማውቀውን የተሰማኝን(የተገለፀልኝን አላልኩም)እብዱ አሊያም ጉዱ ካሳ ልትሉኝ እንደምትችሉ እያወቅሁ የማወራላችሁ ይሆናል፡፡መሳደብ፤መተቸት፤ዉድቅ ማድረግ ሁሉ ድሞክራሲያዊ (የአጋንንት ድርሰት)መብታችሁ ነው፡፡ 

ድያብሎስ ይዟችሁ ሊወርድ 11ኛ ሰዓት ላይ እንገኛለን፡፡እኔ እንደሚገባኝ ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ በተለያየ ጊዜ ለትውልዱ ለረጅም አመታት መልእክቱ እንደደረሰው ነው፡፡ምክንያቱም እግዚያብሄር ለእያንዳዳችን እኩል እግዚያብሄርን የመፈለገ፤የማወቅ፤የማግኘት፤የመውደድና የማምለክ እድል ተሰቶናል፡፡በራሳችን ምርጫ ግን ድያብሎስን አባትም አምላክም ካደረግነው እንደምትሉት ድሞክራሲያዊ መብታችሁ ነው፡፡መጨረሻችሁ ግን ከእግዚያብሄር ባለሟልነት መሻር ነው፡፡መሻር ብቻ አይደለም ከምድርም ትወገዳላችሁ፡፡እግዚያብሄር ታገሰ፤ተሸከመ ለረጅም ዘመንም ዝም አላችሁ፡፡አሁን ግን እናንተም ነገስታቶቻችሁም፤እውቀታችሁም መሳሪያችሁም ላይታደጋችሁ ስማችሁም ከምድር ላይ ሊደመሰስ የጥንቆላ፤የዝሙት፤የማፍያ፤የግድያ፤የምንፍቅና፤የጦር መሳሪያወቻችሁ ሁሉ ጋር አሻራችሁ  እስኪጠፋ ድረስ እግዚያብሄር አምላክ ሊያጠፋችሁ ወሰነ፡፡ዛሬ አብይና የሃገሪቱ ምሁራን በየቦታው ያለው አመፅ ብንወያይ ይቀረፋል፤አሊያም የህውሃት እጅ አለበት ይላሉ፡፡ወዳጄ እስኪ የተዘረጋች የልዑልን እጅ አብይ ወይስ ይህ የተረትተረት (ሳይንስ) እውቀታችሁ ያጥፋት አሊያም ያድናችሁ ይሆን?የሚመረው ሀቅ ግን አብይም ሆነ እናንተ የሰላም ሰው ብላችሁ ራሳችሁን የኮፈሳችሁ ሁሉ ትሞታላችሁ እንጅ በህይወት አትኖሩም፡፡እግዚያብሄር እንደልቡ የሚሆንለት ንጉስ ቀብቷል፡፡እናንት የጣኦት ጳጳሳት ሆይ እግዚያብሄር ለራሱ እንደልቡ የሚሆንለትን ጳጳስ ቀብቷል፡፡ሁላችሁ ነገስታትና ጳጳሳት ጊዚያችሁ ተፈፅሟልና ስልጣናችሁን ጣሉና ነፍሳችሁን አድኑ፡፡ አብይ ሆይ ለዚች 3 ቀን ለማትሞላ አመታትህ የማትሰራውን ስራ የማታመጣውን ሰላም አመጣለሁ እያልክ ህዝቡን አታታል፡፡አንተ ከሰማይ የተላክ አይደለህም፤የእምየ ኢትዮጵያም የወደፊት ንጉስ አይደለህም፤ዘመንህም እጅግ አጭር እንጅ አንተ እንደምትለው ትንቢት አለኝ እያልክ ህዝቡ በሚያየው መከራ ንሰሃ እንዳይገባበት አታዘናጋ?ይህ ጠጠር ያለ ጥፋት እና ቁጣ ነውና ምድርንም ሳያፀዳ የሚቆም ሰላልሆነ ህዝቡን የውሸት ተስፋ እየሰጠህ አታዘናጋው፡፡የሚነግሰው ንጉስ ሳልሳዊ ቴዎድሮስ ነው፡፡፡፡፡፡ከመፍጠር ዉጭ ሁሉን ያደርግ ዘንድ ተሰጠው፡፡ፍጥረት ሁሉ፤ምድርም ሁሉ ለእሱ ተላልፋ ተሰጠች፡፡እሱም ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አለምን ነው የሚያሥተዳድረው፡፡አንተ ብትደበቅ ይሻልሃል፡፡ይልቅስ ስልጣንህን ወደህ አስረክብ እሱ ሊወጣ ዝግጅት ላይ ነውና የቁጣው ገፈት አንተ ላይ እንዳይወድቅብህ፡አጠፋፍህ ዘግናኝ እንዳይሆን ስልጣንህን ለቅዱስ ሳልሳዊ ቴዎድሮስ አስረክብ፡፡እሱ እንኳን አንተን የአለምን ነገስታት እንደጨው የሚያቀልጥበት ሃይልና ስልጣን ከአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ተቀብሏል፡፡የመጀመሪያው ታአምር አንተ ላይ እንዳይሆን ስልጣንህን ለቀቅ፤ህዝቡንም የአህያ ባል ከጅብ አያድንምና እኔ የናንተን ሰላም ማምጣት አልችልም የእስራኤል አምላክ ይቅር እንድላችሁ ንስሀ ግቡ በላቸው፡፡ይህ የእስራኤል አምላክ አንተንም ፈጥሮሃልና፡፡
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment