የኢትዮጵያ ችግር የገንዘብ ችግር አይደለም

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ፔፕሲ፣ ወተት፣ እንቁላል፣ ቡና፣ ወርቅ፣ እጣን እና ከርቤ…ፀረ– ክርስቶሱ እጁን ያላስገባበት ቦታ የለም። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ ሰብዓ ሰገል ኢትዮጵያውያን የእጅ መንሻ ይሆን ዘንድ ይዘዋቸው የሄዱት ስጦታዎች፤ ወርቅ፣ እጣን እና ከርቤ ነበሩ…. "ቀስተደምና" / "Rainbow" ደግሞ የጌታችን እናት መቀነት ነው።

ቢሌይነር ሼኹን አዲስ ለመረጡት የኢትዮጵያ መንግስት ሲያዘጋጁት፤ መፈንቅለ–መንግስቱ ከመካሄዱ ከጥቂት ወራት በፊት ሳውዲዎች "አሰሩት" ተባለ። ግን ይህ ውሸት ነው!

ስውዬው አልታሰረም። በርግጥ የታሰረው ለኢትዮጵያ መዋል የሚገባውና በአረቦቹ የተዘረፈው የ"ድሆቹ" የኢትዮጵያውያን ገንዘብ ነው። የኢሳያስ አፈወርቂን ኤርትራን በገንዝብ እጦት ካንበረከኩ በኋላ ኢትዮጵያንም የውጭ ምንዛሬ እጦት ቀውስ ውስጥ እንድትገባ አስገደዷት፤ በዚህም ወደ እነርሱ እንድትመጣና እንድትለምን አደረጉ። አሁን በቁጥጥራችን ሥር ናት ብለው ስላመኑ ዶ/ር ሸህ አላሙዲንን "ለቀቅነው" አሉን። ከደርግ መንግስት በኋላ ክፉኛ የተራቆተችውን/ያራቆቷትን ኢትዮጵያን ለመበዝበዝ ከልጅነቱ ጀምሮ በሉሲፈራውያኑ የተዘጋጀው ዶ/ር አላሙዲን አሁን "ታስሬ ነበር" በማለት፤ እንባ የሚያነባውን አዞ ከበጉ መለየት የማይችሉትን ሞኝ ኢትዮጵያውያን ልብ ለመንካት ይሞክራል፤ በዚህም ኃብታቸውን መሟጠጡን ይቀጥልበታል። እንደ ጃዋር የመሳሰሉት ወስላቶች የእርሱ ተቃዋሚዎች መስለው የሚለፈልፉትን ፍየሎች አትስሟቸው፤ ውሸት ነው፤ ሣር ቤት ባለው የአውሬው በረት ውስጥ እበት እየለቀሙ ድራማ የሚሰሩ ተዋንያን ናቸው። ሁሉም አላማቸው አንድ ነው፦ ኢትዮጵያን እና ተዋሕዶ እምነቷን ማጥፋት። በተለይ አሁን አገራችንን እየመሩ ያሉት (የቀበሌ መሪ እንኳን መሆን ብቃት የሌላቸው ናቸው) የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው፤ ይህን ማየት የተሳነው፡ ወይ መነጽር የሚያስፈልገው፣ ወይ ደግሞ የአገሩ ጉዳይ ግድ የማይሰጠውና የህፃናቱ ወደፊት የማያስስበው ሰው ብቻ ነው።

ዶ/ሮች በየቦታው ብቅ ብቅ አሉ!
የ ዶ/ር ማዕረግ = 666
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment