በኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሽጋችሁ ከአለቃ እስከ ምንዝር ላላችሁ በሙሉ !!
የእግዚአብሔርን በጎች አርዳችኋል፣ በልታችኋል፣ ለአውሬ ሰጥታችኋል፣ ሸጣችኋል ፣ ለውጣችኋል፣ ለሆዳችሁ፣
ለክብራችሁ፣ ለገንዘባችሁ የእግዚአብሄርን እውነት ለውጣችኋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ተሰብስባችሁ ዘወትር የጌታን ቁስል ትወጋላችሁ፡፡ በእመቤታችን ስም ትነግዳለችሁ፤ ታላግጣላችሁ፤ የፖለቲካ ሰራተኛ ሆናችሁ፤ የተሰጣችሁን መንፈሳዊ ስራና እረኝነት ለቄሳር ስራ ለውጣችኋል፡፡ ትገላላችሁ ታስገድላልችሁ፡፡ የአምላካችን ስጋው በሚፈተትበት ደሙ በሚፈስበት ቤተ ክርስቲያን በጎቹን ጠቦቶቹን ግልገሎቹን በሙሉ አርዳችሁ በልታችኋል ! ፍጹም ተኩላ ሁናችኋል፡፡ ህዝቅኤል ም ፡ 34
ስለዚህ አንድም አታመልጡም፤ ወዴትም መሸሻ የላችሁም፤ ፍጹም ትረገጣላችሁ ! የሰበሰባችሁትን እሳት ይበላዋል ! ለዘራችሁ ለስማችሁ ማረፊያ አታገኙም፤ እንደ ትቢያና አቡአራ ትበናለችሁ !! ተሃድሶ ነኝ ! ጸጋ ነኝ ! ቅባት ነኝ ! እያላችሁ በእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ላይ ያላገጣችሁ የእመቤቴን ክብር ለመቀነስ የለፋችሁ፤ የጌታን ፍቅር ክፍያ ያሳነሳችሁ፤ የዲያብሎስ ልጆች ሆይ ! ፀሀይ ሲመታው እንደሚጠፋ ሙጃ ትደርቃላችሁ፤ ለእሳትም ትጣላላችሁ !!
እግዚአብሄር የታመኑ እረኞቹን መርጧል ! አዘጋጅቷል ! ቀብቷል ! ያፈረሳችሁትን ቤት ይገነባል፡፡ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ትታነጻለች፤ እንደ ገና እንደ ፀሀይ ታበራለች፡፡ አንተ ተኩላ፣ የሰይጣን ልጅ ትጠረጋለህ አንድህም አታመልጥም !!
ተዋህዶ ኦርቶዶክስ የእውነት እምነት ባለቤት እንጂ የተኩላዎች መሰብሰቢያ አትሆንም ! የመጀመሪያው ጽዳት በእግዚአብሄር ቤት ይጀምራል ! እሳት ይበረብርሀል፣ እሳት ያበጥርሃል፣ የዘራኸውን ታጭዳለህ !!
ያሳደዳችኋቸው ፣ ያሰራችኋቸው፣ የጨፈጨፋኋቸው፣ የገደላችኋቸው የእምነት አርበኞች፣ ይፋረዱአችኋል፤ በእሳት ያነደዳችሁት ገዳምና ቤተ ክርስቲያን እጅግ ውድ ዋጋ ያስከፍላችኋል !
ዛሬ ዲያብሎስን የምትመርቁና የምታወድሱ ዲያቆናትና ቄሶች፣ ባህታውያን፣ ጳጳሳት፣ ስጋችሁን አወፍራችሁ ምላሳችሁን አጣፍጣችሁ አለሃፍረት ላላችሁ ሁሉ የትም ገብታችሁ አታመልጡም፤ የከፋ፣ የበረታ ቅጣት ትቀበላላችሁ፡፡
የእግዚአብሄር ቤት ትታነጻለች . ከተኩላ፣ ከተባይ፣ ትጸዳለች፤ ታሪኩአ ይመለሳል፡፡ ክብሯ ይታደሳል፣ቅርሷ
ይሰበሰባል፣የእምነት ባለሟሎችና አርበኞች ከተሳደዱበት፣ ከታሰሩበት፣ ከተጣሉበት፣በክብርና በሙላት ይመለሳሉ፤ ይፈወሳሉ፣ ይጠገናሉ፣ እንደ ጸሀይ ያበራሉ፡፡ እውነተኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ይፈወሳሉ !ይጠገናሉ ! በለመለመው መስክ ያድራሉ ! በታመኑ እረኞች ይጠበቃሉ !! ለፈጣሪ ታምናችሁ፣ በድንግል ማርም ጸንታችሁ፣ ለአገልግሎት ጸንታችሁ፣ ከንግድ ስራና ከሸመታ እርቃችሁ፣ ለቃሉ የምትተጉ አይዟችሁ፤ ዋጋችሁ በፈጣሪ እጅ ነው፡፡ ትደምቃላችሁ ! ታበራላችሁ !!
ተዋህዶን እምነት ለስጋ ትርፋችሁ ያደረጋችሁ ወደ ንግድ ጣቢያነት ለለወጣችሁ ወዮላችሁ !!
ትንቢተ አሞጽ ም 2 ፡ ቁ 13 – 16
ስለጣፈጠው ምላሳችሁ በህዝብ ፊት የከበራችሁ በውስጣችሁ አመጽና ቅሚያ ለሞላባችሁ ልብና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ፍርዳችሁን እንደፀሀይ ያወጣዋል !
በሰው ፊት የከበረ በፈጣሪ ይናቃል፡፡ በሰው የተናቀ በፈጣሪ ይከብራል፡፡ ሰው እንደሚያይ ፈጣሪያችን አያይም፣ አይቶም አያውቅም፡፡ እንደሰው የውጭን ገጽታን ፣ ውበትን፣ አለባበስን፣ አነጋገርን አያይም፡፡ እሱ የሚፈትሸው ልብና ህሊናን ነው፡፡ ፍርዱም የሚመሰረተው በዚህ መሰረት ነው፡፡ በመሆኑም ብዙውን ሰዎች የወደዱትና ያጸደቁት ወይም የመረጡት ይወድቃል፡፡ በተጻራሪው የናቁት ይጸድቃል፡፡
ዳዊትን ከነትቢያ ያነሳ ፣ ሳሙኤል ብላቴናውን ከኤሊና ከከበሩ ልጆቹ ይልቅ ወዶ የመረጠ፣ አብርሃምን ከጣኦት አምላኪዎች መሃል መርጦ የወጣ፣ ሃዋርያትን ከየአሳ ማጥመጃ የመረጠ፣ ከተናቀው የቀረጥ ስራ የጠራ፣ የከበሩትን የህግ አወቂዎቹን አነ ገማልያንን ከከበረ ሙክራብ ላይ ያልጠራና ያልመረጠ እግዚአብሄር ሃሳቡ ከኛ ሃሳብ የተለየ ነው፡፡ በኢትዮጵያችንም የሚሆነው ይኸው ነው፡፡ ተናቁ በእውቀታቸውም፣በኑሮአቸውም በሁሉም ነገራቸው እዚህ ግቡ የማይባሉ ተመረጡ !! ተቀብተው ታመኑ ! የእግዚአብሄር ምርጫ ነው፡፡ ትቃወሙት ዘንድ ይቻላልን ! ምንስ ስለሆናችሁ ! ሁሉንም ወደፊት ማየት የተሻለ ነው !! ስለዚህ በመልካም ሰአት እግዚአብሔር ሊጎበኘን በቀረበበት ጊዜ በቤቱ የበቀሉ ጠማማና ወልጋዳዎች ይወገዳሉ ይጠረጋሉ !
፡፡
የዛሬው የተወህዶ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችና እረኞች ስሙ አድምጡ ! ጊዜው አለቀ፤ የዘራችሁትን ማጨጃው ሰአት ደረሰ ! አጫጁም እነሆ በደጃችሁ ቆመ፡፡ ፈጥነህ ውደቅ አታመልጥምና ! በፈጣሪ የታመኑትን የተወደዱትንና ለቃሉ የሚተጉትን፣ ከጳጳስ እስከ ዲያቆን ያሉትን በገዳማት በገጠር ቤተ ክርስቲያን በማስተማር ፣ በቅኔ፣ በድጉአ፣ በዜማ በአቋቋም፣ በተለያየ ትምህርተ ተወህዶ እምነት አንጸው በማውጣት የተሰማሩትን የእግዚአብሄር በጎችና እረኞች ለቅማችሁ አጥፍታችኋል፡፡ በናንተ ቤት እግዚአብሔር አያይም ይመስላችኋል፡፡ አሁን ወዴት ታመልጣለችሁ !
የፍጸሜአችሁ ቀን ደረሰ፡፡ ስራችሁ ተከተላችሁ፡፡ አታመልጡም የፈጣሪ ውሳኔ አርፏል ! የዘራችሁትን ታጭዳላችሁ፡፡ እንሸሻለን፣ አናመልጣለን ብላችሁ አታስቡ፤ ይህ ድሮ ቀረ፡፡ ከአሁን በኋላ ሰው አምልጦ የሚድነው ወደ ኢዮጵያ መጥቶ በመጠለል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ሽሽት ወዴት ! እናንተ መሸሸጊያ ይሆናሉ ብላችሁ በስጋችሁ ያደራጅኋቸው እነባቢሎን ( አሜሪካ )፣ እነአውሮፓ፣ ወይም ኤሽያ ፣ አረቢያም ሁሉም በእዚህም ጽዳት ይካሄዳል፡፡ ምሽጉ የትጋ ነው ! ራሳችሁንና ስራችሁን ይዛችሁ በፈጣሪ እጅ ፍርዱን መጠበቅ ብቻ ነው፡፡ ተጣምራችሁና እጅና ጓአንት ሆናችሁ አባራችኋቸው የምትሰሩላቸውን ሃይሎች እጣፈንታም
ከናንተው ይከፋል እንጂ አይለይም፡፡ ምሽግ የለም ! ሁሉም ተጭኖ መጥቶአል፡፡
Blogger Comment
Facebook Comment