አለቃ አያሌው ታምሩ - ፺፮ኛ ዓመት የልደት በዓል


በዛቲ ዕለት አመ ፳ወ፫ ለመጋቢት ኮነ ልደቱ ለአቡነ ወልደ ጊዮርጊስ ዘውእቱ አለቃ አያሌው ታምሩ፡፡
በተሰጣቸው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ በመረዳት እስከ ዛሬ ድረስ ያልተፈታውን የአገራችንን የኢትዮጵያን ዋነኛ ችግር ከ፷ ዓመታት በፊት ያዩ፣ ሳይታክቱ ያስተማሩ፣ መፍትሔውን ያመላከቱና አድማጭ አጥተው እያዘኑ ያለፉ ታላቅ ክቡር ኢትዮጵያዊ አባት አለቃ አያሌው ታምሩ በዛሬዋ ዕለት ተወለዱ፡፡
ክቡራን ኢትዮጵያውያን! በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ ሊቃውንት፣ በተለያየ ደረጃ ያላችሁ አገልጋዮችና ምእመናን!
ቅድስት አገራችን ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየገባችበት ካለው የመከራ አረንቋ ትወጣ ዘንድ በኢትዮጵያዊው ነቢይና ሐዋርያ የተሰጡ ትምሕርቶችንና ምክሮችን ወደ ኋላ ሄዳችሁ በማስታወስ ተግባራዊ እንድታደርጉ ይኽን በማድረግም አገርን፣ ህዝብን ራሳችሁንም ጭምር ሊመጣ ካለው ጭንቅና መከራ አንድትታደጉ ከታሪክ ተወቃሽነትም እንድትድኑ በኢትዮጵያና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምላክ ስም እንጠይቃለን፡፡
ምንጭ፦ aleqayalewtamiru.info
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment