✍ መንግሥቱ ጎበዜ
ከዓመታት በፊት፣ ታላቁንና ባለራእዩን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕን በቅርብ የሚያውቃቸው አንድ ወዳጄ የብፁዕነታቸውን ጥልቅ ትዝብት አጋርቶኝ ነበር። ብፁዕነታቸው በወቅቱ፦ «የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የወደፊት ታላቅ ስጋት አክራሪ እስልምና ነው» ይሉ እንደነበር አጫውቶኛል።
እውነታውና አሁን በሀገራችን እየታየ ያለው ነባራዊ ሁኔታም ይህንኑ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። የውሃብያ እስልምና በሐሰት ትርክቶችና በአጥፊ ስልቶቹ አዲስ ሀገር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ለብዙዎቻችን ግልጽ እየሆነ መጥቷል። የውሃብያ ፊታውራሪዎች በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በየቀኑ በግልጽ የሚያራግቡት አጀንዳም ይህንንኑ ያረጋግጣል። ለዚህ ዓላማቸው ስኬት የሚጠቀሙባቸው ዋና ዋና ስልቶችን ቀጥሎ በተዘረዘሩት አምስት መንገዶች መገንዘብ ይቻላል፦
1. ታሪክን መበረዝና የሐሰት ትርክቶችን መፍጠር
የመጀመሪያው ስልት ዓለም በግልጽ የሚያውቀውን እውነተኛ የኢትዮጵያ ታሪክ በመበረዝ፣ አዲስ የፈጠራ ታሪክ የመጻፍና የማንበር ዓላማ ነው። ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆነው፣ «እስልምና ከክርስቶስ ልደት በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ ነበረ» የሚለውና «በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነጋሺ የሚባል የሰለመ ንጉሥ በኢትዮጵያ ነበር» የሚለው በድፍረት መጽሐፍ ተጽፎለት የቀረበው የልብ ወለድ ድርሰት ነው። በዚህ የፈጠራ ትርክት አማካኝነት በርካታ መጻሕፍት ተጽፈዋል፣ ተቋማት ተሰይመዋል፣ ድርጅቶችም ተዋቅረዋል።
2. አጥፊዎችንና ወራሪዎችን እንደ ጀግናና ቅዱስ አድርጎ መሳል
ሁለተኛው ስልት በኢትዮጵያ ታሪክ በውድመትና በአጥፊነታቸው የሚታወቁ ግለሰቦችን እንደ ጻድቅና ብሔራዊ ጀግና አድርጎ በትውልዱ አእምሮ ውስጥ ለመቅረጽ የሚደረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነው። ለዚህ ማሳያው፣ ኢትዮጵያንና የቤተክርስቲያኗን ማኅበረሰብ፣ መንፈሳዊና ታሪካዊ ቅርሶችን በ15 ዓመታት አሰቃቂ ጦርነት ያደቀቀውን አሕመድ ግራኝን እንደ ቅዱስና ጀግና አድርጎ የመሳል ስልት ነው።
ስለ አሕመድ ግራኝ አረመኔነትና አጥፊነት በዘመኑ የነበሩና ድርጊቱን እግር በእግር እየተከታተሉ ይጽፉ ከነበሩ የአረብ ጸሐፍት ሰነዶች ጭምር ማረጋገጥ ይቻላል። እሱን እንደ ጀግና መቁጠር ግን ዛሬም በአርሲና በተለያዩ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመውን ግድያና ጥፋት እንደ ትክክለኛ እርምጃ የመቁጠር ያህል አደገኛ አንድምታ አለው።
3. በቅዱሳን መካናት ላይ የይገባኛል ጥያቄ ማንሳት
ሦስተኛው ስልት በሀገራችን በሚታወቁ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳን መካናት ላይ የይገባኛል ጥያቄ በማቅረብ፣ በሕብረተሰቡ መካከል ክፍፍልና ግርግር መፍጠር እንዲሁም የመካናቱን ገጽታ ማበላሸት ነው።
ይህንን አካሄድ «የፍትሕ ጥያቄ» በሚል ስም በአክሱም ዙሪያ እየተካሄደ ካለው ከመስመር የወጣ እንቅስቃሴ መረዳት ይቻላል። ከዓመታት በፊትም ምንም ዓይነት ሙስሊም አማኝ በሌለበት በቅዱስ ላሊበላ ከተማ፣ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት እርድ በመፈጸምና የአንድን ግለሰብ ቤት ወደ መስጊድ ለመቀየር በድብቅ ተንቀሳቅሰው የነበረ ቢሆንም፣ በከተማው ማኅበረሰብ ንቃት ሊከሽፍ መቻሉ ይታወቃል።
4. የ«ተበዳይነት» የሐሰት ትርክት ማስፋፋት
አራተኛው ስልት እስልምና እና ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሁልጊዜም እንደተበደሉና የስቃይ ሰለባ እንደነበሩ አድርጎ መሳል ነው። ይህ ዓይነቱ የሐሰት ትርክት ለመጀመሪያ ጊዜ በስልታዊ መንገድ ጥቅም ላይ የዋለው ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሕዝቡን ከፋፍሎ ለመግዛት በነደፈው ስልት ነበር። ፋሺስቶች የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እና የሺህ ዘመናት ክርስቲያናዊ መንግሥቱን እንደ ጨቋኝ፣ ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ደግሞ እንደ ተጨቋኝ አድርገው ለመሳል ሰፊ ሥራ ሠርተዋል።
በመሠረቱ፣ በማንኛውም በሰነድ በተደገፈ የሀገሪቱ ታሪክ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሌሎችን እንደገፋችና እንደበደለች የሚያሳይ ማስረጃ የለም። እንዲያውም የሆነው የተገላቢጦሹ ነው፤ በተለያዩ ዘመናት ሙስሊሞች በውጭ ኃይሎች ጭምር በመታገዝ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጥቃት ሲፈጸሙ ቆይተዋል። ለዚህም በኦቶማን ቱርክ ታግዞ ወረራ የፈጸመውን አሕመድ ግራኝን፣ የግብፅን፣ የማኅዲስታውያንንና የሌሎችንም ተከታታይ የውድመት ታሪክ መጥቀስ ይቻላል።
5. አዲስ ታሪክና ማንነት የመፍጠር የመጨረሻ ግብ
ከላይ የተጠቀሱት የሐሰት ታሪክ መፈብረክ፣ አጥፊዎችን እንደ ጀግና መቁጠር፣ የቅዱሳን መካናትን ገጽታ ማበላሸትና የ«ተበዳይነት» ትርክትን ማስረጽ የመጨረሻ ውጤታቸው በኢትዮጵያ ላይ አዲስ ታሪክ መጻፍ፣ ያልነበረ ጀግና መውለድ፣ ነባር ምልክቶችንና ስያሜዎችን በአዲስ መቀየር እና በአጠቃላይ ከዚህ ቀደም ያልነበረች አዲስ ሀገር የመፍጠር ሂደት ነው። ይህ ሂደት በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፍጥነትና በተቀናጀ መንገድ እየተከናወነ ይገኛል።
ምን ይደረግ? (የመፍትሔ አቅጣጫዎች)
ውሃብያ አሁን እያደረገ ያለውን አደገኛ እንቅስቃሴ ዝም ብለን የምንመለከት ከሆነ እንደ ቤተክርስቲያንም እንደ ሀገርም ብዙ ውድ ዋጋ ሊያስከፍለን፣ አልፎ ተርፎም ሀገራችንን ራሷን ልንቀማ እንችላለን። ዝምታችን ይህንን አደገኛ መንገድ እንደ ትክክለኛ አካሄድ ሊያስቆጥረው ስለሚችል፣ በኦርቶዶክሳውያንእና በሌሎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በሀገራችን በተለይም በውሃብያ እየተከናወነ ያለውን የጥፋት ጉዞ በንቃት መከታተልና መመከት ይኖርብናል። ይህንን የተቀናጀና ስልታዊ ጥቃት ለመመከት የሚከተሉትን የመፍትሔ እርምጃዎች መውሰድ ይገባናል፦
• ታሪክ ተኮር የምርምርና የስነ-ጽሑፍ ስራዎች ላይ ማተኮር፦ የውሃብያ አራማጆች የሚያትሟቸውንና በመገናኛ ብዙኃን የሚያሰራጯቸውን የሐሰት ትርክቶች በጥናት በተደገፈ መልኩ በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የታሪክ ሰነዶች ውድቅ የሚያደርጉ መጻሕፍት፣ ጥናታዊ ጽሑፎችና በራሪ ወረቀቶችን በብዛት አሳትሞ ማሰራጨት አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ የአሕመድ ግራኝን የጥፋት ሥራ የሚገልጹትን፣ በራሳቸው በአረብ ጸሐፍት የተጻፉ መጻሕፍትን ወደ አማርኛና ወደ ተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በሰፊው በመተርጎም ለሕዝብ ማሰራጨት ተገቢ ይሆናል።
• መገናኛ ብዙኃንን ለግንዛቤ ማስጨበጫ መጠቀም፦ ወጣቱ ኦርቶዶክሳዊ ትውልድ ስሜታዊ በሆነ መንገድ ሳይሆን፣ የታሪክ እውነታዎችንና ማስረጃዎችን በመያዝ በማኅበራዊ ሚዲያ (TikTok, YouTube, Facebook ወዘተ) ላይ ንቃተ-ሕሊናን የማሳደግና ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መሥራት አለበት። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስር የሚገኙ መገናኛ ብዙኃንም አካሄዳቸውን አዘምነው በመሰል ወቅታዊ ሀገራዊና ታሪካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ተከታታይ መርሐ-ግብሮችን በትኩረት ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል።
• የቅዱሳን መካናትን ሕጋዊና ማኅበራዊ ከለላ ማጠናከር፦ እንደ አክሱም፣ ላሊበላና ሌሎች ታሪካዊ ገዳማትና አድባራት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎቻቸውና ታሪካዊ ይዘታቸው በሕግ ፊት በሚገባ ሊጠበቅና ሊደራጅ ይገባል። እግረ-መንገዱንም የአካባቢው ማሕበረሰብ በትክክል ምን እየሆነ እንዳለ ተረድቶ ራሱንና ቤተክርስቲያኑን ይጠብቅ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የማንቃትና የማደራጀት ስራ ሊሰራ ይገባል። በተለይም ደግሞ በየአካባቢው የሚገኘው የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ሁልጊዜም ንቁና የተደራጁ መሆን አለባቸው።
• ከነባሩና ሰላማዊው የሀገር በቀል እስልምና ጋር ተባብሮ መሥራት፦ የውሃብያ አስተምህሮ ከጥንቱ፣ ከኢትዮጵያዊውና ሰላማዊው የሱፊ እስልምና ጋርም ጭምር የሚጋጭ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። በመሆኑም የጋራ ሀገራችንን ሰላምና አብሮ መኖር ከሚፈልጉ ነባር ሙስሊሞች ጋር የሐሳብ ልውውጥ በማድረግና በመቀናጀት፣ የውሃብያን አክራሪነትና ሀገር የማፍረስ አጀንዳ በጋራ ማውገዝና መከላከል ይቻላል።
• በእውነተኛ የታሪክ እውቀት ላይ ተመስርቶ ትውልድን ማነጽ፦ ተወደደም ተጠላም አሁን የሀገርና የቤተክርስቲያን ትልቁ ፈተና ከታሪክ ማዛባት ጋር የተያያዘ ነው። በመሆኑም ወጣቶች ትክክለኛ ታሪካቸውን አውቀው ይታነጹ ዘንድ የቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርትን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ ማካተት፣ የስልጠና ሰነድ ማዘጋጀትና ልዩ ልዩ መርሐ-ግብሮችን በማዘጋጀት ወጣቱ ትውልድ እውነተኛ ማንነቱን እንዲረዳና እውነቱን ከሐሰት እንዲለይ ማድረግ ያስፈልጋል። ትውልዱ ታሪኩን ካወቀ በውሃብያ የሚነዛው የሐሰት ትርክት ቦታ አይኖረውም፤ ቤተክርስቲያኑንና ሀገሩን ለመጠበቅ ዘብ ይቆማል።
Blogger Comment
Facebook Comment