ክብረ ነገሥት መጽሐፍ በመኖሩ የኢትዮጵያውያን ማንነት እና ታሪክ ምን ያህል ተቀየረ?


ይህ ክብረ ነገሥት መጽሐፍ በመኖሩ የኢትዮጵያውያን ማንነት እና ታሪክ ምን ያህል ተቀየረ? ... መጽሐፉስ ባይኖር ኖሮ የኢትዮጵያውያን ብሎም የዓለም ታሪክ ምን ያህል ይቀየር ነበር ፣ አንዳንድ ሃገራት ሙሉ ለሙሉ ከዓለም ካርታ ላይ ላይኖሩ ይችሉ ነበር... ስለነዚህ ጉዳዮች ቀጥለን እናያለን።

በክብረ ነገሥት መጽሐፍ ላይ የሚነሱት ዋና ዋን ነጥቦች፦

- የሰሎሞን ሥርወ መንግሥት መሠረት
- የንግሥተ ሳባ እና የንጉሥ ሰሎሞን ጉዞ
- የቃል ኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ መምጣት
- የኢትዮጵያውያን ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና መሸጋገር ናቸው።

ከነዚ ነጥቦች ጀርባ ግን አንድ ትልቅ ጉዳይ በታሪክ መጽሐፉ መልክት ውስጥ አብሮ ይተላለፋል... ይህንን ጉዳን ከማንሳታችን በፊት ግን መጽሐፉ በመኖሩ እና ባይኖር ብለን የዓለም ታሪክ ምን ያህል ይለወጥ ነበር የሚለው እንመልከት።

አብርሃም እግዚአብሔርን በመፈለጉ ትእዛዛቱንም ሁሉ በመፈጸሙ እግዚአብሔር ለአብርሃም ቀጥሎም ለይስሃቅ እና ለያቆብ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል ይህም  ታላቅ ህዝብ እንደሚያደርጋቸው፣ ርስት የምትሆናቸውን ሃገር እንደሚሰጣቸው፣ አህዛብም በነሱ በኩል እንደሚባረኩ ቃል ገብቶላቸዋል... እግዚአብሔርም በቃል ኪዳኑ መሠረት  ከያቆብ አስራሁለቱን ነገደ እስራኤልን እንዳወጣ እና እንዳበዛቸው ታላቅ ህዝብም እንዳደረጋቸው፣ ርስት የምትሆናቸውን የከነአን ምድርም እንደሰጣቸው፣ እሰራኤልም ደግሞ የእግዚአብሔር ህዝብ በመሆናቸው ከሌላው አህዛብ የሚለያቸውን ኦሪትን ህግጋት እና ስርዓት እንደሰጣቸው በመጽሕፍ ቅዱስ ላይ ያለ ታሪክ ነው።

የኦሪት ህግጋት የተሰጡት ለእስራኤላውያን ብቻ እንደሆነ እስራኤላውያን እነዚህን የኦሪት ህግጋት እና ስርዓቶች ለሌላው ህዝብ ወይም አህዛብ የመስበክ፣ አህዛብም የኦሪትን ሕግጋት የመጠበቅ ግዴታ እንደሌለባቸው  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ተቀመጦ  እናየዋለን።

ለምሳሌም  እስራኤላውያን ሃገር መስርተው፣ ንጉሥ አግሠው፣  ኃያል ሆነው በዙራያቸው ያሉ አህዛብን በሚያስገብሩበት ጊዜ ወደ አህዛብ ሄደው የኛን የኦሪትን ህግ እና ስርዓት ተከተሉ ብለው ተጽእኖ የፈጠሩበት በዚህን መልኩ ሰዎችን የቀየሩበት እንድም አጋጣሚ የለም፣ በሌላ መልኩ ደግሞ  እስራኤላውያን አቅም አጥተው ከሃገራቸው ተሰደው ወደ በተለያየ ሃገራት በኖሩባቸው ጊዜያት ለምሳሌ ወደ ግብጽ ፣ ወደ ባቢሎን ፣ ወደ ሮም ግዛቶች  ሁሉ ሲሰደዱ  የራሳቸውን የኦሪትን ህግ እና ስርዓቶችን ጠብቀው  ከአህዛብ ጋር ሳይጋቡ እራሳቸውን ለይተው የመኖር ልምድ እንዳላቸው እንጂ ኦሪትን ለሌላው ህዝብ እንስበክ ከአህዛብ ጋር ተዋልደን ዘራችንን እናብዛ በፍጹም አይሉም አያደርጉም ነበር።

በአጠቃላይ  የኦሪትን ህግጋት የመጠበት ግዴታ ያለባቸው የአብርሃም ዘር የሆኑት ህዝብ ብቻ ናቸው ማለት ነው፣  የኦሪት ስርዓት ካለ እስራኤላውያን እዛ እሉ ማለት ነው።

ታዲያ ይህንን የእስራኤላውያን ታሪክ እውነታ ከተረዳን ቡሃላ ወደ ኢትዮጵያ ስንመለከት ፣  የኦሪት ስርዓት በኢትዮጵያን ህዝቦች ዘንድ ከጥግ እስከ ጥግ ክላይ እንከታች ድረስ ስትፈጸም እናያለን ፣ ከታቦተ ጽዮን ጀምሮ ፣ የኦሪት መስዋእት ማቅረቢያዎች  እና  ምኩራባት በሃገሪቱ የተለያየ ቦታዎች መኖር፣ የኦሪት  መጻህፍት መኖር፣ የሰንበት አከባበር ፣ የሚበሉ እና የማይበሉ እንስሳት መለየት ፣ ግርዛት ፣ የበዓላት አከባበር፣ የቤተ ክህነት መገልገያ እቃዎች እና ስርዓት፣ የዜማ መሳሪያዎች (በገና ማሲንቆ)፣ ሌሎችም ብዙ የኦሪት ህጎች እና ስርዓት በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲተገበሩ በምናይበት ጊዜ ሁለት አይነት ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል።

አንደኛው ኢትዮጵያውያን የኦሪትን ስርዓት የሚፈጽሙት ወደ ሃገራቸው ከሄዱት በጣም ጥቂት እራኤላውያን ተምረውት ነው ...

ሁለተኛው ደግሞ በቃ ይህንን ሁሉ የኦሪት ስርዓት ያላቸው ኢትዮጵያውያን እራሳቸው በመጽሐፍ  ቅዱስ ላይ ያሉት እስራኤላውያን ናቸው ማለት ነው።

ሁለተኛው መደምደሚያ አሁን ላሉት እስራኤልነን ብለው ላሉት አይሁዳውያን እንደ እሬት እጅግ በጣም የሚመር በፍጹም በፍጹም መስማት የማይፈልጉት  እውነታ ነው፣ ይሄ እውነት የነሱን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ፣ የዘር ግንዳቸው ሃሰተኛነት የሚያረጋግጥ አሁን ያለቸው እስራኤል የምትባለው ሃገር ላትኖር የምችልበት አጋጣሚ  ሁሉ የሚፈጥር  ነው ፣ ምክንያቱም እውነተኞቹ እስራኤሎች ያሉት ኢትዮጵያ ከሆነ ሌላ እስራኤል የምትባል ሃገር እና ህዝብ  አያስፈልግም  ማለት ነው፣  በኦሪትም ላይ ወንጌል እንደተጨመረ የሚጠበቀው መሲህም እንደመጣ፣ መሲሁን ያልተቀበሉት የሰቀሉት እስራኤላውያን እንዳሉም፣ ክርስቶስን አምላክነቱን ጌትነቱ  የተቀበሉ እስራኤላውያን እንዳሉ  እነዚህም በኢትዮጵያ ያሉት ክርስቲያኖች  እነደሆኑ በነቢያት የተነገረው ትንቢት ሁሉ እንደተፈጸመ ፣  የአሁኖቹን አይሁዳውያን ክህደታቸውን እና አታላይነታቸውን ስለሚያጋልጥ ኢትዮጵያውያን እውነተኛ  ማንነታቸውን እንዲያውቁ የዓለምም ህዝብ እንዲያውቅ አይፈልጉም   ...

ከአሁኖቹ አይሁዳውያን ተጨማሪም የአውሮፓውያኑ እና የምዕራባውያኑ የካቶሊኩም የፕሮቴስታንቱም የእስላሞችም መሠረት ይናጋል...  ምክንያቱም እውነተኞቹ የመጽሐፍ ቅዱሶቹ እስራኤላውያን የተባሉት ኢትዮጵያውያን ከሆኑ የድሮዎቹ የእስራኤል  ነገሥታት እነ ዳዊት ሰሞሎን፣ ነብያትም፣ ሐዋርያትም እመቤታችንም ጌታችንንም  ሁሉ ፈረጆች ሳይሆኑ የአሁኖቹን የኢትዮጵያውያን መልክ ነበር ያላቸው አለባበሳቸውም፣  አኗኗራቸውም፣  ባህላቸውም የአሁኑን የኢትዮጵያውያን ባህል ነበር ማለት ነው። ይሄ ደግሞ ለአውሮፓውያን ለካቶሊክ  እና ፕሮቴስታንቱ ዓለም የሞት ሞት ነው...

ስለዚህ እነዚህ ሁለ ኃይላት የኅልውናቸው መሠረት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ  የኢትዮጵያን እውነታ እና ማንነት ለመቅበር ያላደረጉት ጥረት የለም ከነዛም መካከል በክብረ ነገሥት መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ታሪኮች ዋናኞቹ ናቸው።

በክብረ ነገሥት መጽሐፍ ላይ የሚነሱት ዋና ዋን ነጥቦች 
- የሰሎሞን ሥርወ መንግሥት መሠረት 
- የንግሥተ ሳባ እና የንጉሥ ሰሎሞን ጉዞ
- የቃል ኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ መምጣት
የመሳሰሉ ከላይ ደስ የሚሉ ሃሳቦች ያሉት ቢመስልም ከነዚህ ሃሳቦች  ከሥር አብረው የሚተላለፉት ነጥቦች ግን እነዚህን የመሳሰሉት ናቸው።  

1. ኢትዮጵያውያን የኦሪት ስርዓትን የሚፈጽሙት ወደ ሃገራቸው ከመጡት እስራኤላውያን ተምረውት እንደሆነ።

3. የኢትዮጵያውያን እግዚአብሔርን የማያውቁ ጣኦትን የሚያመኩ ሕዝቦች እንደነበሩ  አስረግጦ የሚናገር ነው።

2. የኢትዮጵያ ህዝቦች እና የእስራኤል ህዝብ ፈጽመው የተለያዩ ህዝቦች እንደሆኑ።  

እስኪ የነዚህን ነጥቦች እውነታነት በዝርዝር እንፈትሽ፦

1. ኢትዮጵያውያን የኦሪት ስርዓትን የሚፈጽሙት ወደ ሃገራቸው ከመጡት እስራኤላውያን ተምረውት እንደሆነ አስረግጦ የሚናገር ነው።

እንደ ክብረ ነገሥቱ ታሪክ መሠረት ኢትዮጵያ ህገ ኦሪትን የተቀበለችው ከሰሎሞን ጋር የመጡት 12,000 የእስራኤላውያን የበኩር ልጆች ምክንያት መሆኑን ለማስረዳት ይሞክራል።

ከላይ በጥቂቱ ለማንሳት እንደሞከረነው የኦሪት ህግጋት እና ስርአት የተሰጡት ለእስራኤላውያን ብቻ እና ብቻ ነው፣ ሌላው የዓለም ህዝብ ይህንን ህግ እና ስርዓት የመከተል ምንም ግዴታ የለበትም፣  የኦሪትን ህግጋት እና ስርዓት  የሚሰበኩ፣  ወደ ሌላው ህዝብ  የሚተላለፉ አይደሉም። የብሉይ ኪዳን መጻህፍትም ይህንን እውንት ይመሰክራሉ። 

ክብረ ነገሥት ግን የኢትዮጵያውያ የኦሪት ህግጋትን መከተል ምንጩ ከሚኒሊክ  ጋር በመጡት 12,000ዎቹ የበኩር ልጆች ምክንያት ነው ይላል።   ይሄ ፈጽሞ ከብሉይ መጻህፍት እና ሌሎች የታሪክ ተመራማሪዎች ግኝቶች ጋር የሚቃረን ነው።

እዚህ ላይ ብዙ ጥያቂዎች ሊነሱ ይችላል፦ 

* እስራኤላውያን በስደት በግብጽ፣ በባቢሎን እና በተለያዩ ሃገራት የሲኖሩ ሲሆን ኦሪትን አስተምረው አህዛብን ቀይረው አያውቁም እንደውም እነሱ ጣኦት ማምለክን ይማራሉ እንጂ፣ ወደ ኢትዮጵያም ሲመጡ ሊሆን የሚገባው ይሄ ነበር ።

* እስራኤላውያን ለ4,500 በብሉይ ዘመን ሲኖሩ፣ የእስራኤልን ባህል ተምረው   ወደነሱ ማህበረሰብ የተቀላቀሉ በጣም ጥቂት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ብቻ ናቸው (ረዓብ ፣ ሩት እና ኬጢያዊው ኦርዮ ናቸው)፣ ሙሉ ማህበረሰቦችን ቀይረው አያውቁም።

* 12000 ሰዎች እስራኤላውያን መጥተው ከሆነ የራሳቸውን ኦሪት እራሳቸው ይከተሉታል እንጂ ለሌላው ኢትዮጵያዊ አያስተምሩም ነበር  ለምሳሌ ግርዛት ለአብርሃም ዘር የተሰጠ ነው ታዲያ ኢትዮጵያውያን የአብርሃም ዘር ሳይሆኑ ቢገረዙ ባይገረዙ ምን ያደረግላቸዋል?  የሚበሉ እና የማይበሉ ነገሮችን መምረጥ እስራኤላዊ ላልሆኑት ለኢትዮጵያውያን ምን ያደርግላቸዋል? እስራኤል ከግብጽ የወጡበትን የፋሲካን በዓል ማክበር ለኢትዮጵያውያን ምናቸው ነው?     

* 12000 ሰዎች እንዴት የአንድን ሃገር ማህበረሰብ ልማድ እና ባህል ሙሉ ለሙሉ ሊቀይሩ ይችላሉ? 

* ኢትዮጵያውያን በዚህ መልኩ ኦሪትን ከተማሩ ቀድሞ ከነበራቸው የጣኦት አምልኮ ጋር ቀላቅለው ሲፈጽሙት ይታያል እንጂ ሙሉ ለሙሉ የቀድሞውን ትተው ኦሪትን ብቻ ሲፈጽሙ አይገኙም ነበር።

* ኢትዮጵያውያን 12000 ሰዎች ኦሪትን ተማሩ ካልንም ከላይ ከላይ ያሉትን ዋና ዋና  ህግጋት ይማራሉ እንጂ  በባህላቸው ውስጥ ስር በሰደደ መልኩ  አይማሩም አይፈጽሙትም ነበር... 

