በእንጦጦ አዲስ አበባ መስቀል ሊሠራ ነው። ክቡር መስቀሉ የሚሠራው በደብረ መድኃኒት አቡነ ሃብተማርያም፣ ቅድስት ልደታ እና ቅድስት አርሴማ ገዳም ጫፍ ላይ ነው። ከዚህ ተራራ ጫፍ ሆኖ በመላው አዲስ አበባን አካባቢዋ ሊታይ ይችላል፤ ማታ ላይም በደንብ እንዲታይ መብራት ይኖረዋል።
ይህ የተቀደሰ ሥራ ከሁሉም ሥራዎች ቀድሞ በፍጥነት መከናወን ይኖርበታል።
በመጭዎቹ ወራት አዲስ አበባውያን የተዋሕዶ ልጆች በሚከተሉት ሁለት ነገሮች ይፈተናሉ፦
፩ኛ፦ ለክቡር መስቀሉ ምን ያህል ፍቅር እንዳላቸው በማሳየት
፪ኛ፦ በሊቢያ በሙስሊሞች ለተሰውት ሰማዕታት አስከሬን እንዴት አቀባበል እንደሚያደርጉ
በመቅሰፍት የተመታችው አዲስ አበባ መዳን የምትችለው በፖለቲከኞች የተመሰቃቀለ ጭንቅላት ሳይሆን በክቡር መስቀሉ ነው። ቶሎ እናሠራው! መስቀል ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው!!!
ልዑል እግዚአብሔር በመስቀሉ ኃይል ኹላችንንም ከልዩ ልዩ ዓይነት መከራ ይጠብቀን፡፡
Blogger Comment
Facebook Comment