ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
[ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፲፩፥፵፫]
በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ፥ በከበረችም በግብጽ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል፤ የልብያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይከተሉታል።
የቱርክ መንግሥት ወደ ሱዳንና ሶማሊያ እንዲስፋፋ እየተደረገ ነው፦
ዒላማቸውም ኢትዮጵያ ናት…
እነ ሆንዱረስ፣ ጓቴማላ ቶጎና ሌሎች የደቡብ አሜሪካና አፍሪቃ አገራት ኢምባሲዎቻቸውን ወደ ኢየሩሳሌም ለማዞር
ሲወስኑ፣ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ያለምንም ግዴታ ጸረ–ክርስቶሷን ቱርክና ባቢሎን አረቢያን ለምደገፍ ወስነዋል፤
በዚህ መልክም መላው የመጽሐፍ ቅዱሷን ኢትዮጵያን (ሱዳንን፣ ሶማሊያንና ቻድን) በአንድ ላይ አድርጎ የጸረ–ክርስቶሱ
ደጋፊ ለማድረግ ሤራ ተጠንስሷል። ክርስቲያኖች የጸረ–ክርስቶሱ ደጋፊ ሊሆኑ ስለማይችሉ፤ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
ፈጥና ይህን የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ውሳኔ (በቱርክ አምባሳደር የነበሩት የፕሬዚደንት ሙላቱ እጅ ይኖርበት
ይሆን?)ማውገዝ ይጠበቅባታል።
ጸረ–ክርስቶሷ ቱርክ ርካሽ በሆኑትና በኬሚካል በተጨማለቁት እቃዎቿ፣
በአገሯ እንኳን በከለከለቻቸው የቴሌቪዥን ድራማዎቿ ኢትዮጵያውያንን እየበከለች ነው፤ ውሃውን፣ እህሉን፣ ስኳሩን፣
ጨርቃጨርቁን፣ ምድጃውን ወዘተ።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ ምዕራባውያኑ እስከ አፍንጫዋ ያስታጠቁላትን የጦር
ሠራዊቷን በሶማሊያ፣ በሱዳን እና በቻድ በማስፈር ኢትዮጵያን በመክበብ ላይ ትገኛለች። እኛ የራሳችን የሆኑትን /
የነበሩትን የባሕር ዳርቻዎቻችንን እንደ ህጻን ተታለን ለጠላቶቻችን ስናስረክብ፤ ጠላት ደግሞ እንዳፈቀደው የጂቡቲን፣
የኤርትራን፣ የሶማሊያንና የሱዳንን የባሕር መውጫዎች ተከራይቶ መፈናፈኛ እንዳይኖረን አድርጓል። ይህ አልበቃ ብሎ፤
ወገኖቻችን በእነዚህ ቦታዎች ለባርነትና ለፈተና እንዲጋረጡ ተደርጓል፣ አማራጩ ያላቸው እንኳን ወደዚሁ እንደ
ዲባይ፣ ካታርና ቱርክ ወደ መሳሰሉት ወደጠላቶቻችን ግዛት እየተጓዙ ገነዘባቸውን ያስረክባሉ። ሸህ አላሙዲም
ከኢትዮጵያ ኃብት በኢትዮጵያውያን ላብ ያጠራቀሙትን የኢትዮጵያውያን ገንዘብ አሁን ሳዑዲና ሞሮኮ በነጻ ሊወስዱት
ነው። እስክ 20 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ እንዲጠረፉ በተደርጉባቸው በያዝናቸው ሳምንታት ውስጥ።
በቅርብ ቀን ዝርዝሩ በኢትዮጵያ አውታር ራድዮ ይዤላቹ እቀርባለው።
Blogger Comment
Facebook Comment