ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በአሁኑ ዘመን ይህችን ምድር በመምራት ላይ ያለው ዲያብሎስ ነው። ስለዚህ በእያንዳንዱ አገር በመሪነት ቦታ ላይ መቀመጥ ያለባቸው የእርሱን ተልዕኮ ለማሟላት ፈቃደኞች የሆኑት ሰዎች ብቻ ናቸው። በኢትዮጵያ ያየነው ዓይነት መፈንቅለ–መንግስት ለቬኔዙዌላም ታስቧል፤ ልዩነቱ በኢትዮጵያ አገልግሎታቸውን የጨረሱት ፖለቲከኞች ወደውም ይሁን ተገድደው ከስልጣን ሲሰናበቱ፤ የቬኔዙዌላው ሌላ ወስላታ ማዱሮ ግን ፈቃደኛ አይደለም። ስለዚህ፡ እራሳቸው ያስቀመጡትን ይህን ሶሻሊስት አሁን ጠምደውታል፤ በሌላ አገር ጉዳይ የማዘዝ መብት እንዳላቸው፡ "ከስልጣን ውረድ፣ ጊዜህ አብቅቷል ይሉታል።!" በዚህም እንደ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኢራን እና ቱርክ የመሳሰሉ የድራማው ተካፋዮች በቁጥጥር ሥር እንዳሉ ተቃዋሚዎች ተቃራኒውን ሚና ለመጫዋት ይገደዳሉ።
የወስላታው ፈላስፋ ጆርጅ ሄገል ዲያሌክቲክስ (Thesis + Antithesis = Synthesis)። በአገራችንም እየሠሩ ያሉት ሥራ ይህን ይመስላል፤ የራሳቸው የሆነውን ዐቢይን ስልጣን ላይ አወጡት፤ ከሩቅ የሚቆጣጠሩትን ተቃዋሚ ደብረጽዮንን (ፀረ ጽዮን) በተቃራኒው በኩል አስቀመጡት፤ ሁለቱ ሲፋጩ ለተፈለገው የሕዝብ ቁጥር ቅነሳ (depopulation) ጦርነት ይካሄዳል ሰው ያልቃል ማለት ነው። አቶ መለሰ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂ በባድመ ጦርነት ለአንድ ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ሕይወት መቀጠፍ መሣሪያ ለመሆን እንደበቁት።
ልብ ብለን ካየን፤ በየአገሩ በ666ቱ አውሬ የሚመረጡት ሁሉ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ፣ ልምድ የሌላቸው ወጣት ፖለቲከኞች ናቸው። ልክ እንደ ፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ማክሮን (በጊዜው 39)እና የቬኔዙዌላው ተቃዋሚ መሪ ሁዋን ጋይዶ (35ቱ ነው)፤ ዐቢይ አሕመድም ከዓመት በፊት በፍጹም የማይታወቅ ሰው ነበር። እነ መንግስቱ ኃይለማርያምም በጣም ተመሳሳይ የሆነ አመጣጥ ነበር የነበራቸው። በአንድ ነገር ግን እርግጠኞች መሆን አለብን፡ እርሱም፤ እነዚህ ቅጥረኞች ሁሉም በአንድ ወቅት በአሜሪካ የስለላ ድርጅት(CIA) ትምህርት ተቀብለዋል፤ ተመልመለዋል።
Blogger Comment
Facebook Comment