ኢትዮጵያዊው የቅዱስ ሚካኤል ሥዕሎች በአሜሪካዋ ቦልቲሞር፣ ሜሪላንድ ዋልተርስ ቤተ መዘክር


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ


ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስን ከቤተ ክርስትያን ሲያስወጣ

ነጮች ጥቁር ወይም ኢትዮጵያዊነት ምንእንደሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በጥቁር ህዝቦችና በኢትዮጵያውያን ላይ ከፍጥረተ አለም ጀምሮ ሴራቸው በተለያየ መንገድ ሲፈጽሙበት ኖረዋል። መንፈሳዊ የበላይነቱ በመንጠቅ በሰይጣናዊ ኃይል የበላይ ለመሆን እስከ የዛሬው ዘመን ድረስ ደርሰዋል። በተደጋጋሚ በተለያዩ መንገዶች ለዘመናት በሰሩት የአእምሮ አጠባ ሰራ (brainwsh)  ጥቁር ህዝብ የነጮች አገልጋይና ተገዢ እንዲሁም የበታች እንደሆነ እንዲያስብ ተደርጓል። እውነታው ግን በተቅራኒው ነው።  ፈጣሪ የሰው ፍጡር በሥላሴ አምስል ሲፈጥር ሁሉም ፍጥረት በእኩል በማየት ነው።

የተለያዩ የህው ሰሌዳዎች ስፈልግ ያገኝሁት ቅዱሳን ስዕል ላካፍላቹ። መጀመርያ ግን ማለት የምፈልገው ነገር አለ። ነጮች የሴራቸው ብዛት በዚህ ጽሑፍ የሚጨረስ አይደለም። እኛም ነገሮች ባለመመርመር ነጭ የነገረን ነገር ሁሉ አሜን ብለን የመቀበል ከፍተኛ መሰረት የያዘ ችግር አለብን።

የአለም ፈጣሪና መጋቢ መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊ የሆነ መልክ እንዳለው መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን እውነት ነው። ሆኖም ነጮች (ኢሉሚናቲዎች) በበረዙት መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን እውነት እንዲደበቅ አድርገውታል። ኢትዮጵያዊ መልኩም በነጭ ቀለም አሳምረው በማቅረብ የክርስቶስ መልክ ይህ ነው ብለው አቀረቡልን እኛም ተቀብለን እየተጠቀምንበት ነው። ይህም የነጭ ስነ ልቦና በጥቁር ህዝብ ላይ የበላይ ለማድረግ ተጠቅመውበታል።

በተጨማሪም ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ  ከአሜሪካዋ ቦልቲሞር፣ ሜሪላንድ ዋልተርስ ቤተ መዘክር ያገኝህዋቸው የቅዱስ ሚካኤል ቅዱሳን ሥዕሎች ናቸው። በብዛት የምናውቀው የቅዱስ ሚካኤል ስዕል ቅዱስ ሚካኤል ነጭ ዲያብሎስ ጥቁር ተደርገው የተሰራው የነጮች የበላይነት የሚያንጸባርቅ ሥዕል ነው። ይህ ሥዕል ቅዱሳን አባቶቻችን ቢያዩት ምን ይሉ ይሆን ብየ እጠይቃለው ፧

ነጮች ኢትዮጵያዊነት ምን መሆኑ በሚገባ ያውቃሉ። ለዚምነው ትኩረታቸው ሁሌ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የሆነው። ተከታዮቹ ሥዕሎች ከአሜሪካዋ ቦልቲሞር፣ ሜሪላንድ ዋልተርስ ቤተ መዘክር ድህረ ገጽ የተገኙ ናቸው።

ቅዱስ ሚካኤል በተለያዩ ቅዱስ ስራዎች ተሰማርቶ ያሚያሳይ ከ ፬ መቶ አመታት በፊት በኢትዮጵያ የተሳሉ ቅዱሳን ሥዕሎች።ከዋናውየህዋ ሰሌዳ ሥዕሎች ለመመልከት ይህ አስፈንጣሪ ይጫኑ።

እነዚህ በብዙ ቀለማት ያሸበረቁና የሚያበሩ ፵፱ ሥዕሎች የወቅቱን የበለጸገ የሥነ ጥበብ ባህል ያንጸባርቃሉ። የእጅ ጽሑፉ በሊቀ መላእክት ሚካኤል ተአምራት እና ፵፱ ደማቅ ቀለም ባላቸው የእግዚአብሔርን ገጸ–ባህሪያት በሚያሳዩ ሥርዓት ትምህርቶች ላይ ያተኮረ እንዲሁም በቅዱስ ሚካኤል የተፈጸሙ ተዓምራቶችን አጣምሮ የያዘ ነው። የእጅ ጽሁፎቹ ክፍሎች እንደ ተለመደው በቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ የበዓል ቀናት ይነበቡ ነበር፤ እናም ሥዕሎቹ በምንባቡ ጎን አብረው ይቀርቡ ነበር።እነዚህ በድርሳነ ሚካኤል አነሳሽነት የተሠሩት ድንቅ ሥዕሎች የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ በአበበበት በ ፲፯ ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ነበር በጎንደር ከተማ የተሠሩት።

በተጨማሪም ሁሉም ሥዕሎች ላይ የሚታዩት መልአክትና ቅዱሳን የኢትዮጵያውያን ገጽታ እንዲኖራቸው ተደርገው ነበር የተሠሩት። ፈረንጁም በአገሩ ይህን ነው ከአድናቆት ጋር እያሳየ ያለው። ታዲያ ይህን የሚያዩ ሠዓሊያን ወገኖች፡ መልአክቱንና ቅዱሳኑን ሁሉ ፈረንጅ አስመስለው አሁን ሲስሉ እጅግ በጣም አያሳዝንምን፧ አያንገፈግፍምን፧ ምን ነክቷቸው ይሆን፧ በእውነት፡ አባቶቻችንን ምን ያህል ቢንቋቸው ነው፧ የሚያሰኝ ጉዳይ ነው።

ኢሉሚናቲ ለምን ጥቁር ህዝቦች ይጠላሉ ፧

የኢሉሚናቲ የደም ሓረግ የሜላኒን/ካርቦን ንጥረ ነገር እጥረት ያለበት ነው። ይህም የቆዳቸው ቀለም ነጭ (ብጫ) እንዲሆን አድርጎታል። ሜላኒን ጥቁር ህዝቦች የቆዳቸው ቀለም ጥቁር እንዲሆን የሚያደርግ ነው።የመጀመርያው ፍጡር አዳም ጥቁር ኢትዮጵያዊ ቀለም ነበረው። ይህ ታላቅ እውነታም ተፈጥሮ ራስዋ የምትመሰክረው ነው። መቼም ነጭ በሃገራችን ሲያይ መስገድ የሚቃጠው የአሁኑ ትውልድ ይህንን እውነት ብሎ ለመቀበል አይደፍርም ብተቃራኒው ያሾፋል። የሰው ልጅ ከአፈር እንደመሰራቱ ነጭ አፈር ታይቶም አይታወቅም።
የካርቦን ሜላኒን ንጥረ ነገር የህይወት መሰረት ነው። ያለ ካርቦን ህይወት ሊኖር አይችልም። ይህ ካርቦን ለመንፈሳዊ ህይወትም ወሳኝ ነው።

ሜላኒን=ካርቦን=መንፈሳዊ የበላይነት

ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ክብር ነው።




ኅዳር 11,2010 ዓመተ ምሕረት
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment