በጣም ኃያል ለሆኑት ምንሊክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ሰላምና ገናናነት ለርስዎ ይሁን። ዛሬ አንድ ንጉሣዊ ልግስና እንዲያደርጉ የምክር ቃላችንን ክርስቲያናዊና ንጉሣዊ ለሆነው ልብዎ ለመላክ አሰብን። ይህ ድል ብዙ ምርኮኞች በእጅዎ ጥሎልዎታል። እነዚህ ምርኮዎች በወጣትነት ዘመን የኑሮኣቸው ተስፋ በአበበበትና የብርሃን ጎህ በቀደደበት ሰዓት ካገራቸው ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው ይገኛሉ።
የነርሱ ምርኮ የግርማዊነትዎን ዝናና ገናናነት ምንም ሊያስፋፋው አይችልም። ይልቅ የምርኮ ዘመን ጊዜ በረዘመ መጠን በሺ የሚቆጠሩት ቤተሰቦቻቸው የመንፈስ ሀዘን እየበዛ ሄዷል። ከኢየሱስ ክርስቶስ በተቀበልነው የተቀደሰ መልእክት እንደ ልጆቻችን እንወዳቸዋለን።
ስለዚህ ያንድ ልብ በቅድስት ሥላሴ በተባረከችይቱ ድንግል ወይም ከዚህ ዓለም በሚወዱት ስም የሚያቀርብልዎትን ልመና ይቀበሉና ሳይዘገዩ ነፃነታቸውን ይስጡዋቸው። ኃያሉ ንጉሠ ነገሥት ሆይ ይኽን የደግነት ሥራ ባለመሥራት እምቢታዎን በዓለም ነገሥታት ዐይን ፊት አይግለፁ። በወንድማማችነት እና በሰብአዊ ተግባር አንፃር ያለው የጦር መብትዎ ምንድን ነው የዚህን ብድር ርኀሩኅ አባት እግዚአብሔር በብዙ ይክስዎታል። ይህን ክብር ያላትን ደብዳቤ በመንግሥትዎ ዜና መዋዕል ያስመዝግቧት።
እስከዚያው ለንጉሣዊ ቤተሰብ እግዚአብሔር በረከት እንዲያወርድ እንለምናለን።
ሮማ ቅዱስ ጴጥሮስ "ግንቦት ፲፩ ቀን፣ ፲፰፻፺፮ ዓ.ም በ፲፱ኛው ዘመነ ጵጵስና ተፃፈ»
ዋቢ፦ አፄ ምንሊክና የኢትዮጵያ አንድነት።
Blogger Comment
Facebook Comment