ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ እና በቀይ ባህር ስር የሚያልፉ የኢንተርኔት ኬብሎችን እቆርጣለው ስትል አስጠንቅቃለች። ከዓለም አቀፉ የኢንተርኔት ፍሰት ውስጥ ከ95 እስከ 97 በመቶ የሚሆነው በሳተላይት ሳይሆን በባህር ወለል ስር ከ1 እስከ 2 ሜትር ተቀብረው በሚገኙ የፋይበር ኦፕቲክስ ኬብሎች አማካኝነት የሚጓዝ ነው። የእርስዎ የባንክ ዝውውሮች፣ የአክሲዮን ግብይቶች፣ የክላውድ ኮምፒውቲንግ አገልግሎቶች እና እያንዳንዱን የፋይናንስ ገበያ የሚያስተሳስሩ የመረጃ ፍሰቶች በሙሉ በእነዚህ ኬብሎች ላይ የተመሰረቱ ናቸው። እነዚህ ሁሉ ኬብሎች የተዘረጉት በአሁኑ ወቅት የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኃይል (IRGC) ለመተላለፊያ ክፍያ የዩዋን (Yuan) ገንዘብ በሚሰበስብበት ጥልቀት በሌለው የባህር ወለል ላይ ነው።
እነዚህ ተራ ክልላዊ መስመሮች አይደሉም፤ እስያ፣ አውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካን የሚያገናኙ የዓለም አቀፉ ዲጂታል ንግድ የጀርባ አጥንቶች ናቸው።
የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኃይል (IRGC) መጋቢት 28 ቀን ባወጣው መግለጫ፦ “ጥቃቱ (Aggression) የሚቀጥል ከሆነ በሆርሙዝ እና በቀይ ባህር ያሉ ስልታዊ መሠረተ ልማቶች አይማሩም” ብሏል።
እስካሁን የተቆረጠ ኬብል የለም። ጎግል (Google) እና ሜታ (Meta) የመረጃ መስመሮቻቸውን የመቀየር (Rerouting) የጥንቃቄ እርምጃዎችን ወስደዋል። ስጋቱ እንደ ያልተመጣጠነ (Asymmetric) ምልክት ተዓማኒ ቢሆንም፣ በተግባር ላይ ማዋሉ ግን ከፍተኛ አደጋ ያለውና ምናልባትም "የማስፈራሪያ ፉከራ" (Bluff) ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም፦
በ2008 በግብፅ የባህር ዳርቻ ስምንት ኬብሎች ተቆርጠው ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ አውሮፓ የሚሄደው የኢንተርኔት ፍሰት ከ70 እስከ 80 በመቶ ተቋርጦ ነበር። ጥገናውም ከ3 እስከ 8 ሳምንታት ወስዷል። በ2024 ደግሞ ከሁቲዎች ጋር በተያያዘ የመርከብ መልሕቅ በመጎተቱ አራት ኬብሎች ተጎድተው ጥገናው ወራትን ፈጅቷል። ሁለቱም ክስተቶች በአጋጣሚ የተከሰቱ ናቸው። ሆን ተብሎ በመንግሥት የሚደገፍ መጠነ ሰፊ የኬብል ማውደም እርምጃ እስካሁን ተከስቶ አያውቅም፤ ምክንያቱም ውጤቱ ለሁሉም ወገን አውዳሚ ነው። የኢራን የኢንተርኔት ግንኙነትም በእነዚህ ኬብሎች ላይ የተመሰረተ ከመሆኑም በላይ፣ ማንኛውም ኬብል ቢቆረጥ በቀጠናው የሚገኙ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ እና የፈረንሳይ የባህር ኃይሎች አፋጣኝ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወስዱ ምክንያት ይሆናል።
የስታርሊንክ የባህር ላይ አገልግሎት (Starlink Maritime) ቀድሞውኑ የሆርሙዝ ሰርጥን በሚዘልሉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ተገጥሟል። ዋና ዋና የመርከብ ድርጅቶችም ፈጣን የሳተላይት ኢንተርኔት በመጠቀም ላይ ናቸው። ብሉምበርግ (Bloomberg) እንደዘገበው፣ ስፔስ ኤክስ (SpaceX) በዚህ ሳምንት የስታርሊንክን የአክሲዮን መሸጫ ሰነድ (IPO) ያቀርባል፤ ይህም በሰኔ ወር የኩባንያውን ዋጋ ከ1.5 እስከ 1.75 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ማለት ኬብሎች ስጋት ላይ በወደቁበት የጦርነት ወቅት የእሱ ምርት ብቸኛ አማራጭ ሆኖ እየቀረበ ነው።
20% የዓለም ነዳጅ፣ 20% የተፈጥሮ ጋዝ እና አንድ ሦስተኛ የሂሊየም ጋዝ የሚጓጓዝበት ይኸው ሰርጥ፣ 95% የዓለምን የመረጃ ፍሰትም ይሸከማል። ነዳጅ፣ ጋዝ፣ ሂሊየም፣ ሴሚኮንዳክተሮች፣ ማዳበሪያ፣ የኢንተርኔት ፍሰት እና የዩዋን ክፍያዎች በሙሉ በኢራን እና በኦማን መካከል ባለው ባለ 39 ኪሎ ሜትር የውሃ መስመር ውስጥ ያልፋሉ።
አንድ ወሳኝ መተላለፊያ (Chokepoint)፤ ሁሉንም የዓለም የኢኮኖሚ ዘርፎች የያዘ። ገበያው ገና የዚህን ስጋት ስፋት አልተገነዘበውም።
ምንጭ፦ ኢትዮ አዲስ
Blogger Comment
Facebook Comment