ዋና ዋናዎቹን የኦሪትን ህግጋት እና ስርዓትን  (ታቦተ ጽዮን ፣ የኦሪት  መጻህፍት መኖር፣ የሰንበት አከባበር ፣ የሚበሉ እና የማይበሉ እንስሳት መለየት ፣ ግርዛት ፣ የበዓላት አከባበር፣ የቤተ ክህነት መገልገያ እቃዎች እና ስርዓት፣ የዜማ መሳሪያዎች (በገና ማሲንቆ)፣ )  ሁሉ ትተን  ጥቃቅን የኦሪት እና የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማዶች በኢትዮጵያውያን ባህል ምን ያህል  ስር የሰደዱ እንደሆነ እንመልከት።

የዮፍታሄ ታሪክ እና ያአሸንዳ ባህል መገናኝት፣  እስራኤላውያን ላልሆኑት ኢትዮጵያውያን ይሄንን በዓል ማክበር ምን ያደርግላቸዋል የራሳቸው ታሪክ ካልሆነ በስተቀር?

ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል። በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ  እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ስለሆነ ይህን ታሪክ ለማሰብም ጉልባን እና ንፍሮ በኢትዮጵያውያን ባህል የተለመደ ነው፣

የራሳቸው ታሪክ ካልሆነ  ኢትዮጵያውያን ይሄንን መዘከር ምን ያደርግላቸዋል?

በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው እስከ ጥቃቅኑ ስርዓት  ድረስ መነሻው ብሉይ ኪዳን ነው።፣

ጥቃቅኑ የኢትዮጵያውያን ባህል መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንደሆነ  የሚያስረዳን በመጽሐፈ አክሲማሮስ ላይ አዳም ሄዋን ባሳሳተችው ጊዜ እንጨት አንስቶ አማታለሁ ሲል ዘላ ከአትክልት ውስጥ ተደበቀች እሱም ተከትሎ ገብቶ አልመታትም... ይሄ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በኢትዮጵያውያን ዘንድ አስካሁን ልምድ ሆኖ አለ ባል እና ሚስት  ሲጣሉ ባል ሊማታ ሲል ሚስት ወደ ማጀት ከገባች ባል ተከትሎ ገብቶ አይማታም ይሄም ልምድ ሆኖ እስካሁን አለ።

በተመሳሳይም የኢትዮጵያውያን ባህል የሆነው፣  ሰው መንገድ ሲሄድ መሸኘት መገኛው ከመጸሕፍ ቅዱስ አዳም ከገነት ሲሰደድ አአዋፍ እና አንስሳት ሸኝተውት እንደተመለሱ በማስታወስ ነው። 

እነደነዚህ አይነት በኢትዮጵያውያን ዘንድ በጣም ስር የሰደዱ መጸሕፍ ቅዱሳዊ ባህሎች ምንጫቸው  ቀድሞም የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት  ኦሪትን እና መጽሐፍ ቅዱስን የተሰጡት እውነተኞቹ እስራኤል ሰልሆነ ነው እንጂ  ከውጪ የመጡ ጥቂት ሰዎች የሚያስተምሩት ትምህርት የተኝኙ አንዳልሆኑ ማረጋገጥ ይቻላል።

እኛ ኢትዮጵያውያን የጥንቶቹ እስራኤላውያን መሆናችንን  በዐይን የሚታይ፣  በእጅ የሚዳሰስ፣ በመጻህፍት የሚመሰከር፣ በታሪክ የሚረጋገጥ እውነት ኖሮን ሳለ... እነዚህ ፈረንጆቹ  ሱፋቸውን ገድግደው ይመጡና አንድ የታሪክ ማስረጃ ሳይኖራቸው እኛ ነን የጥንቶቹ እስራኤል ሲሉን አዎ ብለ እንቀበላልን።

ሌላው ትልቅ ማስረጃ በኢትዮጵያ የሚገኙት ቤተ እስራኤላውያን ናቸው...  ቤተ እስራኤላውያን በቀጥታ በዘር እስራኤላዊ እንደሆኑ ሁለም የሚያምነው ሲሆን እነዚህን  ሰዎች  በመልክ፣ በአለባበስ ፣ በቋንቋ ከሌላው ኢትዮጵያዊ የሚለያቸው ነገር ሳይኖር እነሱ በዘር እስራኤላዊ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ እስራኤላዊ የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም። 

በታሪክም ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልክ እንደ አሁኖቹ ቤተ እስራኤላውያን በኦሪት ብቻ በመከተል  ሲኖር የነበረው... ክርስትና ከገባ ቡሃላ ግን ክርስትናን ያልተቀበሉት ቤተ እስራኤል ተብለው ሲጠሩ ፣ ክርስትናን የተቀበሉት ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ተብለው መጠራት ጀመሩ እንጂ ቤተ እራኤላውያን ከሌላው ክርስትናን ከተቀበለው ህዝብ ጋር ምንም አይነት የዘር ልዩነት የላቸውም።

ከላይ ካየናቸው ተጨማሪ በእስራኤላውያን ዘንድ ብቻ የሚፈጸሙ ሌሎች ህዝቦች ተምረው ሊፈጽሟቸው ከማይችሏቸው ልምዶች እና ባህሎች መካከል።

የተጣላ ሰውን ለማስታረቅ እና  ለትዳር  ሽማግሌዎሽን መላክ መነሻው ሥላሴ ወደ አብርሃም ቤት የመግባታቸው ነው። ይሄም ልማድ በኢትዮያውያን ዘንድ የተለመደ በአሁኖቹ የሃተኞቹ እስራኤላውያን የሌለ ነው፣ ይሄም የመጽሐፍ ቅዱሱ ታሪክ የኢትዮጵያውያን እንጂ የፈረንጆቹ እንዳይደለ ያስረዳልናል።

ብዙ ኢትዮጵያውያን ከእመቤታችን ቀጥሎ ለቅዱስ ሚካኤል ጥልቅ የሆነ ፍቅር እና አክብሮት አላቸው ይሄ አክብሮት ከባዶ የመነጨ ሳይሆነ በጥንት ጊዜ  ለእስራኤል ጠባቂ ሆኖ የተሾመው እስራኤልንም ከጠላት ሲጠብቅ የኖረ መልአክ በመሆኑ ያ ታሪክ በህዝቡ ውስጥ ውስጥ በመኖሩ  የተነሳ ነው... 

አሁን እይሁድ ነን የሚሉትን ፈረንጆች እንኳን በወርሃዊ እና በዓመታዊ በዓላት ሊያከብሩት ቀርቶ ስሙን እራሱ አያውቁትም።  ይሄ የሚያሳየው የጥንቱ የእራኤል ባህል የአሁኖቹ ኢትዮጵያውያን ባህል መሆኑን እንጂ የፈረንጆቹ እንዳልሆነ ነው።

ብዙ ኢትዮጵያውያን ከእመቤታችን ቀጥሎ ለቅዱስ ሚካኤል ጥልቅ የሆነ ፍቅር እና አክብሮት አላቸው ይሄ አክብሮት ከባዶ የመነጨ ሳይሆነ በጥንት ጊዜ  ለእስራኤል ጠባቂ ሆኖ የተሾመው እስራኤልንም ከጠላት ሲጠብቅ የኖረ መልአክ በመሆኑ ያ ታሪክ በህዝቡ ውስጥ ውስጥ በመኖሩ  የተነሳ ነው... 

አሁን እይሁድ ነን የሚሉትን ፈረንጆች እንኳን በወርሃዊ እና በዓመታዊ በዓላት ሊያከብሩት ቀርቶ ስሙን እራሱ አያውቁትም።  ይሄ የሚያሳየው የጥንቱ የእራኤል ባህል የአሁኖቹ ኢትዮጵያውያን ባህል መሆኑን እንጂ የፈረንጆቹ እንዳልሆነ ነው።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment