የኦሮሞና የአማራ የዘር ምንጭ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ የዘር ምንጭ አንድ ነው - አዳም


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


ፍቅሬ ቶሎሳ (ፕሮፌሰር) ጽፈው ያበረከትሉን "የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ" የተሰኝው መጽሓፍ የብዙ ሰዎች መወያያ እና መከራከርያ ከዛ አልፎም መሰዳደብያ መድረክ የፈጠረ ሆኗል።በዘረኝነትና ጎጠኝነት ለሚታመሰው የአሁኑ ትውልድ ይህ መጽሐፍ ለመረዳት እንደሚከብደውና የራሱ ታሪክ ባዕድ ሆኖ እንደሚታየው ምንም ጥርጥር የለዉም።እኔ እይታ መጽሐፉ ለመረዳት መንፈሳዊ ከፍታ ላይ በመውጣት  እውነታኛው ኢትዮጵያዊነት መረዳትና ማወቅ እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚጠይቅ ነው።

አስደናቂው ነገር መጽሐፉ በአሉታ መንገድ የሚተቹ ሰዎች ሙሉም ማለት በሚባል ደረጃ ምንም አይነት የሚጨበጥ ማስረጃና ማጣቀሻ ማቅረብ ማይችሉ ናቸው።ለመቃወም መነሻቸው በፖለቲካዊ ዘረኝነት የናወዘው ጭንቅላታቸው ተጠቅመው መቃወም ብቻ ነው።

ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ምዕራባውያን እንኳን የሚመሰኩርለት ኢትዮጵያ የአዳምና ሄዋን መፈጠርያ (መነሻ ) መሆንዋ የማያውቅ በራሱ ዜጋ ተጽፎ ሲቀርብለት ግን እውነትኝነቱ የሚጠራጠር ትውልድ ስለሆነ ብቻ የመጽሐፉ ይዘት ይቃወማል።ሉሲ የመጅመርያው የሰው ዘር ሙሉ የአጥንት ቅሪት (fossil) ናት ተብሎ በምዕራባውያን ሲነገረው አሜን ብሎ ሲቀበል አዳም ኢትዮኦጵያዊ ነው ሲባል ያሾፋል።ይቀልዳል።አየ ማንነትን አለማወቅ።


የሰው ልጅ  መሰረቱና ትውልዱ አንድ ሆኖ ሳለ የኦሮሞና የአማራ የዘር ግንድ አንድ ነው ሲባል ማጎረምረም የጤና ይሆን ኦሮሞው ወይ አማራ ከሌላ አለም የመጡ ፍጡሮች (aliens) ናቸው እንዴ? አረ ተው  ነገሮች በቅን ልቦና መመርመር ትተን ሁሉንም ነገር ተቃውመን አንዘልቀዉምና ልብ እናድርግ።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment