ፀሐይ በአመቱን ውስጥ በምትጓዝበት ጊዜ በሶስት ዋና ዋና ክበቦች ላይ የምትመላለስለስበት ጊዜ አራቱ ወቅቶች ይፈጠራሉ። ከነዚህ ሶስት የሃሳብ መስመሮች አንደኛው የምድር ወገብ ላይ ያለው ክበብ ሲሆን ሁለተኛው ክምድር ወገብ 23 ዲግሪ ከፍ ብሎ ያለው ትንሹ ክበብ ወይም (topic of cancer) ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ በጣም ሰፊው (topic of Capricorn) ከምድር ወገብ 23 ዲግሪ ዝቅ ብሎ የሚገኘው ነው።
1.ፀደይ - ከመጋቢት 26 እስከ ሰኔ 25 ያለው ወቅት ሲሆን ከጷግሜ 1ቀን ተጨምሮለት በአጠቃላይ 91 ቀን ያለው ነው። ይህ ወቅት የሚፈጠረው ፀሃይ ከምድር ወገብ ካለው ክበብ ወደ 23 ዲግሪ ከፍ ብሎ ወዳለው ትንሹ ክበብ ወይም (topic of cancer) በምታደርገው ጉዞ ሲሆን በዚህ ጊዜ ቀኑ እየረዘመ እየረዘመ መጥቶ በአመቱ ውስጥ በጣም ከፍተኛው የብርሃን ጊዜ እና በጣም አጭሩ ማታ ጊዜ የሚፈጠርበት ወቅት ነው።
2. ክረምት - ሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ያለው ወቅት ሲሆን ከጷግሜ 1ቀን ተጨምሮለት በአጠቃላይ 91 ቀን ያለው ነው። ይህ ወቅት የሚፈጠረው ፀሐይ ትንሹ ክበብ ወይም (topic of cancer) ወደ ከምድር ወገብ ካለው ክበብ በምትመለስበት ጊዜ ሲሆን በዚህ ጊዜ ቀኑ እያጠረ ማታው ደግሞ እየረዘመ የሚመጣበት ወቅት ነው።
3 .መከር - መስከረም 26 እስከ ታህሳስ 25 ያለው ወቅት ሲሆን ከጷግሜ 1ቀን ተጨምሮለት በአጠቃላይ 91 ቀን ያለው ነው። ይህ ወቅት የሚፈጠረው ፀሐይ ከምድር ወገብ ካለው ክበብ ወደ 23 ዲግሪ ዝቅ ብሎ ወዳለው ታላቁ ክበብ ወይም (topic of Capricorn) በምታደርገው ጉዞ ሲሆን በዚህ ጊዜ ቀኑ እያጠረ እያጠረ መጥቶ በአመቱ ውስጥ በጣም ዝቅተኛው የብርሃን ጌዜ እና በጣም ረጅሙ ማታ ጊዜ የሚፈጠርበት ወቅት ነው (የገና ጀምበር የሚባለውም ቀኑ በጣም ሰለሚያጥር ነው )።
4. በጋ - ታህሳስ 26 እስከ መጋቢት 25 ያለው ወቅት ሲሆን ከጷግሜ 1ቀን ተጨምሮለት በአጠቃላይ 91 ቀን ያለው ነው። ይህ ወቅት የሚፈጠረው ፀሐይ ታላቁ ክበብ ወይም (topic of Capricorn) ወደ ከምድር ወገብ ካለው ክበብ በምትመለስበት ጊዜ ሲሆን በዚህ ጊዜ ቀኑ መርዘም የሚጀምርበት እና ማታው ደግሞ እያጠረ የሚመጣበት ወቅት ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment