ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው ማንንም በአጉል ምክንያት ለመተቸት አይደለም።ነገሮችን በተለየ አቅጣጫ በማየት ለመግለጽ ነው።የሴቶች ተፈጥራዊ እኩልነት መቶ በመቶ የማምን ሰው ነኝ።ማለትም እግዚአብሔር የሰው ልጅን ወንድና ሴት አድርጎ ሲፍፈጥር የራሱ የሆነ ምንም ስ ህተት የሌለበት ምክንያት አለው።በተቃራኒው ዘመናዊነት ተገን አድርጎ የሰው ልጅ የፈጠረው ሰውኛ ሴቶች ከወንድ ጋር እኩል ናቸው የሚለው የምዕራባውያን አጥፊ ሃሳብ
(feminism) ግን ተቃዋሚ ነኝ።ምክንያቱም ሴትና ወንድ እኩል ተፈጥራዊ መብትና ክብር ቢኖራቸዉም አንደኛው ለሌላኛው አስፈላጊና ጎደሎን የሚሞላ ተፈጥሮ ያላቸው እንጂ እኩል እንዳልሆኑ ተፈጥሮው ራሱ በግልጽ ያለ ቃል የሚናገረው ነው።ታድያ ለምንድነው ሴቶች ከወንድ ጋር እኩል ናቸው የሚል አስተሳሰብ ( በተፈጥሮ እኩል መሆናቸው እውነት ቢሆንም የዚህ ሃሳብ አራማጆች የሚገልጹበት መንገድ ግን የተለየና ሌላ ተጬማሪ አላማ ያለው ነው) ማራመድ ያስፈለገው ፧ ይህንን ለመመለስ ነገሮች በተገቢና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ በማጥናት መልሱ ይገኛል።
የኛ የሴቶች ቡድን በሃገራችን ኢትዮጵያ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በተውጣጡ ፭ ሴቶች አባልነት ከአመታት በፊት የተመሰረተ ቡድን ነው።አላማዉም ሴቶችን የሚያጋጥምዋቸው ችግሮች መሠረት በማድረግ ችግሮች ለመፍታት ህዝቡ በተለያዩ መንገድ በማንቃት የችግሩ መፍት ሄ እንዲሆን የሚል ነው።ታድያ የኔ መነሻ ሓሳብ እዚ ላይ ይሆናል።ይህ ቡድን እውነት ችግሮች ለመፍታት አላማው መሆኑ ድንቅ ነው።የሚደገፍም ነው።ቡድኑ የሚንቀሳቀስበት ገንዘብ ከየት ያገኛል ፧ ከጀርባውስ የሚያስተባብረው ማነው የሚለው መመለስም ግድ ነው።
የቡድኑ የገንዘብ ምንጭ አውሮፓዊትዋ ሃገረ እንግሊዝ ናት።ታድያ ምን ችግር አለው የሚል ጥያቄ መቅረቡ ተገቢ ነው።በተገኝው ገንዘብ የሚሰሩ ሙዚቃዎችና የሬድዮ ድራማዎችና ውይይቶች የሚያስተላልፉት መልዕክትና ይዘት ለተገነዘበ ግን ሴራው ፍንትው ብሎ ይታየዋል።መግብያው ላይ እንደተገለጸው ሴቶች ከወንድ ጋር እኩል አይደሉም።እንዲሁም ወንዶች ከሴቶች ጋር እኩል አይደሉም።በሚያሰራጩት ድራማዎች ላይ በተደጋጋዊ ለመረዳት እንደቻልኩት የጾታ ልዩነትን በማጥፋትና በማጥበብ የሰነ ተዋልዶ ተፈጥራዊ ስርዓትን ለመቀየርና የተመሳሳይ ጾታ ግንኝነት እንዲለመድ ወይም ተገቢነት እንዲኖሮው በድግግሞሽ በማስተላለፍ (mind control) ተቀባይነት እንዲኖሮው የሚያደርግ ነው።አውሮፓውያን ህጻናት ልጆችን ከ አንደኛ ደረጃ የክፍል ደረጃ ቸው እኩልነት በሚል ሽፋን የተመሳሳይ ጾታ ግንኝነት እንዲለምዱት በትምህርት ስርዓታቸው ዕውቅና ተሰጥቶት ይሰራል።ይህም አሁን ለሚታየው የግብረሰዶማዊነት ተግባር መስፋፋት ከፍተኛው አስተዋጾ እያደረገ ነው።ታድያ ይህ አስተሳስብ እንዲሰፋፋ ነው የኛ የሴቶች ቡድን በሃገረ እንግሊዝ ድጋፍ እንዲንቀሳቀስ የሚደረገው።በእኩልነት ሰበብ የሚደረገው ይህ እኩይ ተግባር የኛዎ ቹ መገናኛ ቡዝ ሃንም አጨብጫቦዎችና አጫፋሪዎች ናቸው።ምዕራባውያን በጦርነት ያጡትን ድል ተለሳልሰው በመግባት አላማቸው እያስፈጸሙ ናቸው።
ይህንን ሁሉ እንድጽፍ መነሻ የሆነኝ ዛሬ ታህሣሥ 10,2009 ዓመተ ምህረት የአለም አቀፍ መረጃ አውታር (internet) ሳስስ ያገኝሁት ዜና ነው።ዜናው የሃገረ እንግሊዝ መንግሥት ለየኛ የሴቶች ቡድን 5.2 ሚልዮን ፓውንድ ድጋፍ ማድረጉ የሚል ነው።ዜናው ብዙ የሃገር እንግሊዝ ጋዜጦች ያሰራጭት ሲሆን የኛ የሴቶች ቡድንን ማጣፈጫ ሴቶች (Spice Girls)
በማለት ሲያደንቋቸው ሲሰይምዋቸው ዉለዋል።
የጋዜጣዎቹ ዜና ለማንበብ አስፈንጣሪዎቹ ይጫኑ
ሰኞ ታህሣሥ 10, 2009 ዓመተ ምህረት
መቐለ
Blogger Comment
Facebook Comment