ፖፕ ፍራንሲስ የካቶሊክ ቄሶች ሴት መነኮሳትን የወሲብ ባሪያ ማድረጋቸውን አመኑ


ፖፕ ፍራንሲስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃትን እንደሚፈፅሙና ባሪያ አድርገው አስቀምጠዋቸው እንደነበር አመኑ።

በዚህም ምክንያት ከሳቸው በፊት የነበሩት ፖፕ ቤኔዲክት በካህናቱ ተደጋጋሚ ወሲባዊ ጥቃት ይደርስባቸው የነበሩ የሴቶች መነኮሳት ጉባኤን ለመዝጋት ተገደዋል።


ፖፑ አክለውም "ችግሩ ከፍቶ የወሲብ ባሪያ የተደረጉ የሴት መነኮሳትን ጉባኤ መበተናቸው ይበል የሚያሰኝ ስራ ነው" ብለዋል።
ፖፕ ፍራንሲስ ሴት መነኮሳቱ በካህናቱ ወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ሲያምኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ቤተክርስቲያኗ ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ብታደርግም አሁንም ድረስ ጥቃቱ እየተፈፀመ እንደሆነ አልካዱም።

ፖፕ ፍራንሲስ ይህንን የተናገሩት ታሪካዊ በሚባለው በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸው ላይ ለሚገኙ ጋዜጠኞች ነው።
ካህናቱና ኤጲስ ቆጶሳቱ መነኮሳቱ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውንም ቤተክርስቲያኗ እንደምታውቅና ለመቅረፍም ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።


ፖፕ ፍራንሲስ በሴቶች መነኮሳት ላይ የሚደርስ የወሲብ ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ የተንሰራፋ መሆኑን አምነው በተለይም በአዳዲሶቹ ጉባኤዎች ላይ ስር የሰደደ ነው ብለዋል።

በባለፈው ህዳር ወር ላይ የአለም አቀፉ የካቶሊክ ሴት መነኮሳት ማህበር በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያለው ጥቃት ላይ ያለውን ዝምታና ሚስጢራዊ ባህሉን ማውገዛቸው የሚታወስ ነው።



ከቀናት በፊትም የቫቲካን የሴቶች መፅሄት ጥቃቱን አውግዞ በአንዳንድ አካባቢዎችም በካህናቱ ተደፍረው የፀነሱ ሴት መነኮሳት እንዲያስወርዱ እንደሚገደዱም ዘግቧል።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment