በዘረኝነት ለሚማቅቁ ፍጡር ሁሉ የተቀመመ ጤና አዳም በ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ


ማስታወሻነቱ በሠው ዘር ስም ባለማወቅ ሕይወታቸውን ላጡትና በቁም ለሚሰቃዩት ወገኖቻችን ፈውስ አንዲሆን፦

በዘረኝነት ለሚማቅቁ ፍጡር ሁሉ የተቀመመ ጤና አዳም በ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ

"እንዲሁም የዘር ልዩነትን በሚመለከት ረገድ፡ አንዱ ዘር ከሌላው ዘር ፥ ይበልጣል፣ ይሻላል የሚለው እምነት ዋጋ እንዲያጣ ሆኖ ካልተወገደ ፤ በአንድ ሀገር ውስጥ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ካልተሰረዘ ፤ አንድ ሰው በቆዳው ቀለም ብቻ የመብቱ መጓደል ካልቀረ ፤ ለሁሉም ሰው የዘር ልዩነት ሳይታሰብ እኩል የኢኮኖሚና ተመሳሳይ ሰብአዊ መብት ካልተሰጠው ፤ እነዚህ፡ በዚህ፡ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ሁሉ እስካልተፈፀመበት ቀን ድረስ፡ ሁላችንም የምንደክምለትና የምንመኘውን፡ የዓለም በህግና በደንብ መተዳደር ሊደረስበት የማይቻልና እንደዚሁም በአለም ላይ ሰላም ጸንቶ እንዲኖር የምናደርገው ሙከራ ሁሉ ባዶ ምኞትና መና ሆኖ የሚቀር ግብ እንዳይሆን፡ የሚያሰጋ መሆኑ አስተምሮናል፡ እኛም መስክናል ። ሠላም እንዲኖር የሁላችንም ተባብሮ መስራት ይጠይቃል ፨



በአፍሪቃም ውስጥም ሆነ ባዓለም ላይ ያሉ የጥቁር ህዝቦች ከዘረኝነት ቀንበር ነፃ እስካልወጡ ድረስ በልጽገናል ሠልጥነናል አንድ ሆናል ሁሉ በልቶ ሠላም አድሯል ማለት አስቸጋሪ ይሆናል...”

የሁላችንም ዕድል አንድ ነው ወይ መጥፋት ወይ መዳን ሁላችንም ጥፋት አንፈልግም! ሁላችንም በዓለም ላይ ድንቁርና ድህነት በሽታ እንዲወገድ እንፈልጋለን ዕድል ስናገኝ ግዜ ሣያልፍ የሚቻለንን እናድርግ ደስ ከማይል ዕርምጃ እንዳን ለዓለም ሠላም ፨

ለመኖር ከፈለግን በጊዜያችን ከገጠመን ከባድ ችግር ለመዳን ቁልፉን የት ነው የምናገኘው?



ከሁሉ አስቀድሞ የሰውን ልጅ ከእንስሳ አስበልጦ የማሰብ ኃይል ወደ ሰጠው ፈጣሪያችን መዞርና መመልከት አለብን: በአምሳሉ የፈጠረው ሰው ራሱን እንዲያጠፋ እንደማይተው ማመን አለብን:ከዚህም ከዚያም ወደ ራሳችን መመልከትና ራሳችንን መመርመር አለብን: ካሁን ቀደም ያልነበረውን መሆን አለብን: ካሁን ቀደም ከነበረው ይልቅ ደፋር ፣ ብርቱ ፣ መንፈሰ ጠንካራ ፣ ልበ ሰፊ ፣ አርቆ አስተዋይ ሆነን መገኘት አለብን።ጥቅምን የተወ ለአንድ መንግስት ሳይሆን ታማኝነቱ ለመላው የሰው ልጅ ያደረገ አዲስ ዘር መሆን አለብን ። ይህ ነው ታላቁ ፈተና።



ወጣቶች በጣም ፍቱን በሆነና በተቀነባበረ የተጣመመ መሰሪ ዜናና ፕሮፖጋንዳ ህቡእ ሰሆነ መንገድ ይጋለጣሉ። እንደ ንጉሥ ለክርስትያንም ሆነ ሙስሊም ሆነ እምነት ለሌላቸው እኔ እኩል ነኝ!"
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment