ፓስተር ዋልተር ማጋያ የተባለዉ የዚምባብዌ ሰባኪ ለብዙ ጊዜ ምዕመናንን ከ ኤች አይ ቪ ኤድስ እፈዉሳለሁ እያለ ከሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር እዉቅና ያላገኘ መድሃኒት እያደለ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ሲሰበስብ ቆይቷል።
የፓስተሩን ተግባር ከዚህ በላይ አልታገስም ያለዉ የዚምባብዌ መንግስት ባለፈዉ ህዳር ወር ማጋያን አስሮታል።
ለምን ማረጋገጫ የሌለዉ መድሃኒት ሰጠህ ተብሎ ሲጠየቅ 'መድሃኒቱ ሙሉ በሙሉ ተፈጥሯዊ (ኦርጋኒክ) ስለሆነ የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለዉ በማሰብ ነዉ' የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
የዚምባብዌ ፍርድ ቤት ግን የሰጠኸዉ ምላሽ አላሳመነኝም እናም ከጥፋትህ ትማር ዘንድ 700 ዶላር ቀጥቼሃልሁ ብሎታል።
ፓስተር ዋልተር ማጋያ ባለፈዉ አመትም በተመሳሳይ የልብ ድካምን በሊፒስቲክ (የከንፈር ቀለም) አድናለሁ እያለ ሊፒስቲክ በብዛት ይሸጥ እንደነበርም ፖሊስ ደርሼበታለሁ ብሏል።
ፓስተር ማጋያ የዚምባብዌ ኢኮኖሚ ሲወድቅ የመዳንና የገንዘብ ተአምራትን እንፈጥራለን እያሉ ብቅ ካሉ ፓስተሮች መካከል አንዱና ብዙ ተከታይ ያለዉ ነዉ።
ዚምባብዌ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት መካከል ስድስተኛዋ ከፍተኛ ኤች አይ ቪ ኤድስ ተጠቂ ያላት ሀገር ነቸ።
1.3 ሚሊዮንየሚሆኑ ዜጎቿ ከኤች አይ ቪ ኤድስ ጋር ይኖራሉ።
Blogger Comment
Facebook Comment