የነፋሳት አይነትና መውጫ መስኮቶች.... የምድር አብዮት...

✍ ይታገሡ በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር | ሰላቢ እጆች

እውን ከዋክብት፣ ጨረቃ፣ ፀሐይ ከሰው ስነ-ተፈጥሮ ጋር ግኑኙነት አላቸውን ታላቁ ሄኖክ #በጥንት_ብራናው ምን እውነት ይነገርናል!?

በአንድ ወቅት #ወሎ አካባቢ አንድ የጥንት ድንቅ ገዳም አቅንቼ ታላቁን የሄኖክን ሙሉ ይዘት ያለው ብራናን ተመልክቸ እጂጉን ተገርምኩ።

ብዙወቻችን ታላቁ ሄኖክን ከስም በዘለለ ስለተናገራቸው ድንቅ እውቀቶችና ሚስጥራዊ የአለምም አመሰራረት የሰማይ ጠፈር መመላለስ የፀሐይና የከዋክብት መዎጫና መግቢያ የወቅትና ወራት መለዋወጥ ተፈጥሮአዊ በሆነ ቀመር መለየት የፀሐይ ኡደት የጨርቃን ምልዓትና ሕፀፅ የፀሐይና የጨረቃ ግርዶሽ በምን ሁኔታ ይከሰታል በምን ወቅትና ጊዜስ!? የነፋሳት አይነት!? መውጫ መስኮቶቹ  የመከራና የሰላም ነፋስ አነፋፈስ ጊዜ ወቅት? የከዋክብት ምግብና የጠፈር ድምቀት ከወራትና አዝማኑ ጋር ያለውን ግኑኙነት እጂግ በሚደነቅና ልዩ በሆነ አገላለጽ ያስረዳል። 

ይህ ብቻ አይደለም በዓመት ውስጥ ስንት ዕለታት እንዳሉ የምናውቅበት ጨረቃ ከፀሐይ በምን ያህል ቀን ቀድማ ዓመቷን እንደምትጨርስ የሌሊቱ ማጠር እና መርዘም በፀሐይ መንገድ ተለይቶ እያንዳንዷን ዕለት ምን ያህል የመዓልትና የሌሊት ስፍር ስዓት እንዳላት በመግለጥ የአመቱን ወራቱን ወቅቶችን ፍንትው አድእጎ ያስረዳል። በየትኛው ወርና እለት መዓልቱ የሌሊቱ እጥፍ ወይም ግማሽ ይሆናል እንዲሁም መች ይተካከላሉ በአመቱ የመጀመርያው ወር የትኛው ነው!? የፀሐይና ጨረቃ ልዩ ክስተት፤ ፈለኮች ስለ ዘመናት መገባደድ እና እለተ ምጻዕት መድርስ የሚሰጡት መልክት በዝርዝር ያስረዳል። 

ይህ ድንቅ ሰው ብዙ የአለም ሚስጥሮችን የፈታው ድንቁ መጻህፉ ሙሉ በግዕዝ ብራና ተቀምጦ ጥቂት ቦታወች ይገኛል። 

ስለ ቅዱሳን መልእክት እና ስለ ወደቁት ኔፍሊሞች የሰው ልጂ ጉዞው ከአዳም እስከ ዕለተ ምፅአት እንዲሁም ስለ ወንዞች ተራሮች ዕፅዋቶች እና እንስሳት አራዊት የስነ ፈለክና ኅዋ ምስጢራትንም ከአመታዊ ጉዞአቸው ጋር የሚገልጥ አለም የሚፈልገው  መጻሕፍ ነው። 

ታድያ ይህ ድንቅ ሰው ባስቀመጠልን ድንቅ ቀመር ተነስተው በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ሰዎች በመነፈስ ቅዱስ ገላጭነት ይህንን አቡሻህር(አቡሻክር) የሚለውን እወቀት ይዘዋል አሁን በዘመናችንም በጣም ጥቂት በገዳማት የሚኖሩ አዋቂወች ኡሉ። 

ፈለኮች ለበርካታ ፍጥረቶች መኖር ወሳኝ ናቸው ሰወች እንዲንቀሳቀሱ የደም ዝውውራችን እንዲሳለጥ እጽዋቶች ፍሬ እንዲያፈሩ ዝናማት እንዲወረዱ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች ሃሪኬን ኤሊኖ ሱናዊ የምድር መናወጥ ጎርፍ መብረቅ ሁሉ እንዲረጉና እና በምድር ላይ ጉዳት እንዳያደረሱ የፈለኮች ሚና ለምድር የተሰጣት የአምላክ ስጦታ ነው። 

#ታድያ ምድር አብዪተኛ ስትሆን በሰማይ ያሉ ፈለኮች ቅርጽና ስርአተ መዋቅራቸውን ያዛባሉ ሰማያትን ይለጉማሉ ወይ ጎርፍ አድረገው ያጠለቀልቃሉ ሱናሚ ተከስቶ ምድር ትናወጣለች #ዋዕይ መከራ ርሀብ ችግር ጥም እና ስደት ይመጣል...

ሰማያት ይነገራ ስብሃት እግዚአብሔር እንዲል ዳዊት ከዋክብት እና የጨረቃን ቀመር በወጉ የተረዳ ሊቅ ሰውች ብዙ ሁነቶችን ፀሐይና ጨረቃን ከዋክብትን ተመልክተው መተንበይ ይችላል።
ብዙ ጊዜ እኒህ ነገሮች ወደ አልተፈለገ አላማ ዙረው መሰግላን የሚባሉ ባለ ጨሌ ሆዳደር ጠንቋዮች የሰውን እድል ፈንታ እና እጣ ፈንታ ለመናገር ይዳዳቸዋል። 

በዚህም ምክኒያት ይህንን የመሰለ ቀመር እና እውቀት ሊቃውንቱ ወይ ለሚወዱት አስተምረው ይሞታሉ ወይ ደግሞ ቀብረዉት ያልፋሉ።

የዚህ ቀመር ልኬታውን በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው  የሚመጣውን ዘመኑን በሚገባ የሚያወቁ ሊቃውንት ቀና ብለው ሰማይን ያነባሉ ነብይ እንዳይባሉ ይህ የነብያት ስራ ሳይሆን በእውቀትና በጥበብ መራቀቅ ነው።  

ለዚህም ምስክር የሚሆነው አለም ላይ ያህል ሜትሮሎጂስቶች የሚተነብዩትን ሳይንሳዊ ትንበያ መሰረት ተደርጎ የአየር በረራወች ይቋረጣሉ፤ የተገደበ እንቅስቃሴ ይኖራል፤ ለሚመጣው ዝናባማ ሆነ ድርቅ በብሄራዊ የአገር አድን  ራሳቸውን ያዘጋጃሉ። 
የከባድ አውሎ ነፍስ መምጣት ሲተነብዩ  የአስትሮይዶች ምድር ይመታል የሚል ትንበያ ሲያሰራጩ የጨረቃ እና የፀሐይ ግርዶች ይሆናል ሲሉስ ትንበያ አይደለም ታድያ!? የእነሱ ልክ ሁኖ የእኛ ሊቃውንት ስህተት የሚሆንበት ምክኒያቱ ምንድን ነው!?

#እኛ_ባለነበት በዚህ ዘመን ዝናባት የሚያወረዱና  የሚያዘንቡ ሰወችን ገፍተን በሀገር አቀፍ ደረጃ ደመናን አበልጸገን ዝናብ አዘንብን የሚሉት የምንቀበልበትስ ምክኒያት ምንድን ነው!?
ይህ ድንቅ መጻህፍ በዋናነት ምድር ላይ የሚነቀሳቀሱ አራት አበይት ከዋክብት በአመት ውስት ጊዜያቸውን ጠብቀው ይወጣሉ።

አንዱ ኮከብ 91 ቀይ ያበራል ማለት ነው ታድያ እኒህን በደንብ የተረዳና ያወቀ ሰው ስለ ተፈጥሮ ለመረዳት እና ለመናገር አያዳግተውም።

እኒህ ከዋክብት #ምልክኤል(ከመጋቢት መጀመርያ እስከ ግንቦት መጨረሻ ያበራል) ሊቃውንቱ #ተመዓኒና ፀሓይ ይሉታል፤ #ሕልመልመሌክ ብሩኅ ፀሐይ(ከሰኔ 1 እስከ ነሐሴ መጨረሻ ነው)  #ምልኤል(ከመስከረም መባቻ እስከ ኅዳር መጨረሻ ያበራል)  እና #ናርኤል ( ከታህሳስ 1 እስከ የካቲት መጨረሻ ያበራል) ። 

የእነዚህን ኡደት የተረዱ ሊቃውንት ልጆቻቸውን የሚወልዱትም በቀመር ቀምረው ዘመኑን እና ቀኑን አስተካክለው ነው። 
ሰሞኑን ጳጉሜ 2 ይታያል የተባለው የጨረቃ ግርዶሽ ብዙ መላምታዊ ንግርት አለው። 

የሚታየበት ክፍለ ብርሃን ሕልመልመሌክ በተባለው ኮከብ በሚመግበብት ጊዜ እና ወቅት ነው።

ይህ ዕለት የወደ ፊት ዕለት ምጻዕትም ናት ትባላለች። 
ታድያ በዚህ ዕለት የሚከውነው ነገር በቸልታ ማለፍ አለማስተዋል ነው።  

የሊቃውንቱን ለጊዜው ልተወው እና ይህ  ክስተት ምን ይናገር ይሆን ለሚሉት የጥንት አፈታሪክ መሳይ መላምቶች ከበጎም ከመጥፎም ይተረጉሙታል። 

ከየትኛውም ዘር ቀለም እምነት የተወጣጡ ሰወች ልዩነታቸውን ትተው አንድ የሚሆኑበት መልካም ዘመን ይመጣል፤ ምድርም ልጆቿን ትፈውሳለች። ሰወች እጅ ለእጅ ተያይዘው  በፍቅር ይሰበሰባሉ። የሰው ዘር ሁሉ ህዝብ ተብሎ የሚጠራበት ዘመን ሊመጣ ነው ይላሉ። 

ሌሎች ደግሞ በጣም ጨለማ የሆነ ሞት መከራ ችግር ርሃብ መሰደድ መጎሳቆል ድቅድቁ ጨለማ ባሻገር ተስፋ እንዳለ የሚያመለክት ነው ይላሉ። 

ግን አንድ እውነት አለ እሱም አለም አዲስ አሰራር ሂደትና ፈጥሮአዊ እንቅስቃሴን ታስተናግዳለች። ይህ ነገር  ሁንም ወደ ፊትም ተሶ የሚታይ  ይመስላል። 

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment