ወርቃማው ክቡር መስቀል ለመጀመሪያ ጊዜ በሳዑዲ አረቢያ ቤተ መንግሥት አበራ


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


የሊባኖስ ዓብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በትናንትናው ዕለት ሳዑዲ አረቢያን ሲጎበኙ ታላላቅ መስቀሎቻቸውን አጥልቀው ታይተዋል።
መስቀል፣ ማሕተብ እና መጽሐፍ ቅዱስ፤ ባጠቃላይ የክርስትና ምልክቶች ሁሉ ክልክል በሆኑባት ሳዑዲ አረቢያ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም በንጉሣውያኑ ቤተ መንግሥት ውስጥ መስቀልን ላጠለቁ የቤተክርስቲያን አባቶች አቀባበል የተደረገው። ሌላ ጊዜ/ሁልጊዜ ገና አውሮፕላን ማረፊያ ነበር መስቀሉና ማሕተቡን በጥሰው የሚጥሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስንም ቀዳዶ መጣል የተለመደ ነው።
ነገር ግን፤ በዚህ ያልተለመደ ተግባራቸው እነዚህን እባቦች በጭራሽ ማመን የለብንም። ለመስቀል ያላቸውን ጥልቅ ጥላቻ እናውቃለን።
አፄ ኃይለ ሥላሴ በዔሳውያን እና በእስማኤላውያኑ ተታለው ነበር የተገደሉት። ገዳያቸው ከሮበርት ጥጋቤ ጋር ነው ያለው። የሚገርም ነው፤ አፄ ኃይለ ሥላሴም ሆኑ ሮበርት ጥጋቤ ልክ እብቦቹ የባቢሎን ጠባቂዎቹ ሳዑዲዎች ባሁኑ ሰዓት በጥድፊያ በማድረግ ላይ ያሉትን ዓይነት ውስጣዊ ለውጥ ፈጥነው ማድረግ ነበረባቸው። ተሳሳቱ!
ሳዑዲዎች እውሩን የምዕራቡን ዓለም ለማታላል፤ እስልምናን እና አገራችንን ዘመናዊ እናደርጋለን በማለት አንዳንድ የፕላስቲክ ቀዶ ጥገናዎቹን በማድረግ ላይ ናቸው። 500ቢሊየን ዶላር የሚያወጣና ኒው ዮርክ ከተማን 33 እጥፍ የሚበልጥ አንጋፋ ከተማ ቀይ ባሕር አካባቢ እንገነባለን፤ ለሁሉም ክፍት የሆነ፡ ሁሉም ሃየማኖቶች የሚፈቀዱበት፣ ሴቶች ነፃ ሆነው የሚንቀሳቀሱበት ልዩና ዘመናዊ ከተማ ነው የምንሰራው አሉ። የዔሳውያኑንም አፍ አዘጉ፤ 500 ቢሊየን “ዶላር”፣ ኢንጂነሩ፣ ማናጀሩ ሁሉ ከእነዚህ ም ዕራባውያን አገራት ይመጣልና።
የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፯
፲፰ ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።
ባቢሎንን የሚሠሩት፤ ልክ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኤዶም ዔሳው የነበረበት ቦታ ላይ ነው(ደቡብ ዮርዳኖስ፣ ቀይ ባሕር ድረስ)። ሰሜን ምስራቅ አፍሪቃንም ለመተናኮል እንዲመቻቸው በግብጽ በኩል፡ ቀይ ባሕር ላይ ድልድይ እንሠራለን ብለዋል።
አንድ መጠየቅ ያለበት ነገር ግን፤ እዚያ ውሃ የሌለበት በረሃ ላይ ውሃ ከየት ለማግኘት አቅደው ይሆንአባይን፡ እዚያ ጭቃ ጭንቅላታቸው ውስጥ አስገብተውት ይሆን?
እስማኤላውያኑ ሳዑዲዎች የሌባኖስን ዓብያተ ክርስቲያናት መሪዎች አሁን መቀበላቸው ያለ ምክኒያት አይደለም። ከዔሳውያኑ ጋር በማበር ጥንታዊቷን ክርስትናን እና የቆዩትን ክርስቲያኖችን ከኢራቅ እና ከሶሪያ ምድር ሙሉ በሙሉ አጥፍተዋል። የሚቀጥለው ዘመቻቸው ወደ ሌባኖስ ግዛት፣ ከዚያም ወደ ግብጽ፤ በመጨረሻም ወደ ጥንታዊቷ ክርስቲያን ኢትዮጵያ ነው የሚሆነው። በዚህ አንጠራጠር።
እነዚህ የምዕራቡ ዔሳውያን እና እስማኤላውያኑ ታላቂቷን ባቢሎንን እንደሚገነቡ መጽሐፍ ቅዱስ ጠቁሞናል። ደህና፣ ይሥሩ፤ ይጨርሱት፣ ይሳካላቸውም ይሆናል፤ ግን ፣ ክርስቶስ ጌታችን፦ “ሞኝ/ሰንፍ ሰው አሸዋ ላይ ቤቱን ይሠራል[ማቴ ፯፥፪፮]ብሎ እንዳስተማረን፡ በኋላ ላይ ሁሉም መፍረሱ አይቀርም፤ ልክ ወደ ኢትዮጵያ በግልጽ መዝመት ሲጀምሩ፤ እግዚአብሔር ድምጥማጣቸውን ሁሉ ያጠፋልናል። በዚህም ሙሉ በሙሉ እተማመናለሁ!
የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፯
 ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ። ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤
 የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ።
 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።
 ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤
 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም። ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።
 ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment