ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፡ መልዕክት ሦስት ክፍል ፩


በምድሪቱ ሁሉ ላለህ የሰው ዘር በሙሉ



ተጻፈ በመጋቢት 19 ቀን 2001 .



ይህ መልዕክት የመጨረሻ የአፈጻጸም ውሳኔ ሲሆን የመጀመሪያውንና የሁለተኛውን መልዕክት ወደ አፈጻጸም የሚቀይር ውሳኔ ነው።


የፍጥረት ሁሉ ጌታ ስሙ ይክበር ይመስገን፣ በዓይናችን ከምናየው፣ከምድርና ፀሀይ በብዙ ትሪሉዮን ክብደት ስፋትና እርቀት የሚበልጡትን ከዋክብቶች የፈጠረ፣በሰማይ ላይ እንደማይቆጠር አሸዋ የበተነ፣ሁለን ቻይ
ፈጣሪ፣ በብዙ ሚሊዮን የሙቀት ዲግሪ ሴሌሺየስ የምትንቀለቀለውን ፀሀይ በአንድ ስፍራ አቁሞ ለምድርና
በውስጧም አልቆ ለፈጠረው ሰውና ፍጥረታት በሙሉ እንድታገለግል፣ብርሃንና ሙቀት እንድትለግስ ላደረገ
አምላክ ከብርሃን እጅግ በፈጠነ ሩጫ የሚከንፉትን በቅጽበትም ለሚሰወሩት በትልቅነታቸው ከፀሀይ በብዙ
ቢሊዮን የሚበልጡትን ከዋክብት ህልው ላደረገ፣አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ይክበር ይመስገንና፤
ይህን አምላክ በምን ልክ በምን ቋንቋ በምንስ የፍጥረት ብልሃት ትገልጹታላችሁ? ትመስሉታሊችሁ?
ጌታችን ፍጹምና ከሕሊናችን ዕሳቤና ግምት እጅግ የራቀ ነው። በምንም አንመስለውም ስንወደው፣ ስንታዘዘው፣
ስናመልከው ያኔ በቸርነቱ፣ በበረከቱ ፣በአባትነቱ ፣በርሕራሄው ፣በፍቅሩ፣ በቅን ፍርዱ እናውቃለን። ስንንቀው፣
ስንክደው፣ በእርሱ ምትክ ሌላ አምላክ ስናቆም የቁጣውን በትር የሚያሳርፍ ምንም አምሳያ የሌለው አምላክን
በምን ትገልጡታላችሁ? ከሰው ይልቅ እንስሶች በተሰጣቸው የደመ ነፍስ እይታ የተሰጣቸውን ስርዓተ ህይወትና አኗኗር ሳያዛንፉ ለሰው አገልግለው ያልፋሉ። ባጭሩም ሆነ በረዘመ ዘመናቸው ፈጣሪአቸውን ያመሰግናሉ ሰውስ? የከበረው የአዳም ዘርስ? እንደ ፍጥረት ልቀቱ ነውን? እንድናስተውል አዕምሮ ለሰጠን አምላክ ምስጋና ይገባዋል። ሰውን ለክብሩ ሊመሰገንበት በራሱ አምሳል እጅግ አልቆ የፈጠረ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ከዘለአለም እስከ ዘለዓለም ይክበር ይመስገን።
በአንድነቱ በሦስትነቱ የከበረ ጌታ የተመሰገነ ይሁን በማንኛውም ፍጥረት እሳቤና ህሊና የክብሩ፣የግዝፈቱ፣
የጥልቀቱ፣የብርሃን ምንጭነቱ የማይዳሰስ ጌታ ሁሉን ህልው የሚያደርግ፣ ሁሉን የሚያሳልፍ፣ማንም በማይቀርበው ብርሃን ላይ፣ማንም ሊያየው በማይቻለው የእሳት ፍምና ምንጭ ላይ ዙፋኑን የዘረጋ፣የገዘፉትንም ያነሱትንም የሚታዩትም የማይታዩትም ረቂቅ ፍጥረት ሁለ ቀደስ! ቅዱስ! ቅዱስ! እያሉ ሌት ከቀን በምስጋናቸው
የሚያረሰርሱት እንደ አርሞንኤም ጠል፣ሳያቋርጡ ምስጋናው ዘወትር የሚፈስለት ጌታ ይክበር ይመስገን አሜን።



የዳዊት መዝሙር 97(98)
የዳዊት መዝሙር 148
እኔም የሥላሴ ባርያ ! እጅግ ባደፈችው አንደበቴ፣ እጅግ በምታንሰው ሰውነቴ ደፍሬ አመሰግነዋለሁ። ቃሉን ትዕዛዙን ፣ፍርዱን፣ ተግሳፁን፣ቁጣውን ፣በረከቱን፣ ምህረቱን ለሰው ዘር በሙሉ ከሁሉ በሚያንሰው በእኔ ይነገር ዘንድ ፈቃዱ የሆነ አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን አሜን !
መዝ. 18(19)7-14
የዛሬው መልእክት አዲስ ትዕዛዝ አዲስ መልእክት የሚመነጭበት ሳይሆን ቀድመው በተገለጹት 1 እና 2
መልእክቶች እንደተገለፀው፣ በልዑል እንደተወሰነው እና እንዯታዘዘው እኔም ሳይጨመር ሳይቀነስ እንደገለጽኩላችሁ ሁለቱም መልእክቶች የሚወቅሱ፣ፍርዱን የሚገልፁ ናቸው። የሰራዊት ጌታ ፍርድ በመጻኢ
ህይወታችን ላይ ምን እንደሚመስል በየትኛው ተግባራችን ላይ እንደተመሰረተ ጠቅልሎ የሚገልጽና ፍርዱንም
የሚያሰማ ለንስሃም እድል የሚሰጥ ነው። የቅጣቱንም ሁኔታ የሚገልፅና ጅምሩንም በግልፅ እያሳየ ያለ
ቀጣይነቱንም የሚያሳይ ነው።



ታዲያ ይህ መልእክት ለምን ተጻፈ? የሚሌ ጥያቄ ሊኖር ይችላል። በእርግጥም ሊጠየቅ ይገባል። በአንደኛው
መልዕክትና በሁለተኛው መልዕክት የሰፈረው የጌታ ቅን ፍርድና ውሳኔ አፈጻጸሙን ጥልቀቱንም እናም
የሚመጣውን ውጤት የሚገልፅ በመሆኑ ይህ መልዕክት ደግሞ የተበተነውን ለመሰብሰብ፣ የተሰበሰበውን መልካም ፍሬ ለመሸከፍ ነው። በዚህ መልዕክት የሁለቱንም መልእክቶች አፈፃፀም በዝርዝር ለመግለፅና በመላው አለም ላሉ ህዝቦች ሁሉ፣ እንደየ አደረጃጀታቸው የተፈፃሚነቱን ዝርዝር እንዲያውቁ በቅጣቱም ሆነ በምህረቱ የተጎበኙ ሁሉ ሊያደርጉ ስለሚገባቸው ዝርዝር መመሪያና ማረፊያ መደምደሚያ ለማስቀመጥ የታሰበ ነው። በአምላኬም ይህንን እንዳደርግ የታዘዝኩ ስለሆነ ነው።



በዚህ መልእክት ለሁሉም መንግስቶች፣ ድርጅቶች ፣መንፈሳዊ ተቋሞች ቡድኖች፣ግለሰቦች ማህበሮች ፣ክፍለ
አህጉሮች፣ አገሮች በሁለቱም መልእክቶች ውስጥ ሲመዘኑ በልዑል ፊት ምን እንደሚመልሱ እንዲያውቁት
የሚያደርግ የሁለቱንም መልእክቶች ዝርዝር ማብራሪያና መመሪያ በመስጠት ዓለም ወዴት መጓዝ እንዳለበት
ከልዑል የታዘዘውን ለማሳወቅ ለሁለም የሰው ዘር ከእንግዱህ ከወዴት የመንፈሳዊንም ሆነ የስጋዊን አመራር
እንደሚያገኝ የሚያስረግጥ ይሆናል። ሁለም ልብ ይበል የቀደመው የዓለም ስርዓት ሁሉ ይሻራል።



የመዋቀሻው ዘመን አልፏል። አሁን በዓይናችሁ እንደምታዩት በጀሮአችሁ እንደምትሰሙት ዓለም በምጥ ጅማሮ
ውስጥ ናት። ስለሆነም ከእግዚአብሔር አገልጋዮችና ባሮች መንፈሳዊንም ሆነ ስጋዊውን አመራር እንደ ልዑል
ትዕዛዝና ፈቃድ መስጠት ግድ ነው። የኔም ሆነም የወንዴሞቼ ኃሊፊነት ግዳታም ነው። ጭንቁ እየበረታ ሲመጣ
በጎችን ማረጋጋት፣ ማፅናናት፣ማፅናት፣ወደ መልካሙ ስፍራ መምራት አለብንና!



ለመንጋው መሰማሪያ፣መመሰጊያ ፣መጠለያ ማሳየት ወደዚያም መምራት የእረኞች ግዳታ ነው። ከበጎች መቀላቀል
የማይገባቸው ፍየሎች ፣ተኩላዎች በፍርድ እንዴት እንደሚጠበቁ ማረፊያቸውንም ያውቁት ዘንድ የግድ ይላል።
ተግሳፅን ንቀው ትዕዛዙን አፍርሰው በአመፅ አድገው፣ በክፋት አርጅተው ለመልካሞቹ እንቅፋትና ጥፋት ሆነው
ሁሌም እንደማይቀጥል ዳኛው ልዑል በቃሉ መሰረት እንደሚፈርድባቸው ሊያውቁት ይገባል። ይህንን ኃሊፊነት
የተሸከሙ የበጎች እረኞች ከመንጋቸው ተኩላዎችን ማራቅና በጌታ ቅን ፍርድ ስፍራቸውን ማስያዝ ይገባቸዋል።
በአንድ ባሕርይ ሦስትነቱ ፍጹም የሆነ ልዑል የሰጠንን የእረኝነት ኃሊፊነት ልንወጣ በስሙ ለተጠራን ለታማንን
ሁሉ የውዴታ ግዳት ያለብን ነን በፍቃደ የምትገዙ ሁሉ።



የእግዚአብሔር ቃል ዘመንን ሁሉ ያውጃል ዓለምንም በየዘመኑ ያፀናል። በየዘመኑ ያሉት ትውልዶቹም ሁሉ በቃሉ ይፈርዳል፣ይምራል፣ይቀጣል፣ይገስፃል ወደ እውነት መሄጃውን መንገድ ያመለክታል። ለሰው ያለው ፍቅር መለኪያ የለውም የዚህ ሁሉ ዘመን ትዕግስቱ ለሰው ዘር ሁሉ ያለውን የፍቅር ርቀት ያሳያል። ሰውን ከጥፋቱ ለመመለስ ወደ መንግስቱ ወራሽነት በንስሃ እንዲመለሱ ለማድረግ ሁለም የሰው ዘር የሚያውቀውን ማንም ሊከፍለው የማይችለውን የኃጢአት እዳ በመክፈል በፍቅሩ ወደ መንግስቱ እንድንፈልስ አድርጓል።


5500 ዘመን የዘለቀ ትዕግስት፤ 2000 ዘመን የዘለቀ የምህረትና የፍቅር ጥበቃ፣ የአባትነት ተግሳፅና ምክር ማን

ያደርገዋል? ለመሆኑ ይህንን ጌታ በምን ልንመስለው እንችል ይሆን? በየዘመኑ በስሙ ያተማቸውን በቅዱስ
መንፈሱ ያነፃቸውንና የሞላቸውን ነቢያትን፣ ሐዋርያትን፣ እረኞችን፣ ባሕታውያንን፣ መነኮሳትን፣ ከጳጳስ እስከ
ዲያቆን ለአገልግሎት ታምነው በመውጣት ለሰው ዘር በሙሉ የመዳንን መንገድ ሲያሳዩ ወደ ፍቅሩ መንግስት
ሕዝብን ሲጠሩ፣ሲወቅሱ፣ ሲያስተምሩ ማን አስተዋለ? እኛ ሰዎች ደፋሮች ነን። ለዲያብሎስም የጥፋት ስራ
መማሪያ እና ከለላ ሆነናል። ለእውነት የመጡትን የጌታ እረኞች ምን አደረግናቸው ምንስ ከፈልናቸው። አዎ ሁለም የሚያውቀው ነው።አሰርናቸው አሳደድናቸው ፣ገደልናቸው ይህ የሚታይ፣የሚዳሰስ፣ የሚዘከር የጨለማ ስራችን ነው።



ሰው ሆይ አድምጥ በምድር ሊይ ከተበተነው ፍጥረት ሁሉ የምትበልጥ በማስተዋል፣ አስበህ በማደር፣ በማዋል
የምትኖር ክፉና በጎን የሚለይ፣ጥቅምና ጉዳትን የሚያውቅ አዕምሮ የተቸረህ፣ ሁለም ህይወት ያለው የምድር
ፍጥረት ከበታችህ እንዲገዙ ልዑል ያደረገልህ፣ በአምሳል ፈጥሮ፣ በክብር አልቆ፣ በደሙ ዋጅቶ፣ ለማንም
ያላደረገውን የፍቅር ፀጋውን ያለበሰህ፣ የሰው ዘር አድምጥ፤ በትዕቢት ተሞልተህ ለምን ትጠፋለህ? በከንቱ ለምን
ትጠረጋለህ? ለምንስ አጥፊህን ዲያብሎስን ትተማመናለህ? ለምንስ ወደ ጨለማው ትገሰግሳለህ? ስንቶች ሊወቅሱ ወደ እውነት ሊመልሱህ ተነሱ? አንተስ ምን ከፈልካቸው? እንዴትስ ሸኘሃቸው? ለየትኛው የእግዚአብሔር የታመነ አገልጋይ መልካም መለስክ? አንድም ምስክር የለህም፡፡ ሁለንም አሳደሃል ሁሉንም ገድለሃል፣ ሁሉንም አጥፍተሃል።



ለሚጠፋ ስልጣን ፣ክብር፣ለሃብትና ገንዘብ ስትል የጥፋት እጅህን አስረዝመሃል። ለመሆኑ በዓለም ላይ የነገሱ፣
የሰለጠኑ፣ በባለሃብትነት፣ በመሪነት፣ በጦር አዝማችነት ስማቸው ገኖ በሰዓቱና በጊዜው በተሰጣቸው ትንሽ
ዓመታት የዘላለም ስሌጣን፣ ሃብት፣ ጉልበት ያፀኑ እየመሰላቸው የሰው ዘር በሙሉ የእነሱ ባሪያና አገልጋይ እንደሆነ በመቁጠር በንቀትና በትዕቢት የተጓዙ በኋላም ሳያስቡት የጨለመባቸው ስንቶች ናቸው።
ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 32 በሙሉ ከትላንቶቹ የማይማሩ የዛሬዎቹ ከቀደሙት ጨካኞች ብሰው በእውቀታቸው፣በጦራቸው፣በሃብታቸው በገንዘባቸው ብዛትና በጦራቸው ታምነው ሰውን ለመግዛት በጭካኔ ለመንዳት ምን ያላደረጉት አለ። የዘመኑ አጥፊዎች በዲያብሎስ በመመራት በእሱ ፈቃድና ትዕዛዝ በመነዳት የሚተካከላቸው የሌለ ሆነዋል። በብልጠትም ፈጣሪን የሚያታልሉ አርገው ያስባለና።


ዘሬ በየአገሩ ያለ መሪ፣ ባለሃብት ነጋዴ፣ ባለኢንደስትሪ ፣የጦር አዛዥ፣ የፀጥታ ኃሊፊ ቀን እንደ ሰው ለብሶ

የሚንቀሳቀስ የሚሊዮን ከበሬታን ስፍራ ይዞ የሚያዝ፣ የሚናዝዜ፣ሲሆን ሌሊት ደግሞ ወደመኝታው በመሄዴና
ፈጣሪውን ከማመስገን ይልቅ ወደ ጠንቋይ፣ መፅሃፍ ገሊጭ፣ኮከብ ቆጣሪ፣ድቤ መቺ፣ጫት ቃሚ፣ ሼክ፣ደብተራ፣
ተብታቢ የአየር፣ የምድር፣ የውሃ፤ የጥፋት አጋንንት መላእክቶችን ሳቢ በማሰስ ደጅ ሲጠና ይውላል፡፡ ያድራል።
ሲጎነበስ ሲሰግድ ሲለምን ያመሻል። የሚያዙትንም ሳያቅማማ ይፈፅማል፡፡ ያስፈፅማል፡፡ የመረጃ ምንጮቹ፣
የስሌጣን ምሰሶዎቹ፣ የገንዘብ ሰብሳቢዎቹ፣ አድርጎ ስለሚቆጥራቸው፤ አድርግ የተባለውን ማናኛውንም የከፋ ስራ ይሰራል።



እነዚህ የጨለማ ሰራተኞች ከተገዙላቸው ለአጭር ጊዜ የሚያገለግል የእግዚአብሔርን መንገድ ሰው እንዳይከተል
በማድረግ ወደ ጥፋቱ ሲነዳ፤ በንስሃ ለንስሃ ሳይበቃ ፣ከፈጣሪ ሳይታረቅ በቁሙ ወደ ውርደት ቢሞትም ወደ ገሃነም የሚሰዱት ናቸው። እነሱ ለፍርድ እንደተጠበቁ ሁሉም ሰው የቅጣታቸው ተሳታፊ የዘላለም የጨለማ ወራሽ እንዲሆን ያደርጉታል። ዛሬ ተመቸኝ የምትል የዘመኑ ፈራጅ ፈሊጭ ቆራጭ አዴምጥ !



ዛሬ ብዙ እንዲውም ሁሉም መሪዎች ማየት ይቻላል የዲያብልስ ተገዥዎች ናቸው። ባለሃብቶች፣ ስለ እውነት
የሚያውቁ የኃይማኖት አባቶች፣ ከተራ ስፍራ እስከ ከፍታ ያለ ሃብት፣ ስሌጣን፤ ክብር ናፋቂዎችና በያዘት ላይም
አብዝቶ ለመጨመር የሚለፉ ሁሉ የዚሁ የጨለማ ገዥ ተገዥ ናቸው።
በእግዚአብሔር እንደተነገረው በቃሉ ተመስርቶ ከልዑል እስትንፋስ በእኔ በውዳቂው ባርያው የወጣው አንደኛ እና ሁለተኛ መልእክቶች እንደተገለፀው ማንም ልብ ያለው ያስተዋለው የለም። እናንተ የዘመናችን የጥፋት ሰዎች
ማድመጥ፣መመለስ፣መፀፀት በፍፁም አልዘራባችሁም። እንዲያውም ጊዜ ሲቸራቸው ወደከፋ ጥፋት ተሸጋግረዋል። በመጀመሪያው መልዕክት በህዳር 7/1998 . ተፅፎ ፍርዳቸውን እንዲያውቁ ተሰጣቸው በሁለተኛው መልዕክት በግንቦት 27/2000 . እንዱሁ ፍርዱንና የመጀመሪያውንም መልዕክት በማፅናት የመጨረሻ የፍርድ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ። ሊደርስ የሚችለውንም ጥፋት አመለከተ ማንም አልሰማም በተለይ መሪዎች የየአገሩ መሪዎች እነ አሜሪካ ፣ባቢልን፣ አውሮፓ ኤሽያ፣ሊቲን አሜሪካ ፣መካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ሁለም ሰሙ ናቁ ተሳለቁ። አይ የሰው ጥጋብ በስራው ዓለም ሲመፃደቅ።


የእምነት መሪዎች ቫቲካን ፣ምስራቅ ክልል ያሉ የቻይና፣የህንድ ጣዖት አምላኪዎች ፣ፕሮቴስታንቶች፣ ሙስሊሞች

ሌሎችም እምነቶች ሁሉም በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ ሰሙ አላደመጡም እንዲገባቸው በአለም መግባቢያ በሆነው ቋንቋቸው የሁለተኛው መልእክት በእንግልዝኛ ቀረበላቸው። በመልእክቱ እንደተመለከተው የኢኮኖሚ ቀውስ፣ የገንዘብ ቀውስ፣ የከፋ ሪሴሽን፣ የበጀት ጉድለት፣ ግጭት፣ ጦርነት፣የመሬት መንቀጥቀጥ፣ማዕበል እሳት ሁሉም የከፋው እርምጃ መዘጋጀታቸውን እያሳዩአችሁ ቢሆንም አልሰማችሁም ታዲያ እነዚህ መች ይሰማሉ? አመፀኞች ማንን ፈርተው የፈጣሪን ቁጣ ሊቆጣጠሩት ዕቅድ ፕላን ይነድፋሉ። ስብሰባ በስብሰባ ያደራጃሉ ግን ምንም የፈየዳት የለም፡፡ እየተከሰቱ ያሉት ምልክቶች እርምጃዎች የመልዕክቶችን አይቀሬነትና እርግጠኝነት ከልዑል ለመውጣታቸው የሚያረጋግጥ ሲሆን አመፀኞች ሁሉ እንደሚጠረጉ ግልፅ ሆኗል። እኔም ምንም የተናቀ ህይወት ብመራም ብተችም በልዑልም ታዝዤ የአገልጋይነት ስራየን ለመወጣት የምተጋ፤ እንደሌላው ከአለም የምሻው የለም። ስለ ስሜ እንኳን መግለፅ አልፈለግሁም። ምክንያቱም እኔ ታዛዥ መልዕክት አድራሽ እንጂ ሌላ ምንም እንዳልፈለግሁ ሰው ሁሉ ሊረዳና ወደ ፈጣሪው መልእክት እንዲያተኩር ስለፈለግሁም ነው።
ዜና መዋዕሌ ቀዲማዊ 1621-23 ከፈጣሪየም የተማርኩት ትምክህትን አርቆ ትህትናን መልበስን መልካም ስለሆነ ነው እንጂ ለነገርም ሊታሰብ የማይችል ስጦታውን ጌታ ለእኔ ለትንሹ ባርያው ሰጥቷአል።ትምክህት ከጨለማ ስለሆነ በመመካት አልናገርም መግለፅ ግድ ካልሆነብኝ በቀር። የሰው ዘር አድምጥ መሪዎችህ ገዥዎችህ በከፍታ ላይ አቁመህ የምታያቸው የምትንቀጠቀጥላቸው ጣዖቶችህ ክቡር እከሌ፣አዋቂው ፣ባለሙያው ፣ሊቃውንቱ ፣የጦር ባለሙያው፣ኢኮኖሚስቱ፣ ባለሃብቱ፣ቢሊኒየሩ፣ኢንደስትርያሊስቱ፣ የህክምና ጠበብቱ ፣መሃንዲሱ፣ የአየር ንብረት አዋቂው፣ የጦር አለቃው፣ ተመራማሪው ፣የፖለቲካ ሳይንቲስቱ፣ ኧረ ምኑ ተቆጥሮ የሊቁ፣ የአባይ ጠንቋዩ ፣የጦር ኤክስፐርት ወዘተ እኒህ ሁሉ ምን ፈየዱ? ምንስ ለወጡ? ምንስ አመጡልህ? በየአገሩ ህዝባቸውን በመግዛት፣ በማስጨነቅ ወደ ጥፋት በመንዳት ላይ ያሉ ከመንደር እስከ አገር፣ ክፍለ አህጉር የተኮለኮሉ ገዥዎች መቼ ጊዜ ለፈጣሪ ትዕዛዝ ጀሮ ሲሰጡ ታየ? የእነሱ ጥፋት ምድርን ሸፍኖ ሰማይን አዳርሷል። የዘመኑን ፊደል ቆጠሩ ሁሉን አዋቂ ሆኑ ሰርቆ፣ ነጥቆ ገሎ፣ አመንዜሮ፣ ዋሽቶ አታሎ በየትኛውም ቀን ተሰማርቶ ገንዘብን ሰብስቦ ህዝብን አስጨንቆ መኖሩ ህልማቸውና ደስታቸው ከሆነ ዘመናት አለፈም ተቆጠሩም። በወቀሳ ፣በማስተማር በመገሰፅ በመለስተኛ ቅጣት መፍታት ቢቻል ኖሮ 7500 ዘመን ሙሉ ጌታ ያለመታከት በትዕግስት ሸፍኖታል። የሚያዳምጥ ጠፋ እንጂ !



ጊዜን በሰጡ ፣ምክርን በለገሱ የጥፋትንም ስፋት ባሳወቁ ፍርዱንና ፍፃሜውን በገለፁት ሁለት የጌታ መልእክቶች
ማን ተጠቀመ። መጭውን አስከፊ ጠረጋና የከፋ አደጋ ለሰው ሁለ በመግለፅ በኩል በሃገሬ ብዙ ባሕታውያን
መመህራን ከጌታ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ በመቀበል ለማዳረስ ጥረዋል እስከ ህይወት ዋጋም ከፍለዋል። ግን ማን
አስተዋለ? ማንም ተሳለቀ እንጂ በእኔ በባርያው የአስተላለፈውን የፍጻሜ መልእክት ማንን አስደነገጠ ? በተለይ በትዕቢት በማን አለብኝነት በአውቃለሁ ባይነት የተወጠሩ የየአገሩ መሪዎች መቼስ ደነገጡ ?


በህዳር 7/1998 እና ግንቦት 27 /2000 የተገለጹት መልእክቶች በሕዝብም በመሪዎችም በተለያየ ባህል፣ እምነት፣ የአገዛዝ ስርዓት ውስጥ ያለ ሁሉ እንዴት ተመለከቱት እንዴትስ አስተናገደት እንየው አራት አይነት ሰዎች ተከስተዋል። ከእነዙህ ከአራቱ አይነቶች የሚዘል አልነበረም አይኖርምም ይህንን በዝርዝር መግለጫ ውስጥ የምታዩት ይሆናል።

ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 7 27-28
የአዳም ልጅ እንግዲህ ገላጋይ ወደሌለበት ወደ ብርቱ የቅጣት መእበል እየተንደረደርክ ነው። ፍጠን አምልጥ፣
ተባልክ ተነገርክ፣ተመከርክ ተዘከርክ፣ ትዕቢትህ የበዛ ነውና መልሰህ ንቀት ትችት በመልእክቱ ከመጠቀም ይልቅ
ስለ መልእክቱ አድርሻ ማንነት ለማወቅ ደከምክ አይ የሰው ልጅ ምክንያትህ ምክንያትን እየወለደ ፣ሰበብህ
ሰብብን እየፈጠረ ልትጠቀምበት ይገባህ የነበረውን ቀናቶችና ወራቶች በከንቱ አሳለፈክ። ጥቂቶች ግን ተጠቀሙበት ወደ ፈጣሪያቸው ጉያ ገቡ ተሸሸጉ። ቅጥራቸውን አጠበቁ አንተስ? በምን ላይ አረፍክ ? አዝናለሁ ጊዛህ አበቃ!


የተከፈተው በር ተዘጋ ! ተከረቸመ ዛሬ በአለም ላይ የሚታየው የቀውስ አይነት ፣የተፈጠሮ አደጋ ብዛት የሕዝብ

ግጭት የአገሮች አለመስማማት የታላላቅ መንግስታቶች ወደ አዘቅት የመውደቅና የመጥፋት ጉዞ ጀምሮ 2000
. ማለቂያ ከነኀሴ መጨረሻ ላይ ከዋናው አምላካችሁና ጣዖታችሁ ከአሜሪካ(ባቢልን) በገንዘብ ቀውስ የጀመረ ሲሆን አድማሱን በማስፋት የኢኮኖሚ መቅለጥ ፣የኢኮኖሚ ቀውስ ወደ ማህበራዊ ቀውስ እየዘለቀ ይገኛል



ተስማምቶ የሚፈታ ታቅዶና ተተልሞ የሚተገበር ነገር ከእንግዱህ የማይታይበት ወደ ጨለማ መገስገስ
ተጀምሯል። ሁለንም አዳርሰዋል ይቀጥላል በብርቱም ይከፋል። በመልእክት ቁጥር 2 እንደተገለፀው (በእንግሉዝኛው) የእስትንፋስ ጊዛ አይሰጥም የኢኮኖሚ ቀውስ ፣የገንዘብ ቀውስ፣የኢንደስትሪ ቀወስ፣ስራ ፈቱ በአጠቃላይ በሁለም ዘርፍ ያለ ቀውስ በከፋ ሁኔታ ይጨምራል። መፍትሄም አጥታችሁ በልዑል ፊት እስክትወድቁና እስክትንበረከኩ ድረስ። የልዑል ቃል ወጣ አይመለስም እንደ ቃለ ያደርጋል እንጂ በከፍታ ላይ ያለ መንግስታቶች በሰበሰቡት ገንዘብ ፣ወርቅ፣ ታንክ፣ ጀት፣ኒውክሊየር፤የኢንደስትሪ ብዛት፣ የህንጻ ውበት የጀትና የባቡር የመርከብ ግዝፈትና ርቀት በየቀኑ የሚዘቅጠው ነዲጅ( ዘይት) በማዳበሪያ በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ በፈጠሩት የእህል ዘር የሚመኩበት ደሃን በምጽዋት ደልለው የሚገዙበት ዕቅዳቸው የጨለማ አገዛዛቸውን የጥፋት የምንዝርና የግድያ ህጋቸውን የሚጭኑበት አካሄዴ የሚቀጥል መስሎቸው አምነውበትም
ነበር።
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ 24 በሙሉ



በዲያብሎስም ፍፁም ታምነው ነበር ዛሬ ወደ ቁልቁለት ጉዝ ጀምረው ከዚህ ገዥአቸው እጅ አልወጡም
አይወጡም ፍርዳቸው ወጥቷአል። ተግባሩን ጀምሯል። ዛሬ የሚታየው የምጥ ጅማሮ ለውጊያው በማጥፋቱ
የታዘዙት ቅዱሳን መላእክት በመጨረሻው ርምጃ ጠቋሚ የሆነውን የሚያመለክት የልምምድ እርምጃ እያሳዩ ነው።


መቼ ጀመሩ መጪውን የግዳጅ አፈፃፀም ልታየው ነው። ገንዘብ የኃጢአት ስር ነው። ገንዘብ ደግሞ የዲያብሎስ

መጠቀሚያ ነው በመልእክት 2 እንደተገለፀው። ታዲያ ይኸው የዘመኑ ባለጠጎች መሪዎች በልፅገናል ባይ አገሮች
ዋና መታመኛቸው ይኸው በቁጥር ለመግለፅ የሚያታክት ገንዘባቸውና ወርቃቸው ነው። የእርምጃው ጅማሮ ደም ስራችን ነው በሚሉት ገንዘብ ላይ በትሩን በማሳረፍ ተጀምሯል ከእጃቸው እንደ ሰም ይቀልጣል እየቀለጠም
ይገኛል። ስለ ትርፍ ብቻ እንጅ ስለ መክሰር ሰምተው የማያውቁ በአሜሪካ፣በአውሮፓ ፣በእስያ፣ በሊቲን አሜሪካ በአፍሪካ ያለ ታላላቅ ባንኮች ኢንሹራንሶች እየተመቱ ናቸው። በአለም ያለው ቀውስ ምን ይመስላል በዚህ ቀውስ የጉዳቱ መጠን እንዴት ነው? በጥቅል በገንዘብ ቀውስ እንደምንሰማው በአጭር ወራቶች ውስጥ ባንኮች ከሦስት ትሪሉዮን በላይ በአውሮፓና በአሜሪካ ያለት ብቻ አጥተዋል። ይህ አሃዜ የኢንሹራንሶችን ክስረት ሳይጨምር ነው።



የሞርጌጅ ባንኮች ከመደበኛ ባንኮች በሚቀራረብ መጠን ከስረዋል። አረቦች ሁለት ተኩል ትሪሉዮን አጥተዋል።
ይህ ሂደት ገና አሌተገታም አይገታም። የኢኮኖሚ ቀውሱ መጠኑንና አዴማሱን በማስፋት ሁለም የምድር ብርቱ
ነን መንግስታቶች እስኪከስሙ ይቀጥላል።



ትንቢተ ኢሳያስ 459-10
ዛሬ ይህን አደጋ ለማጥፋት ምን ዕቅድ ተነደፈ ምንስ እየተዯረገ ነው ብንል ከመንግስት ካዝና ያለውን ከሕዝብ
የተሰበሰበውን ፌደራል የገንዘብ ክምችት ላይ በመቀነስ መደጎምን ተያይዘውታልሌ። አሜሪካ/ባቢልን/ በቡሽ ዘመን 700 ቢሉዮን
>> >> በኦባማ ዘመን 879 >>
እንግሉዜ /ትንሿ ባቢልን/ 90 >>
ሲንጋፖር 13.3 >>
ጀርመን 470 >>
ቻይና 570 >>
ፈረንሳይ 18 >>
ራሺያ 28 >>
/ኮርያ 30 >>
አውስትራሊያ 14 >>
ካናዳ መጠኑ ያልታወቀ
ስፔን መጠኑ ያልታወቀ
ሌሎችም እንዲሁ 2 እስከ 10 ቢሉዮን ከማእከላዊ ባንካቸው ፌደራል ሪዘርቭ በማውጣት ደጉመዋል(ቤል አውት )አድርገዋል። በድጎማ በእቅድ በምኞት የሚቆሙ መስሎአቸው ይደክማሉ። ከንቱዎች በመልእክት 1 ሆነ 2 እንደተገለፀው ሕልማቸው እቅዳቸው ሁሉ ቅዠት ይሆናል እንጂ የሚለውጠው ነገር የለም። ሞርጌጅ ባንኮች መሸቃቀጫ ገቢያዎች የሚባሉት ሁሉ በታላቅ ክስረት እየተመቱ ሲሆን ከመንግስት ካዝና የድረሱልኝ ድጋፍና ድጎማ እየተደረገላቸው ነው። ሆኖም አስር ቦታ እንደተበሳ እንስራ ውሃ በአናቱ ሲገባ ከስር እንደሚያንዠቀዥቀው ተመልሰው እና መላልሰው በማፍሰስና በመውደቅ ላይ ይገኛሉ። ታላላቅ የመኪና የኤሌክትሮሊክስ የሸቀጥ ኢንዱስቱሪዎቻቸው በመክሰር ሰራተኞቻቸውን በማባረር ላይ ይገኛሉ። በታንክና በጠመንጃ የማይፈቱት አደጋንና ጅምር እንጂ መቼ ወደ ካፋው ደርሷል። የእኛ ብልሆች የኋለኛይቱ ዝንጀሮ በፊተኛዋ ትስቃለች ይባላል። እሱ ነው እሱ ነው ይባባላሉ።



ከንቱዎች ከንቱ የሚያደርጋቸውን እርምጃ ጀመሩ እንጂ ገና መቼ ወደ ከፋ ፍጥነት ገቡ ሲፈጥን ያኔ ሲፈጭህ
ታየዋለህ። እስትንፋስህ ሲዘጋ ቱልቱላህ ሁሉ ይቆማል። ኖኅ መርከብን አዘጋጀ እንደታዘዘው ለዘርና ለምህረት የታሰቡትን ሰበሰበ እሱም ቤተሰቡም ተጠቃሎ ወደ መዳኛው በእግዚአብሔር እጅ ተጠለሉ።



ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ 89-10
ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 7 13-16
ጌታ ከውጭ መርከቡን ዘጋው። የጥፋቱም እርምጃ ተጀመረ።ተጀምሮም አልቀረም የሚጠርገውን ጠራርጎ
ተፈፀመ። ዛሬስ አመንዛሪዎች የጣዖታችሁ የባቢሎን/አሜሪካ/የአውሮፓ የኤሽያ፣የመካከለኛው ምስራቅ
መታመኛችሁ ግንቡ መሰንጠቅ ጀምሯል።አይነካንም ብላችሁ የተመካችሁበት የሃብት ክምችት ምንጫችሁ
መንጠፍ ጀምሯል።



በኖኅ ዘመን ዝናቡ ሲጥል ቀስ በቀስ የውሃው ሙሌት ምድርን መሸፈን ሲጀምር ሁሉ የአዳም ዘር ይደንሳል፣
ይስቃል፣ ይሣለቃል፣ለነገው ዕቅድ ያወጣል፤እንደደነሰ እንደዘለለ እንደ ፎከረ በኖኅ መርከብና በውስጧ በተጣሉ
በንቀትና በምናምንቴነት እንደተሳለቀ ዛሬ በእኔና በመሰሎቼ እንደምታደርጉት ከእግሩና ጥፍሩ ስር የነበረው ውሃ
ወደ ጉልበቱ ወደ ወገቡ ሲደርስ አሁንም አልተመለሰም ያላግጣል።ደረቱ ላይ ሲደርስ ግን መደንገጥ፣ ጥርስ
ማፋጨት፣ መወራጨት ይጀምራል ምን ዋጋ አለው ውሃው ስራውን አላቆመም አንገቱ ጋር ደረሰ
በስተመጨረሻም እስትንፋሱን ዘጋ። ይህ ነው የዘመናችን አመፀኞች ዕጣ።


ይህ በእግዚአብሔር ቃል የተገለፀ የትላንት ክስተት ለእናንተ ሇዚሬዎቹ 70 እጥፍ ይጨምራል። የኖኅ ዘመን

ሰዎችን በሞት ለምትልቁት ሲነገራችህ መቼ ደነገጣችሁና።



አንደንድ ከአውሮፓና ከሌልችም አገሮች ራሳቸውን ማጥፋት ጀምረዋል ገና በስፋት ይቀጥላል። ሁሌ ሃብት
ማጋበስ፣ሁሌ ትርፍ፣ሁሌ ዲንስ፣ ቀንም ሌትም ያለ እረፍት ለስልጣን፣ለገንዘብ ሩጫ የትም የሚታይ የትልቅነት
ምልክት ነበረ። አሁን ግን ትርፍና ሁሌ በድሃ መቃብር ላይ ማደግና መበልፀግ የለምና!



ከበርቴና ባለስልጣን ድንገት ኪሳራ፣ ሞት፣ በሽታ፣ አደጋ ሲከታተልበት አዕምሮው ስለማይሸከም ሞትን
ይመርጣል። አሁን አልፎ አልፎ የሚታዩ ጠፊዎች ይህችን ዓለም መሰናበታቸው የክብር ሞትን እንደሞቱ
ይቆጠራል። ገና ሞት ይፈለጋል። ራሱን ይሸሽጋል ይህ መጪው ዕጣ ፋንታችሁ ነው። በአንደኛው መልዕክት 7/3/1998. በዝርዝር እንደተገለፀው ተፈፃሚ እንደሚሆን ልትጠራጠሩ አይገባም።
ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 7 በሙለ
በሁለተኛው መልዕክት በአማርኛ እንደተገለፀው
በሁለተኛው መልዕክት በእንግሊዘኛ እንደተገለፀው
በድጋሚ የመጨረሻ ጊዜ እንደተረጋገጠው ጊዜው መሟጠጡን እንዲበሰረው ሰምታችሁ መቼ ተፀፀታችሁ።
በብዙዎች ህሉና ውስጥ እየተመላለሰና እያሰናከለ ያለው ምንዴን ነው? ለምንስ ማስታዋል ጠፋ? ብንል እርቀን ሳንሄዴ መልሱ ቅርብ ነው።


1 እውነትን የሚፈለግ የህሊናና የልብ ውሳኔ ማጣት

2 እውነትን የሚፈለግ ሁለተኛ እምነታችንን መምሰልን እንጂ መሆንን ስላልተላበሰ።
3 አምልኮታችን ጌታ እንደተናገረው በእውነትና በመንፈስ ለማምለክ አለመወሰንና አለመፍቀዳችን።
4 አስቀድማችሁ ፅድቁን ፈልጉ ሌላው ሁሉ ይጨመርላችኋል የሚለውን የልዑል ቃል በዲያብልስ ፈቃድ
በመመራት ገልብጠን አስቀድመን የስጋውን ከዚያ በኋላ ስለ እምነት እንደትርፍ ጉዳይ ማሰባችን።
5 ይህን የተጣመመ አካሄዳችንን የጠፋ መንገዳችንን ለማስተካከል ጌታ ባሮቹንና አገልጋዮቹን እየላከ ሲወቅስ
ሲገስፅ አለመስማታችን ብቻ አይደለም መልዕክተኞቹን ማሳደድ፣ማሰር፣መግደልችን።
6 በተሰጠን ህሊና የፈጣሪያችንን ፈቃድ ከመፈፀም ይልቅ ዕውቀት ሲበዛ የቁሳቁስ ፍላጏታችን ሲትረፈረፍ፣ገደብ የሌለው የስጋ ፍላጎታችን ገንፍሎ በስስት፣በገንዘብ ማከማቸት፣በንፉግነት፣በጭካኔና በተገኘው ስጋዊ ምቾት መታበይ በፈጠሪ ሕግ ማሾፍን እንደ እውቀት በመቁጠር ሰማይ የደረሰ ትዕቢት ተላበስን፣ፈጣሪንም ናቅን ካድን የራሳችን አምላክ አቆምን እውቀትና ገንዘብ ጠመንጃ ትዕቢትን ተካን !



በመልዕክት 1 እንደተጠቀሰው ገንዘብ አምላክ ሆነ፣ሥልጣን ዕውቀት መታበያ ሆኑ የሁሉም ሰው ምኞት ተምሮ
ገንዘብ አፍሶ፣ተሽከርካሪ ሸምቶ ፣ቤት ሰርቶ ፣በድሃው ወንድሙ ላይ ተመፃድቆ ፣ከሆነለትም በደሃው ላይ የሥልጣንና የክብር መንበሩን ዘርግቶ በደሃው ዕድል ፈንታ ላይ ወስኖ መኖር የሚያረካውና የሥጋ ምኞቱ ሆነ። ሁሉም ሰው የሚጋልብበት ጎዳና የዲያብሎስ ጎዳና ይኸው እንዳልኩት ከብዙ በጥቂቱ የብዙዎችን ህሊና ሰቅዞ የያዘው አለማስታወል ከላይ በተጠቀሱት ነጥቦች የሚገለፅ ነው።
ኦሪት ዘሌዋውያን 18 1 - 5
በእነዚህ ሃሳብ የተጠመደ ሰው የዲያብሎስ ፈቃድና ሃሳብ ፈፃሚ ከፈጣሪው ፈቃድ ተጋጭ ሆኖ ይቀራል።
ሰው ሲወቀስ ሲገሰፅ ካልሰማ ሲጠፋ ቢሰማ ምን ዋጋ አለው? ሰው በፍርድ ሂደት ክርክር ውስጥ ሲገባ ከውሳኔው በፊት ነው የመፀፀቻ ዕድሎቹ ሁሉ ያሉት ከውሳኔ በኋላ ውሳኔው ወደ ማስፈፀም የሚሄዱት ሃይሎች እንደስማቸው የማይፀፀቱ የአቤቱታ የይቅርታ ጥያቄ አድማጮች አይደለም። ማስፈፀም ብቻ ነው ስራቸው። ተልዕኮአቸውም ይኸው ነው መፀፀትም መመለስም፣ንስሃ መግባትም ከውሳኔው መስጠት በፊት ነው። ዛሬ በተከታታይ እየተወቀሰ አልሰማ ያለ የሰው ዘር ውሳኔው ሲተገበር ቢጮህ ምን ፋይዳ አለው። መልዕክቶቹ የደረሷቸው ሁሉ ከፊሉ ይህ ሰው ከወዴትስ የበቀለ ነው? ማነው? ምን አገባው? ምን ስልጣን አለው? ማን ሾመው? በየትኛው ጉልበቱና ኃይሉ ነው? የአዕምሮ በሽተኛ ነው ቅዠታም ነው ወዘተ... እያሉ ባያውቁኝም
ሲያብጠለጥሉኝ ይውላሉ። ያድራሉ። ስለ እኔ ማንነት ከሚቸገሩ ይልቅ የመልዕክቱን ሃሳብ ብቻ ተረድተው
ቢጠቀሙበት ምንኛ ባተረፉ ነበር። ከንቱዎች በከንቱ ሃሳባቸው ይደናቆራሉ። ይሁንና እኔ በሁለቱም መልዕክቶች
ለመግለፅ ሞክሬአለሁ ደግሜም የምናገረው ይህንኑ ነው። ድሃ ነኝ እውቀት የለኝም ከሁሉ በሚያንስ ኑሮ ውስጥ
እኖራለሁ። በማንም ዘንድ ግምት የሚሰጠው የሃብትና የእውቀት ስብዕና የለኝም ራሴንም አልሰየምኩም የፈጠረኝ አምላክ እንጂ የሾመኝ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው ስልጣኔን ወደፊት ፈጣሪ ሲገልፅላችሁ ታውቃላችሁ ጉልበቴና ኃይሌ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እሳት ነው። ፀጋው ሽፋንና ከለላዬ ነው። ብዙዎች ከምንግስት እስከ በታች ሹም ወይም ከአለቃ እስከ ምንዝር እኔን ሊያጠፋ ያልወደዱ የሉም። ዛሬም ነጋም ጠባም በእኔ ጉዳይ ትልቅ ስምሪት፣ዕቅድ፣ብልሃት፣ማጥቃት፣ማጥፋት ለመፈፀም ለማስፈፀም ይወጣሉ ይወርዳሉ። ግን በመልዕክት 2 እንደገለፅኩት ከእነሱ የሚበልጠው እነሱን በሚከታተለው በሚያጠፋው የልዑል ኃይል የምጠበቅ ነኝና ምንም ሊሆን አይችልም። ክፉን አላሰብኩም እንዳስብም ፈጣሪዬ አላስተማረኝም።



ትንቢተ ሕዝቅኤሌ 12 1 – 3
ከአለቃ እስከ ምንዝር በእኔ ላይ በጓደኞቼ ላይ የጥፋት ሥራ ሲሰሩ ሲያስቡ፣በከፍተኛ ወጪ ሲሰልሉ በስጋ
ጥበባቸው ብዙ ሉያደርጉ በያዙት ጠምንጃ ሲመኩ ምንም ያልኳቸው ነገር የለም፣ታገስኳቸው እንጂ። ምክር
ተግሳፅ ከመሰንዘር በስተቀር ከዚያ አልዘለልኩም ፈጣሪን ብጠይቅ ፍፁም በእሳት እንደሚበሉ ነግሬአቸዋለሁ።
ዛሬም ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ ብጠይቅ ተፈፃሚ ነው። በጠረጴዛቸው ላይ ስለ እኔ የሚቀርበው ሪፓርት ዝርዝር አውቃለሁ። ትምክህት ግን ምን ያደርጋል። አዝንላቸዋለሁ። መልዕክቱ ደርሷቸው ምን እንዳሉ ምን እንደወሰኑ ሁሉ በግሌ የሚታወቅ ነው። በንቀትም እንደተሳለቁበት እረዳለሁ።



ይሁንና ሳይርቅ ሁሉም ስለሚፈፀም እርምጃቸውን ሁሉ ደግመው ደጋግመው ቢያዩት ለራሳቸው የሚበጅ በሆነ
ነበር። ሆኖም በራሳቸው የስጋ ሩጫ ስለሚያልሙ ከውድቀታቸው አይመለሱም ይበጀናል ብለው የሚወጥኑት ሁሉ ወደ ከፋ ጨለማ እያወረዳቸው ይገኛል። አሁንም ቢይዙት ሰከንድ ለማትፈጅ እስትንፋሳቸው ይመጻደቃሉ።
የመንፈሳዊን ሰው አይን ንቀው በስጋቸው አይን ሊሰልሉት ይደክማሉ። እስከ ቤቴ ገብተው እንዲሰልሉ
ፈቅጄላቸዋለሁ ከተጠቀሙበት። እውር አይናማውን ሲሰልለው እስቲ አስቡት! አለም በምን ምጥ ውስጥ እንዳለ ወዴትስ እንደሚጓዝ በፊታቸው ያለው የልዑል መልዕክት ሲለካቸው ሲመዝናቸው ለፍርድ ሲያዘጋጃቸው በማይታይ የእግዚአብሔር የብርሃን ሰንሰለት ሲጠፍራቸው አያውቁትም አይረዱትም በህሊና በስጋ ዕውቀታቸው ዲያብሎስ በሰጣቸው የውሸት ተስፋ ሲመፃደቁ የተሳካላቸው እየመሰላቸው ሲያከትሙ አይናማው ያያል።እነሱ ግን እንደ ዕውሩ ወደ ገደል ይወድቃሉ። ለምን አያስተውሉምና በትዕቢት ተሞልተው አያዩምና።
ወደ መንደርደሪያ እንግባና ስለዚህ መልዕክት ያላችሁን ግንዛቤ መንገድ ለማስያዝ፣ በመልዕክት አንድና ሁለት የታዘዘውን እየተፈፀመ ያለውንና የሚፈፀመውን ትረዱና ታስተውሉ ዘንድ ይህ መልዕክት የተፃፈ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ተፈፃሚነቱን ብቻ ሳይሆን ዝርዝር መመሪያውን የሚገልጽ ይሆናል።

 ትንቢተ ሕዝቅኤሌ ምዕራፍ 8 በሙሉ

በሦስተኛ ደረጃ እያንዳንዱ የአለም ክፍል ሀገር፣ /አህጉር ሕዝብ፣ ማህበረሰብ፣ የእምነት ተቋም የሚገጥመውን
ሸክም/ቅጣት/ እስከምን እንደሚነድ እንዴት ቅጣቱ እንደሚያበቃ፣ በቅጣቱስ ምን በማድረግ መዳን እንደሚችል
ርዕስ በርዕስ እየተነተነ ይገልፃል።


ይህ መልዕክት ለሁለም የሰው ዘር ሁሉ እንደ ልዑል ትዛዝና ፈቃድ የተዘጋጀ በሁለቱም መልዕክቶች ላይ

መሰረት ያደረገ ዝርዝር የድርጊት መመሪያ ስለሆነ የእግዚአብሔር እውነተኛ አገልጋዮች ፣የታመናችሁ የልዑል
ልጆች በየትኛውም የዓለም ፊት ኑሩ፣ በየትኛውም የህይወት ጎዳና ተሰማሩ ከመልዕክት 1 እስከ 2 እና ይህን ዝርዝር አመላካች መመሪያ ትጨብጡ ዘንድ ሁሉንም ክንዋኔ ትመዝኑበት ዘንድ በጥብቅ እመክራችኋለሁ። እንደምረዳው ለበጎ ቀን የተጠበቃችሁ ከጌታ ጋር ግንኙነታችሁ የጠበቀ በእጃችሁ ያለውን ትዕዛዝ ታውቃላችሁ። ፈጣሪ የሰጣችሁን ምልክት፣ተስፋና ኃላፊነት በማስታዋል በልባችሁ መዝግባችሁ ተጠባበቁ። ልዑል ቃሉን ሊፈፅም ጥሪው ደርሷችኋልና።



ሁሉንም አካሄዳችሁን መዝኑበት፣ አካባቢያችሁንም፣ የዓለምን ሁኔታ ሁሉ እዩበት ከልዑል የተሰጣችሁ መነፅር
ነውና። ዕውር ዕውር ነው ዕውርነት ስላችሁ መንፈሳዊ ዕውርነትን ነው። የመንፈስ ዕውር የጌታን የመንፈስ
መነፅር ሊያደርግ አይችልም። ምክንያቱም እንደ ሰውነቱ የተገዛው ለጨለማው መንፈስ ስለሆነ የብርሃን መንፈስን በደባልነት ሊያጠልቀው አይችልም አጥፊ ነውና።



ዕውር በፍፁም ጠቆረም ነጣ መነፅር ቢያደርግ ዕውርነቱን አይሸፍንለትም በመሆኑም ዕውራን የዘመናችን ታላላቅ ነን ባይ መንግሥታቶች፣ ሹሞቻቸው፣ የእነዚሁ መንግስታቶች አሽከርና ሎሌ መንግስታቶች ከነሹሞቻችሁ አንብቡት፣ እንደለመዳችሁት ወርውሩት ናቁት ተሳለቁበት ችግር የለውም የምትከፍሉትን ዋጋ ከየዝርዝር መግለጫው ስለምታዩት ትሰፈሩበታላችሁ ትጠረጉበታሊችሁ።



የናንተ ጉዞ ረግረግ ላይ እስከ ጉልበቱ ሰምጦ ኳስ እጫወታለሁ የሚልን የዋህ ይመስላል። ስለዚህም ትዕግስቱ
ካላችሁ አንብቡት የጥፋታችሁን ሂደትና ፍጥነት እዩበት።



ለወገኖቼ፣ ለወንድሞቼ፣ ለእህቶቼ፣ ለእናቶቼና አባቶቼ በየትኛውም የምድር ፊት ላላችሁ የእግዚአብሔር
በጎች የሚጠብቃችሁን ክብር፣ በረከት፣ መፅናናትና ደስታ በኔ አንደበት ልገልጽላችሁ ይቸግረኛልና ብቻ ፅኑ
በሚያበጥረው የእሳት ጉዞ ውስጥ ገብታችኋል። እሳቱ እናንተን አይጎዳም ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ አብዲናጎም በልዑል
የታመነ መልአክ / ገብርኤል ስለተጠበቁ ምንም እንዳልሆኑ እነሱን ለእሳት የጣሉትን እንደ በላ በምድሪቱ
የበቀሉት የሊባኖስ ዝግባዎች ረዥሙም አጭሩም ልቅም አድርጎ ሲበላ የምትታዘቡ ትሆናላችሁ ለመጭውም
ትውልድ ምስክር ሆናችሁ ትቆማላችሁ እናንተን የሚያስጨንቅ አደጋ አይመጣም።



ወደ ዕብራውያን ምዕራፍ 12 በሙሉ
መላው የሰው ዘር ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ አስተውሉ
ከእኔ ዘንድ የደረሳችሁ መልዕክት 1 እና መልዕክት 2 እና ይህ 3ኛው የመመሪያ የማብራሪያና የአፈፃፀም
የድርጊት ውሳኔ መግለጫ ሁሉ በቸሩ አምላካችን ታዝዤ ያደረግሁት መሆኑን በኔ ዕውቀት ጥበብና ፍላጎት የመጣ
እንዳልሆነ መታወቅ ይገባዋል። እኔ የልዑል አገልጋይ /የሥላሴ ባርያ/ ትዕዛዙን ፈፃሚ እንጂ በራሴ የማመንጨው አንዲት ነገር የለም።



የክርክር ዘመን አልፏል የእኔ አካሄዴ ትክክል ነው፣የኔ መስመር፣ የኔ እምነት የተሻለ ነው በሚል ከእውነት መንገድ የወጣም በእውነቱም የተመሰረተ የእምነት ጦርነት ሁሉ በሺዎች ዘመን አስቆጥሯል። ዛሬም ይኸው ያለና የሚታይ ነው። ግን አበቃ !



ሁለም ሰው በልዑል ፊት ባመነበት ቆሞ ተሟግቷል፣ ሃሳቡንና እምነቱን ለማስረፅ ከቅድመ አያቶቹ ጀምሮ ተጉዞበታል። ታዲያ ይኸው ሁኔታ የሚቀጥል መስሎአችሁ ሁላችሁም በተመሰረታችሁበት ቆማችሁ በየራሳችሁ መነፅር ስታዩ ኖራችኋል። ሁሉም ባመነበት በልዑል ችሎት ተሟግቷል። ውሳኔ ተላልፏል። ይግባኝ ተሰምቷል። ሌላ ይግባኝ የለም።



በኔ በልዑል ባሪያም የተላለፈውን መልዕክቶች ሁሉ እንደተወለዳችሁበት፣እንዳደጋችሁበት ዛሬም እንደምትኖሩበት አይንና ሕሊና እያያችሁት መልካም ነው።



ልብ ልትሉት የሚገባው ግን ዘመን አበቃ። ትዕዛዜና ፍርዴ ወጣ የአፈፃፀም መመሪያውም ይኸው ወጣ። የክርክር ዘመን አለፈ፣ተዘጋ። ከማነው የምትከራከሩት በየትኛው /ቤት የፍርድ ሂደት ክርክር ይደረጋል።
የፈጀውን ጊዜም ይፈጃል በኋላ በዳኛው ውሳኔ ይሰጣል። በቃ !



እየነገርኳችሁ ያለውን የልዑል ውሳኔ ነው። 1-2 ነግሯችኋል። የዛሬው የውሳኔ አፈፃፀምና መመሪያ ከነሙለ
ማብራሪያው ቀርቦላችኋል። አበቃ !



ትንቢተ ኢሳያስ 438 – 13
ማሳሰቢያ
በየርዕሱ ውስጥ የሚገለፁት ማብራሪዎች መመሪዎች የአፈፃፀምና የድርጊት ውሳኔዎች ሁሉ ርዕሱን
በሚገባ እንዲገልፁ የታሰበና ያረጋገጠ ነው። በየርዕሱ የምታዩት የምትረዱት ሁሉ አንድም ሳይወድቅ የሚፈፀምና የእናንተንም የሚዛን ግምት የሚያብራራ ሲሆን በዚያ ተመስርቶ የሚገጥማችሁን የቅጣት ሂደትና ፍፃሜውንም የሚያስረግጥ ነው።



1 ስለ ሁሉም መልዕክቶች የሰዎች አቀባበልና ምንነታቸው፡፡ በመላው ዓለም ፊት ተበትኖ የሚኖረው የሰው ዘር ቁጥር በዝቶ ምድርን መሸፈን ከጀመረ ጀምሮ እንደየአካባቢው ሁኔታ የሚስማማውን የኑሮ ሕግ መስርቶ በተለያየ የባህል እምነት የአኗኗር ደንብ እየተገዛ መኖር ከጀመረ ቆየ። 7500 ዘመኖችም አለፉ። ፈጣሪ ከዚህ ምድር አዳምና ሔዋንን ፈጥሮ ለመልካም ቢያስባቸውም በትዕዛዝ ጥሰት ከፊቱ መሸሽና ሞትን የሚያህል ዕዳ ከተሸከሙ በኋላ በምድር ፊት ተበትነው ጥረው ግረው እንዲኖሩ በመወሰኑ ይኸው ሂደት ቀጥሎ እዚህ ደርሰናል። ፈጣሪ ፈጥሮ አልተወንም ሰው ከሳተና ትዕዛዙን ካጠፋ ጀምሮ መልሶ የሚድንበትን መንገድ ጌታ አዘጋጀ። እንደ ቃሉ አደረገ ሰው ግን ሁሉንም ትዕዛዙን በማፍረስ የራሱን የጥፋት ህግ በማቆም መልካሙን ትቶ መጀመሪያ ጀምሮ ከመንገዱ ያወጣውን የእባብ ምክር /የዲያብሎስ ምክር/ በመስማት እስካሁን እንደጠፋ ፈጣሪውንም እንዳሳዘነ ይኖራል። ሸክሙ የቀለለውን ትዕዛዝ በማስቀመጥ እዳችንን የከፈለውን ፈጣሪያችን በትዕግስቱ ርቀት ተሸክመን ብርሃንን ትተን ወደ ጨለማው ስንጓዝ በማዘን ታገሰን ሰው ጌታ አልቆ ሲፈጥረው በአምሳሉ ምሳሌ አድርጎ ነው። የምድር ፍጥረትም ሲያስገዛለት ለሰው የሰጠውን ክብር ግልፅ ያደርገዋል
ጥቂቶች ለፈጣሪያቸው ፍቅር ተገዝተው ደምና አጥንት ገብረው የልዑልን ፍቅር ለብሰው ዓለም ንቃቸው
ተዋርደው የሚበልጠውን በመንፈስ አይተው ወደ ፈጣሪያቸው እቅፍ አልፈዋል።



የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1 9 - 28
የሚበዙት ደግሞ መልካሙን ትተው ወደ ጨለማ ተጉዘው ድንገት ወደ ሲዖል ወርደዋል።
የዛሬው እጅግ ከፍቶ የሚታየው የጥፋት ዘመን ከአለፈው ዘመን የጥፋት ጎዳና ጋር ሲነፃፀር እጅግ የከፋ ነው የሰው ልጅ ስብዕናው ወድቆ ከእንስሳ አንሷል በተለያየ የስጋ ምኞት ተጠልፎ የዱያብሎስ ወዳጅ የፈጠረው አምላክ ጠላት ሆኗል። ፈጣሪ የሚጠላውን ለማንገስ እጅግ ደክሟል፡፡ አመዛሪ ነው፣ ውሸታም ነው፣ ነፍሰ ገዳይ ነው፣ ገንዘብ አምላኩ ነው። ፈጣሪውን የካደ ነው። የተለያየ ባዕድ አምልኮ ወዳድና ተከታይ ነው። ጣኦት አምላኪ ነው። ሁሉንም በፈጣሪ የተጠሉትን ክፋቶች ሁሉ እንደመልካም በራሱ እንደነፃነት፣ እንደመብት በመቁጠር ተጀምሮ እስከሚያልቅ የሕይወቱ አካል ያደረጋቸው ናቸው። እንግዲህ በዚህ ሁሉ የፈጣሪ ትዕግስት አልቆ 7/3/1998 ጀምሮ የመጨረሻ ፍርድ እየተገለፀና ለመጨረሻ ጊዜ በድልሜ የልዑል ውሳኔ 27/9/2000 የፀናው የመጨረሻው ውሳኔ ለመላው ሕዝብ ቢገለፅም ከውስን ሰዎች በስተቀር የሰማ የለም። ለሕዝቡም በይፋ የገለፀ መንግስት የእምነት ተቋም ድርጅት የዜና መግለጫ የለም።


ይሁንና መልእክቱ የደረሳቸው እንደምን መልእክቱን ተቀበሉት በመልእክቱ ያላቸው አመለካከት ምን ይመስላል?

1- በአንደኛው ዘርፍ ያሉ ሰዎች አቀባበል በዚህ ክፍል ያሉ ሰዎች መልካም ሰዎች ናቸው ቀና ልብ አላቸው ትሁትና ቅኖችም ናቸው፡፡ በተለያየ የእምነት መስመር ይጓዙ እንጂ የፈጣሪን እውነት የሚወዱ ናቸው። እነዚህ ቅኖች የፈጠሪን ወቀሳና ግሳፄ ሁሉ በቅንነት ተቀብለው እራሳቸውን ከስህተት ለመመለስ ፈጥነው እርምጃ የሚወስዱ ናቸው።
መልዕክቶቹ እንደደረሳቸው በመልእክቱም መልእክት በመወቀስ ህሊናቸውን ወደ እውነት በመመለስ ለንስሃ
ራሳቸውን ያዘጋጁና በፍጥነትም የተመለሱ ሲሆን ያሉባቸውን ጉድለት በመልእክቱ መነፅርነት በማየት ወደፈጠሪያቸው ጉያ የተመለሱ ናቸው።


በሁለተኛው ዘርፍ ያሉ ሰዎች በዚህ ክልል ውስጥ የሚያርፉ ሰዎች በራሳቸውም ሆነ በቀረቡአቸው ሰውች ዙሪያ የሚያዝ የሚጨብጥ ባህርይ የሌላቸው ናቸው፡፡ ሁለት እግር ይዘው ሁለት ዛፍ ባንድ ጊዜ ለመውጣት የሚያስቡና የወሰኑ ናቸው፡ በማናቸውም ጉዳይ ላይ እምነት የማይጣልባቸው ናቸው፡፡ እምነትን ለማመን ከወሰኑም በመምሰ ለመጓዝ የሚወስኑም ናቸው፡፡ ቆርጠው ባንድ አቋም ፀንቶ ጥቅሙንም ጉዳቱን ለመቀበል የሚችልና የሚወስን ህሊና የላቸውም፡፡ አላማቸው ብቻ ነውና በማስተማርም የሚመስሉ አይነት አይደሉም ቢጎዱም ከዋዠቀው አቋማቸው አይወጡም አላማቸው ብቻ ነው፡፡ ጌታ በዮሐንስ ራዕይ ላይ እንደተናገረው

ሙቅነትም ቀዝቃዛነትም የሌላቸው ለብታን የተላበሱ በመሆናቸው ሊተፋቸው ያስጠነቀቃቸው አይነት
ናቸው፡፡ በመላው አለም በቁጥር በዝተው የሚታዩና ለማንኛውም ጉዳይ የማይበጁ ናቸው፡፡ በመልእክት 1
እንዲሁም በመልእክት 2 የተላለፉትን ወቃሽ ፈዋሽና ፈራጅ ገሳጭ መልእክቶች ሰምተው ለጊዜው የመደንገጥ
ምልክት የሚያሳዩ፣ ቆየት ብለው የተሰጣቸውን እድሜ በብልጠት ያገኙት አድርገው በመቁጠር ለከፋው የኑሮ
ገፅታቸው የአለሁበት ማረጋገጫ የሚሰጡ በመሆናቸው ተመልሰው እንደ እርያ ወደ ሃጢያት ጭቃ
የሚመለሱ በመሆናቸው፡፡ በዚህ የፍርድ አፈጻጸም ውስጥ በእሳት የሚበጠሩ ናቸው፡፡ በአብዛኛው የኑሮ
ምቾት የእውቀት ብዛት ያነቃቸው ሩጫቸው ባላቸው ላይ ለመጨመር የሚለፉና ለዚሁ ሁሉ ሌላውን
አሳልፈው የሚሰጡ ናቸው፡፡ በስልጣንም በንግድም በማናቸውም ማህበራዊ ሃላፊነት ቢቀመጡ አታለው
ለመኖር የሚጥሩ የሾማቸውን በከፉ ሰዓት ጥለው የሚጠፉ አምላካቸው ሆዳቸው ብቻ የሆኑም ናቸው፡፡
ስለዚህም አስቸጋሪ ሁኔታ የሚጠብቃቸው መሆኑን ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ፡፡


በሦስተኛው ዘርፍ ያሉ ሰዎች በዚህ መስፈርት የሚያርፉት ብዘውን ጊዜ የሚያጠፉትን፣ የሚሰሩትን፣ ማናቸውንም ጉዳይ አምነውበት ይበጀናል ብለው የሚፈጽሙ ናቸው፡፡ ጥፋትን ሲፈጽሙ ትክክል እንደሰሩ በነሱ እምነት ትክክል እንደሆነ የሚቆጥሩ ለበዙ ሰው የጋራም ሆነ የግል ተቃውሞና ግሳጼ ቦታ የማይሰጡ የኔ ትክክል ነው ብለው የሚያምኑና በዚህም እስከ መጉዳት የሚሄዱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ዛሬ በአለማችን ላይ በእምነት ውስጥ ለእምነቱ ብርቱ ተሟጋች ሆነው የሚቆሙ የሌላውን ተጻራሪነት በማናቸወም መንገድ ማስወገድ የሚፈልጉ ሲሆኑ በስልጣን ጫፍ ላይ ከመጡም ሥልጣኑን ለማቆየት ብቻ ሳይሆን በዚያ ስልጣን ላይ መቆየት አለብኝ ብለው ላመኑበት ምክንያት ጸንተው የሚቆሙ ናቸው፡፡ ከአቅማቸው በላይ የሆነ በግድ የሚያስወግዳቸው ሁኔታ ሲፈጠር ብቻ አቋማቸውን የሚፈትሹና ከጉዳት በኋላ እውነቱን የሚቀበሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በአለም ገጽታ ውስጥ በቁጥር መስፈርት እንደተመለከቱት አይበዙም በእምነት ስንሄድ ሐዋርያው ጳውሎስን ስናስብ ለፈሪሳዊነቱ ለሕጉ በጽኑ የቆመ ክርስቲያኖችን በማሳደድ እንቅልፍ ያጣ ሐዋርያቶችን እጅግ ያስጨነቀ ነበር፡፡ ጌታ ሲለውጠው እንኳን በሐዋርያቶች ዘንድ እሱን ለመቀበል ረዘም ላለ ጊዜ የተቸገሩበት ነበር፡፡ ሆኖም አምኖበት ነውና የተለወጠው በክርስቶስ የወንጌል ሥራ ከማንም በላይ ሠርቶ በመስዋእትነት ያለፈ

ጀግና ሐዋሪያ ነው፡፡ የቅርቡን በሥጋው ያለፉትን ብንጠቅስ ደግሞ እነአዶልፍ ሂትለር፣ እነሮማል፣ እነስታሊን፣ ባገራችንም እነበላይ ዘለቀ፣ እነምነግሰቱ ነዋይ፣ እነጀነራል ታሪኩን እጅግ ብዙ ሰዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በዚህ ክልል ለክፉ የሁን ለበጎ፣ በሥጋውም ይሁን በመንፈሳዊ የሚመጡ ሰዎች በግል እጅግ የሚደንቁኝ ናቸው፡፡

ከነዚህ ክልል ወደፊት በመንፈሳዊ ተልእኮም ሆነ በሥጋው ሥራ ብዙዎችን አያለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጥረቱ መስመር እንዲይዙ እውነትን እንዲጨብጡ መጣር ሲሆን ልዑል ከያለበት ያወጣቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ እነሙሴን፣ እነአብርሃምን፣ እነያእቆብን፣ ሁሉንም ሐዋርያቶች፣ ብንወስድ በዚህ ክልል የሚያርፉ ናቸው፡፡ ሙሴ ከክብር ወደአመነበት ወደጭቃና ወደወገኖቹ እስራኤላውያን ሲመለስ ቅርም አላለው የተወው ሕይወት /የግብፅ ሕይወት/ አልናፈቀውም ፈጣሪውን አወቀ በዚያው ጸንቶ ተጓዘ አለፈ፡፡


አብረሃም አባቱን እሱም ቤተሰቡም የሚያምንበትን ጣኦት ትቶ በሰማው የፈጣሪው ድምጽ አምኖ ሁሉን ትቶ
ወደበረሃ በእምነት ወጣ፤ ማንም ያላገኘውን የእምነት ጽናት በሥላሴዎች ታደለ፡፡ ተባረከበት፣ ተቀደሰበት፣
ለሁላችን ተረፈበት፣የዘለአለምን ሕያወት ወረሰበት፡፡ ያእቆብ ጽኑ የእምነት ታጋይ ነበር፤ ከፈጣሪ የብርሃን
መልአክ ጋር ካልባረከኝ አልለቅህም ብሎ ታግሏል ሹልደው ተጎድቶ በጥረቱ የተደነቀው ፈጣሪ በረከቱን
አጎናጽፎታል፡፡ ሐዋርያቶችን ብንወስድ ከተለያዩ ከተናቀ ሥፍራ ጌታ ቢሰበስባቸውም ለቃሉ ታምነው፣
በወንጌል ለኛ ሆነው ለትውልድ ተርፈው በታላቅ መስዋእትነት ለድል በቅተዋል፡፡ በአገራችን አፄ ቴዎድሮስን
እነላሊበላን፣ እነ ዘርአያእቆብን፣ እነ አፄ ዮሐንስን ብናስብ የእምነትም የአገርም መሪና ጀግና ሆነው ባመኑበት
ዋጋ ከፍለው አልፈዋል፡፡ ስለዚህ በስፋት ያሉ ሰዎች ለጥፋቱም እሰከጫፍ የሚሄዱ ለመልካሙም ብርቱ ዋጋ
የሚከፍሉ ናቸው፡፡ በዛሬው አለማችን ባመኑበት የተሰለፉ ብዙ ናቸው፡፡ ዲያቢሎስ ከነዚህ ሰዎች የህሊና
ምርኮኛ ለማግኘት በብረቱ የሚጥርበት ነው፡፡ እስከ ፍፃሜ ባስጨበጣቸው እውነት መሰል ጥፋቱ
ስለሚዘልቁ በብርቱ ይፈልጋቸዋል ይጠብቃቸዋል፡፡


በዚህ በአራተኛው ዘርፍ ያሉ ሰዎች በዚህ መስፈርት የሚከለሉት ደግሞ እጅግ መጥፎዎች ናቸው፡፡ እነዚህ በጎን መልካምን ነገር በፍፁም የማይወዱ፣ በጭካኔያቸው ወደር የማይገኝላቸው ፍፁም ትእቢተኞች ናቸው፡፡ ማንኛውም ነገር የሚለኩት ለራሳቸው የደስታ ምንጭ ይሆናል አይሆንም ከሚል መስፈርት በመሆኑ ከተጣመመው ፍላጎታቸው ጋር የሚጋጭ ሁሉ ቢጠፋ እምነታቸው ነው፡፡ እየሞቱም እየተሰቃዩም ቢሆን ከትእቢታቸው፣ ከክፋታቸው፣ መጥፎ ከመስራት የማይመለሱና ባሳለፉት መጥፎ ተግባር መዘከር የሚደሰቱ ስለዚህ ብቻ መስማት የሚወዱ ናቸው፡፡ ለዚህ ምሳሌ ጌታ ስለኛ በደል በመስቀል ሲሰቀል በመጥፎ ስራቸው ከተሰቀሉት ወንጀለኞች ነፍሰ ገዳዮች ውስጥ ግራና ቀኝ የተሰቀሉት ፋህታዊ ዘማዊና ፋህታዊ ፀጋምን ነበሩ፡፡ ፋህታዊ ዘማዊ 70 ነፍስ በመጨረሱ የተፈረደበት ሲሆን ፀጋም እንዲሁ ብዙ ነፍስ ያጠፋ ነው፡፡ ሁለቱም ስለጌታ መከራከር ጀመሩ በስተቀኝ ያለው ፋታዊ ዘማዊ ስለጌታ ንጹህነት በመመስከር የራሱን ወንጀለንነት በማመን፣ በመጸጸት ለቅጣቱ አግባብነት ተከራክሮ ጌታ ግን ንጹህ መሆኑን መስክሮ በመንግሥቱ እንዲያስበው ጠየቀ ምህረትም አገኘ፣ ገነት ከማንም ቀድሞ ከጌታ ጋር ገባ፡፡ በስተግራ የተሰቀለው ፋህታዊ ፀጋምን ግን ጌታን በመዝለፍ ንጉሥ ከሆነ ራሱን ያድን እያለ በማፌዝ በትእቢት እንደፀና አለፈ ወደ ጨለማው ነጎደ፡፡ በዚህ መስፈርት ያሉ በምንም መንገድ ቢሏቸው የማይመለሱ በመሆናቸው በፍርድ የሚያገኙትን ቅጣት መቀበል ያለባቸው ናቸው፡፡ ባሁኑ ዘመን እነዚህ እጅግ በዝተው እናገኛቸዋለን፡፡ በሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ቃል ተመስርቶ በፈቃዱ ታዘው የቀረቡት መልእክቶች ማንን ይዳኛሉ? በማንስ ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ?

የሰው ልጅ ከተፈጠረበት እለት ጀምሮ አክብሮ ሊኖርበት የሚገባ ትእዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ይህንን ትእዛዝ
ቢጥስ ደግሞ ቅጣት እንደሚከተለው በግልፅ የፈጠረን አምላክ ደንግጓል፡፡ መብትንና ግዴታን መመለሻውን
ድንበርና መሄጃውን መንገድ አመላክቶአል የሰው ልጅ ታዲያ ይህንን የልዑል ትእዛዝ አክብሮ አልኖረም
አባታችን አዳም እናታችን ሄዋን በእባብ ምክር በዲያቢሎስ ጠንሳሽነት ትእዛዝን አፍርሰው ከተሰጣቸው ድንበር
ወጡ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ያስቀመጠውን ትእዛዝ በመጣሳቸው አዘነም ተቆጣ በፍርድ ወንበሩ ላይ
ተቀመጠ የቅጣት ውሳኔውን ከመስጠቱ በፊት ለአጥፊዎቹ ምክንያታቸውን መሳሳት አለመሳሳታቸውን ጠየቀ፡፡
የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ አዳም በሄዋን ሄዋን በእባቡ አመካኙ ዛሬ የሰው ልጅ ሲያጠፋ ብዙ ምክንያት
እንደሚደረድረው ሁሉ አላጠፋሁም ብሎ መከራከር ከራስ ላይ የጥፋትን ሃላፊነት ማሸሽ ተጀመረ፡፡
ትእዛዝ(ሕግ) ሲጣስ ቅጣት አለ፡፡ ከቅጣቱ በፊት ለዳኝነቱ ትእዛዙን ያወጣው ጌታ በችሎቱ ይቀመጣል፡፡
ክርክር ይካሄዳል ቅጣቱ ይሰነዘራል፡፡ አዳም በማዘኑ በልቡ ይግባኝ በማለቱ ቢደመጥም የሞት ቅጣት
ተሰንዝሯል ለአዳም የሰው ዘር እየበዛ ምድርን እየሸፈነ ከመሄዱ በፊት ጌታ ሕግን እንዲጠብቅ በልቡናው ጻፈ
ክፉንና በጎውን እንዲለይ የሚያስችለው ህሊና ቀድሞም ሲፈጥረን ሰጥቶናል፣ በሕገ ልቡና ረዘም ያለ ዘመኖችን
የሰው ዘር ኖረ፡፡ በሕገ ልቦና ሰው ተዳኝቶአል፡፡ የኖህ ዘመንን ማሰብ በቂ ነው፡፡ ሰዶምና ጎሞራን ማስታወስ
ከበቂ በላይ ነው፡፡ በሁለቱም ወቅቶች ጌታ በልባቸው ባስቀመጠው ህገ ልቦና ፍርድ ሰጥቶአል፡፡ ዳኝነት
ተካሂዷል፡፡ ቅጣቱም ተሰንዝሮ ተፈጻሚ ሆኖአል፡፡


ጌታ ሰው በዝቶ ምድርን መሸፈን ከጀመረ በኋላ የግድ የተጻፈ ሕግ ያስፈልገው ዘንድ አየ፡፡ ፈቃዱም ሆነ

በአባታችን ሙሴ ህገ ኦሪት ተደነገገች በዚህም የሰው ልጅ መብትና ግዴታውን እንዲያውቅ ተደረገ፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት 2 16 - 17
ኦሪት ዘፍጥረት 3 በሙሉ
ኦሪት ዘፍጥረት 6. 7 በሙሉ
ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ሰው ሲያጠፋ፣ ሲቀጣ፣ ምህረት ሲጠይቅ፣ ንስሃ ሲገባ፣ ለጥፋት መስዋእት ሲያቀርብ፣ ምህረትን በይግባኝ ሲያገኝ በየጊዜው ልዑል ዳኝነት ሲሰጥ ዘመናችንም ሲከንፍ አባቶቻችንም ኖረውበት ሲያጠፉ፣ ሲማሩ፣ ወደ ምህረት ዘመን ተደረሰ፡፡ ጌታ እንደቃሉ ለአዳም እንደሰጠው የይግባኝ መብትና በዚያም በጨበጠው ተስፋ 5500 ዘመን በኋላ ጌታ ላንዴም ለሁሌም የሰውን የሃጢያት እዳ ለመክፈል መጣ፡፡


ቃሉን አከበረ፣ ሕግን ፈፀመ ሰው መፈፀም ያቃተውን ትእዛዙን ፈፀመ፡፡ ለሁሉም የሰው ልጅ ሃጢያት በመስቀሉ

ሻረ፡፡ የዘለአለምን ሕይወት ለኛ አፀና የልጅነት ክብርን አጎናጸፈን፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ አሁንም ቀሊል የሆነውን
ሕግና ትእዛዙን አስቀመጠ፡፡ እንጠብቀው ዘንድ አዘዘ፡፡ ስናጠፋ ንስሐ እንድንገባ እንቢ ብንል በችሎት ቀርበን እንደምንቀጣ አረጋገጠ፡፡ ሰው ሞገደኛ ነው ሁላችንም በስጋችን ተሸናፊ ነን፡፡ የምናየው ሁሉ፡፡ እኛም እራሳችን ሁሌ እንደፈነጨን የምንጓዝ ይመስለናል፡፡ በዚህም ትእዛዝን እንጥላለን፡፡ ንስሓ ገብተን በትእዛዝ ጥሰት የሚሰነዘርብንን ቅጣት በይግባኝ /በንስሐ/ ምህረት ማግኘት ስንችል በትእቢታችን በመግፋት እንጎዳለን፡፡
ጌታ ሁሌም ፍቅሩን በመግለጽ በመታገስ ጊዜ፣ በመስጠት፣ በመውቀስ ቀላል አባታዊ ቅጣት በመሰንዘር ወደ
ትክክለኛው መንገድ እንድንመለስ ሁሌ ያደርጋል ይሁንና ሁሉም ገደብ ስላለው የግድ ብርቱ ቅጣት ይመጣል፡
የሰው ልጅ ሁላችን የጌታን ሕግ ጥሰን የራሳችንን የሥጋ ሕግ የእግዚአብሄር ጠላት የሆነውን የዲያቢሎስ ሕግ
በማጽደቅ የፍቅር ሕጉን ንቀን አታመንዝር ያለውን እንደ መብት በሕጋችን የማመንዘርን ፈቃድ አስቀምጠን፣
አትግደል ያለውን እንገላለን፣ አትዋሽ እንዋሻለን፣ ወንድምህን እንደ ራስህ ውደድ ያለውን ትተን አይ የለም
ወንድም፤ ባልንጀራ ገንዘብ እንላለን፡፡ በሁሉም ትእዛዝ አፈረስን በጭለማ ህግ መመራት ጀመርን፡፡
በዚህም ምክንያት ሲታገስ የቆየው ጌያ በተለያዩ አገልጋዮቹ አማካኝነት ማስጠንቀቂያ ሰጠ፣ መከረ፣ ዘከረ፡፡
መልእክት 1 መልእክት 2 በቃሉ ተመስርቶ በኔ በትንሽ ባርያው ለሰው ሁሉ እንዲዳረስ አደረገ፡፡ ፍርዱን
በመልእክት 1 እንዳሳወቀ የደህንነቱን ትእዛዝ አወጣ ሶስት አመት ታገሶ ይግባኝ ያሉትን ( ምህረት የጠየቁትን )
በምህረቱ አተመ፡፡ የናቁትን፣ ይግባኝ ያላሉትን፣ ፍርዱን ያልተቀበሉትን ወደ አፈጻጸም ውሳኔ በመሻገር ፍርዱን
ለማጽናት ተሻገረ፡፡ የእየአንዳንዳችን መዝገብ ላይ በየ ደረጃው የተካሄደውን የፍርድ ሂደት ጨርሶ ወደ አፈጻጸም
አለፈ፡፡ ተወሰነ አበቃ፡፡ ፍርድ ምን እንደሚመስል ሁላችንም እናውቃለን፡፡
ትንቢተ ኢሳኢያስ ም፡ 53 በሙሉ
ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተፈረደ፡፡ ይግባኙ /ፍርድ ቤት ሄደ፡፡ተወሰነ፤ ከዚያ ወዲያ ወዴት ይኬዳል ወደ አፈጻጸም ብቻ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የዛሬው ይህ የፍርድ አፈጻጸምና መመሪያ ከልዑል ችሎት ወጣ፡፡ ይግባኝየለምጊዜየለም፣ ወደ አፈጸጸም የሄደ ውሳኔ በአስፈጻሚዎቹ እጅ ገብቷልና፡፡ መልክቶቹና ፍርድ ሂደት አፈጻጸምና ውጤቱ ወንድሞች፣ እህቶች፣ መላው የሰው ዘር በሙሉ፣ ሰማይና ምድርን የዘረጋ አምላካችን ሲያዝህ፣ ሲመክርህ፣ ሲወቅስህ፣ ለምን አትሰማም? እሱ የፈጠራቸውን እንደፈቃዱ የሚሽራቸውን፣ የሚሾማቸውን፣ የሥጋ አለቆች ትፈራለህ፡፡ እነሱ ሲሉህ ትደነግጣለህ፤ ሲያዙህ ትታዘዛለህ፣ ፈጽም
የተባልከውን ትፈጽማለህ፤ የአምለክህን ትዕዛዝ ግን ትንቃለህ፣ ታሾፋለህ፣ ታፌዝበታለህ፡፡


ብዙ አገልጋዮች ከልዑል ታዘው መጡ፤ መልእክቱን ተሸክመው፣ ምክርና ግሳጼውን፣ ቁጣውንና ፍርዱን፣

በረከትና ምህረቱን ላንተ ለማድረስ የታዘዘውን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር መልክቶች በመግለጻቸው
ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል፡፡ ይህ ሁሉ የተፈጸመው በዲያብሎስ በመመራት የጨለማን ህግ ለማጽናት በመሆኑ በዚህ ድርጊታቸው ገዥዎች ለስልጣናቸው ጥበቃ ሲሉ ሲፈጽሙት የኖሩት ነው፡፡ እነሱ እንደሚሹት መሆን አለበት ባዮች ናቸው፡፡


ይህን አመጻቸውን ለመግታት በተከታታይ የማሳሰቢያ፣ የመውቀሻ፣ የማስጠንቀቂያ መልአክቶች፣ ከጌታ

በአገልጋዮቹ በኩል ሲፈሱ ኖሩ ይሁንና አለም ናቀ በራሱ ሕግና ደንብ ሰመጠ፣ ፈጣሪን ወግድ አለ ይህንን የሺዎች
ዘመን ትእግስትም ልዑል ጨረሰና በኔ በባሪያው በኩል 7/3/1998 .. የመጀመሪያውን ምድርና በውስጧ
ያሉትን የሰው ዘር በሙሉ የተመለከተ ውሳኔ ፍርድ አስተላለፈ፣ ተመለሱ አለ 3 ዓመት እያመመው ጠበቀ ሆኖም
ይህንንም አልሰማ ላለው የሰው ልጅ የመጨረሻው ውሳኔ 27/9/2000 .. በኔው በባሪያው በኩል ተገለጸ፣
ለመሪዎችም፣ ለእምነት ተቋሞችም፣ ለግለሰቦችም፣ ለአለም አቀፍ ተቋሞችም፣ ለመላው አለም አቀፍ የዜና
አታሚዎችም ተሰጠ፡፡
ኦሪት ዘፀአት . 32 በሙሉ
ትንቢተ ኢሳኢያስ . 3 8 – 15
አስገራሚ ሕዝብ ነው አንድም መሪ ድርጅት፣ አንድም የሃይማኖት ተቋም ትንፍሽ አላለም እንደ ሃላፊነቱ በሚገዛው በሚመራው፣ በእምነት ስም ለሰበሰበው አልገለጸም መረጃ ለሕዝብ አድራሽ ነኝ የሚል ጋዜጠኛ ማንም አልተነፈሰም፡፡ 7/3/1998 የጀመረው የፍርድ ሂደት ቀጥሎ 27/9/2000 .. ምህረት ለጠየቁትም ለናቁትም ሁሉንም የይግባኝ የፍርድ ሂደት በልዑል ታየ የመጨረሻው ውሳኔ ጸና፡፡ ዛሬ ደግሞ የፍርድ አፈጻጸምና ሂደቱን ለመግለጽ፣ ለማሳወቅ ይህ ትእዛዝ በልዑል ፈቃድ በኔ በትንሹ ባሪያው እነሆ ለሰው ዘር በሙሉ ወጣ እንግዲህ አበቃ፡፡ አፈጻጸም ምን ይሆናል በሚል ሁላችንም ልናስብ እንችላለን እጅግ ብርቱ ቅጣትን የሚይዝ ነው፡፡


ትንቢተ ኢሳኢያስ 30 8 – 14

ሹሞቻችን ይፈርዳሉ እንደ ፍርዳቸው ያስራሉ፣ ይቀጣሉ፣ ይገላሉ፣ እነሱም ትላንት ሲፈርዱ ቆይተው በተራቸው ይፈረድባቸዋል፡፡ እንዳሰሩ ይታሰራሉ፣ እንደ ገደሉ ይገደላሉ፣ ይህ የአለም የህግ ስርአት ነው፡፡ ሁሉም የአለም ስርአት በቆመው ሕግ በየጊዜው በሚመጡ፣ በሚወርዱ አለቃና ምንዝሮች ይዳኛል እሱም ሲወድቅ በሌላው ተረኛ ይዳኛል፡፡ ፈጣሪ ይዳኛል እንጂ አይዳኝም ፈጣሪ ፈጠረን፣ ሰራን፣ አበጀን፣ በፍቃዱ እስትንፋስ ዘራብን፣ አእምሮ ሰጠን፣ እኛ ቢሻ የሚያኖረን ባይሻ የሚያተነን ነን፡፡ እኛንና በላይዋ የሃጢያት ማእበል ፈጠረን፤
የምንጨማለቅበትን አለምም በፈቀደው ሰዓት በቃ ቢል ምንተን ነን፡፡ የሰው ጥጋብ ግን ወሰን ያለፈ ነው፡፡ በወንዱም ላይ ሲሰለጥን፣ ሲግል፣ ሲቆርጥ፣ ሲያስር፣ ሲያጠፋ፣ ሲዘርፍ፣ በማይጨበጠው እሳት የሚዳብሰውን ጌታ ያቃልላል፣ ይንቃል፡፡ ጨርሶም በትእዛዙም በመልእክተም ንቀት ይሰነዝራል፡፡



ይህ የአገራችን መሪዎችና ሹሞች በህሊና ማጣት በትእቢት ሲፈጽሙት እያየን ነው፡፡ የከንቱ ከንቱዎች ናቸው፡ የእግዚአብሄር የፍርድ አፈጻጸም ሲጀመር አይታይም፣ ሲጨርስም አይዳበስም፡፡ በፈጣሪ ፍርድ የተያዘ መሪም ተመሪም ሁሉም የተሰጠውን የፍርድ አፈጻጸም ሊያልፍ አይችልም፡፡ የማያስተውል ሕዝብ ይገለበጣል ይላል የጌታ ቃል፤ እስከ ዛሬ ሲወቀሱ አልሰሙም፣ ሲጠፉም አይሰሙም፡፡ ውጤቱ በልዑል የተወሰነው እውን መሆን ብቻ ነው፡፡



3. ዓለም በጥቅሉ የሚገጥማት የቁጣ ፍሰት



ትንቢተ ኢሳኢያስ 24 1 – 13
በሁለቱም መልእክቶች እንደተገለጸው ዓለም 12/12/2000.. ጀምሮ ወደ ማበጠሪያው ወፍጮ
ገብታለች፡፡ ማበጠሪያው ትልልቁን ቆሻሻ የሚያስወግደው ሰፋ ያለ ቀዳዳዎች ባሉት የመጀመሪያው መሳሪያ ሲሆን ሁለተኛው ከአንደኛው የጠበበ 3ኛው 2ኛው እየጠበበ የሚመጣ የእሳት ወንፊት ጀምሯል፡፡ እጅግ ከብዶ ይቀጥላል፡፡



የልዑል ቁጣ ገና ጅምር አሳየ እንጂ ሲፈስ እጅግ ይከፋል፡፡ በሕሊናችን ያልገመትነው፣ ያላሰብነው ቁጣ ይፈሳል፡፡ ቀድሞ እንደነገርኳችሁ አንድም አገር፣ ማህበር፣ ተቋም፣ ግለሰብ አያመልጥም ሁሉም በተዘጋጀለት የቅጣት ጎዳና ይጓዛል፡፡ ሞት ከሆነ በሞት ለምኖ፣ ተሰቃይቶ ማለፍ ከሆነ ማለፍ፣ በጉዳት መቆም ከሆነ በጉዳት ባጠቃላይ
ሁሉም የተተመነለትን ይቀምሳል፡፡



በእግዚአብሄር የተመረጡት በምህረቱ የታተሙት ይቀራሉ፡፡ ለምህረት ታስበዋልና ምድርን ይወርሳሉ፡፡
ቀጣፊው፣ ውሸታሙ፣ አመንዛሪው፣ ነፍስ ገዳዩትእቢተኛው፣ በእውቀቱ የታበየው፣ በወርቁ በብሩ የተመካው፣
በታንኩ፣ በጀቱ፣ በኑዪክለሩ፣ በወታደሩ ብዛት የተመካው በሰበሰበው የሲሚንቶ ክምር የታበየው፣ በቆርቆሮና
የብረት ክምሮች የተመጻደቀው ሁሉ ወደ ትቢያነት ይለወጣሉ፡፡ ፋብሪካ፣ እንዱስትሪ፣ ሲደከምበት የኖሩበት ሁሉ ለተባረኩት ይቀራል፡፡ እሱ የተባረከውን ዘመን ስለማያይ ከነዘሩ ይጠረጋል፡፡



ውጤቱ ከላይ እንደተገለጸው ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በየአንዳንዱ የየአገሮች እጣ ፈንታ ርእስ
ውስጥ በዝርዝር ስለሚጠቀስ በዚያ የሚገለጸውን በጥንቃቄ ያንብቡ፡፡


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment