በመላው ዓለም የሚገኙ ብዛት ያላቸው ሰዎች ስለ ኦሮቶዶክስ ክርስትና ምን ታስባለህ? ባማለት ፕሮፌሰሩን ጠይቀዋቸዋል። ሲመልሱም፦
ኦሮቶዶክስ ክርስቲያኖች ይወዱኛል፤ ለምን እንደሆነ አላውቅም ግን፡ እንደሚመስለኝ፡ የሆነ ግንዛቤ አለኝ፦
ብዙ ደብዳቢዎች ከብዙ ሃይማኖት መሪዎች ይደርሱኛል፤ ከአይሁዶች፣ ከክርስቲያኖች፣ ከሙስሊሞች። አብዛኛዎቹ ደብዳቤዎች ግን ከኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ናቸው።
ይቅርታ አድርጉልኝ፤ ፕሮቴስታንቶችን እና ካቶሊኮችን ማጣጣሌ አይደለም፤ የራሳቸው የሆነ ምክኒያት ሊኖራቸው ይችላልና።
ነገር ግን፡ በምዕራቡ ዓለም ሰዎች ክርስትናን የሚያዩት አለማዊ የግንዛቤ ንድፈ–ሀሳብ የሚነጸባረቅበት የእምነት እሴት እንደሆነ አድርገው ነው።
በምዕራቡ ዓለም ክርስቲያን ለመሆን፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ለኃጢአተኞች ቤዛ አድርጐ መስጠቱን ብቻ መቀበል በቂ ነው። ለምን ይህ እንደሆነ ይገባኛል፤ ነገር ግን በዚህ ላይ ብቻ መወሰናቸው አደጋ ያስከትላል።
ኦርቶዶክሶች ግን በዚህ ላይ ብቻ አይወሰኑም፤ ኦርቶዶክሶች “መስቀሉን ተሸክመህ እየተሰነካከልህም ቢሆን ኮረብታውን ውጣ” ብለው ያምናሉ፤ ለእነርሱ መስቀሉ የእውነታ ማዕከል ነው፤ ሁሉም ነገር መስቀሉ ላይ ነው።
ይህን ፕሮቴስታንቶችና እና ካቶሊኮችም ያምኑበታል፡ ነገር ግን ዝቅተኛ ዋጋ ነው የሚሰጡት፤ ይህን ዋጋ አለመስጠታቸው ግን በተለይ በአሁኗ ዓለም በጣም አደገኛ ነው።
ኦርቶዶክሶች፦ “ወደሚቀጥለው ሕይወት ስትሸጋገር ስቃይን፣ ሞትን እና ዳግመኛ መወለድን በእውነታ ማዕከል በሆነው በመስቀሉ ላይ ታገኘዋለህ።”ብለው ያምናሉ።
ይህን መቀበልና ማቀፍ ግድ ነው፤ ይህ ከባድ ሥራ ነው፤ ምክኒያቱም ጉድለቶችህን፣ የእውነታን ጉድለቶች፣ የህልውናን አሳዛኝ ሁኔታ፣ ሞትህን፣ የሰው ልጅን ክፉነት ሁሉ መቀበል ግድ ነውና።
እነዚህ አስገራሚ የሆኑ እና በጣም የሚጠይቁ መስፈርቶች ናቸው። ማድረግ የምትችለውን ታደርጋለህ፤ መስቀልህን ማንሳት ብቻ ሳይሆን ኮረብታውን እየተሰነካከልክ በመውጣት ወደ እግዚአብሔር ከተማ፣ መልካም ወደሆነው ትጓዛለህ።
ኦርቶዶክሶች ይህን ጥሩ አድርገው አዘጋጅተውታል፤ መድረሻ ግባቸው ይህ ነው፤ የኑሮ ትርጉማቸው ይህ ነው፤ ሙሉ በሙሉ ክርስቶስን መምሰል ነው፤ ክርስቶስ አርማቸው ነው፤ ክርስትና እንደሚያስተምረው፦ አምላክ ከ ቅድመ–ፍጥረት የነበረውን የታሪክ ድፍርስ፣ የሁኔታዎች ምስቅልቅል ወደ መኖሪያ ሥርዓት ለመለወጥ ክርስቶስን አርማው አደረገው።
እውነተኛ ንግግር ነው፤“መስቀሉን በጀርባህ ተሸክመህ እየተሰነካከልህም ቢሆን ኮረብታውን ውጣ”፤ ይህ በጣም ወጥ የሆነ ጽንሰ–ሐሳብ ነው።
ኦርቶዶክሶች ይህን ጽንሰ–ሐሳብ ፊት ለፊት በማውጣት የእምነታቸው ዋና መሠረት እንዲሆን አድርገው በመጠበቃቸው በጣም ጥሩ ሥራ ሠርተዋል
ስለ ኦሮቶዶክስ ክርስትና ያለኝ ሃሳብ ይህ ነው!
Blogger Comment
Facebook Comment