✍ ይታገሡ በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር | ሰላቢ እጆች
ባለስምንት አቅጣጫ ኮከብ የካህኑ መልከጼዴቅ ምልክት እንደሆነ ይነገርለታል። ይህ ምልክት ከዚህም በተጨማሪ በካህኑ መልከጼዴቅ በኩል የሚገኘው የአስተሳሳብ መስመር ጠቋሚና የጥንታዊ ኢትዮጵያ ስልጣኔ ምንጭ እንደሆነ መጽሐፈ ነገደ ሰብ/አዳም/ ይናገራል። ይህ የአስተሳሰብ መስመር በ12ተኛ ክፍለ ዘመን ማብቂያ በ13ተኛ ክፍል ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ከኢትዮጵያዊያኖች ዘንድ እየተዘነጋ እንደመጣና ይህንን መስመር ዳግም ወደ መታወቅ ሊያመጡ ይችላሉ የተባሉ መንፈሳዊም ይሁን ቁሳዊ አስተሳሰቦች ከሰዎች ህሊና እንዲዘነጉ በሌላ የአስተሳሰብ ተረኮች ተለውጠዋል። ይህም ቢሆን ግን ባለ ስምንት አቅጣጫ ኮከብ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ስነ-ህንጻ ላይ ዛሬም ይታያል።
ይኽንንም ክብ ቅርፅ ያላቸውን የኢትዮጵያ ቤተክርስትያናት በመመለከት ስምንት ጎን እንዳላቸው ማረጋገጥ እንችላለን። ጥያቄው የሚሆነውም ይህንን ስምንት አቅጣጫ የመከተልን ሃሳብ ከየት አመጡት? የሚለው ነው፡፡ በእርግጥም እነዚህ ሕዝቦች ከማንም ያልተዋሱት የራሳቸው የሚሉት አስተሳሳብ እንደነበራቸው ምንም የሚያጠያይቅ አይደለም። ለማንኛውም በምስሉ ላይ እንደምንመለከቱት ባለ ስምንት ጫፍ ኮከብና በድንጋይ ላይ የተጻፈው ጽሁፍ እንዲሁም ሌሎችም ቁሶች ከኤረር /ከአዳም ርስት ሀገር (የእኛቱ ኢትዮጵያ)ማዕከላዊ ስፍራ/በስተምሥራቅ አቅጣጫ ላይ ከሚገኝ ተራራ ላይ ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት በቁፋሮ የተገኙ ናቸው። ይህንን ተከትሎም በዚሁ ስፍራ ላይ የካህኑ መልከጼዴቅ ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊተከል ችሏል። ይሁን እና ይህ ባለ ስምንት ኮከብ የስልጣኔያችን አንዱ አካል እንደሆነ ይታመናል፡፡ ግን የአባቶቻችን የእውቀት አድማሰ ለእኛ እንዳያንፀባርቅ ድንቁርና እና ዘመናዊትት የሚባል ብኩን የህይወት መንገድ አይናችንን ጋረደን፡፡ .....ስለዚህ የአባታችን የአዳም እና የእናታችን የሄዋን ምድራዊው መኖርያ ኢትዮጵያዊ ውስጥ እንደነበር ለመገመት የሚከብድ አይመስለኝም? ፈርንጆቹ እንደሚሉት እውነትም የሰው ዘር መገኛ ኢትዮጰያ ሀገራችን ነች ጥያቄው እነሱ ሉሲ ያሏት የ3 ሚሊየን አመት እድሜ እንዳላት ይናገራሉ ይህን ግን በኢትዮጵያዊያን የጊዜ ሰሌዳና በኢትዮጵያዊያን አስተምህሮት ተቀባይነት የለውም፡፡ እውነቱ ግን ይህ ነው የእኛይቱ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ የአዳም የእርስት ሀገሩ የገነትም የሲኦልም መሸሸጊያ ገነትን የሚያጠጣው የግዮን ምንጭ መፍለቂያ የሰማዩ ባለቤት የቃልኪዳኑ ማሰሪያ ገመድ የመፀሀፍ ቅዱስ አርስትም መደምደሚያ የመላእክት ልዩ ጥበቃ ያላት ናት።
ኢትዮጵያ የታቧተ ፅዮን መገኛ የነፅነት አርነት ተምሳሌት የምትታይ ግን ያልታወቀች የተገለጠች ግን በሚስጥር ግምጃ የተሸፈነች ደሀ ስትሆን የጥበብ ሀብታም አላዋቂ ስትመሰል ግን 100 % ጭንቅላቱን የተጠቀመዉ ሞትን ያላየው የነቅዱስ ሐኖክ ሀገር ኢምነት ስትመስል ግን ፈጣሪዋ የተሰቀለበትን አማናዊዉ ግማደ መስቀል በጉያዋ የያዘች ትንሽ ስትመስል በፍቅር እግዚአብሄር የገዘፈች..... ይህ ውሸት አይደለም ግን በአባቶቻችን ተጠብቆ የሚኖር እውነት ነው፡፡ ወገኔ ሀገረክን ስታውቃት ኢትዮጰያችን ትንሽም ማወቅ ስንጀምር እንዲህ ኢትዮጵያ እውነትም የፈጣሪ የሚስጥር ዶሴ ናት ትላለህ!!!!
Blogger Comment
Facebook Comment