ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን አባቶች እና በርካታ የምእራባውያን የsigil ሰዎች ሌዋታን እና ብሄሞት የተባሉ ሁለት ዘንዶዎች ዓለምን ከበው እንደሚገኙ የሚናገሩ ሲሆን ከስር የምንመለከተው ስእልም ዘንዶዎች የሚወክል ነው፡፡ እነዚህ ምድራችንን ከበው ይገኛሉ ተብሎ የሚነገርላቸው የሌዋታን እና ብሄሞት ዘንዶዎች ምስል በበርካታ የኢትዮጵያውያን የብራና መጽሀፍት በአረቦች አስተምህሮት እንዲሁም በምእራባውያንም ጥንታዊ መጽሃፍቶች ላይ ይገኛል።
ሌዋታን በባህር በስተግራ በኩል የተጋደመችው እንስት ነች።
ብሔሞት በየብስ በስተቀኝ በኩል ተጋድሞ ምድርን የከበበ ተባዕት ነው።
ሁለቱም ዘንዶ መሳይ ፍጥረታት ክብ ሰርተው አፋቸው ጅራታቸውን ይዞ (Anti clock wise) የተሳሰሩ ሲሆን...የተገናኙ ዕለት ዓለም ፍፃሜዋ ይሆናል ተብሎ ይነገራል።
ይህም ንግርት በኛ ጥንታዊ ሰነዶች ብቻ ሳይሆን በጥንታዊ ምህራባውያን፣ በህንድና በአረብ ታሪኮች ውሥጥ ተፅፎና በስዕል ተገልፆ ይገኛል።
የሰው ልጅ የሚኖርበት ምድር ለ፯ የተከፈለ ሲሆን ፩ ብሔሞት ፪ ሌዋታን ፫ የአራዊት መኖሪያ ፬ በርባኖስ ፭ እሳት ፮ በረዶ ፯ የሰው ልጅ መኖሪያ በሚል።
ብሔሞትና ሌዋታንም የኛን ምድር ፯ኛውን ክፍል የሰው መኖሪያ እንደ መቀነት ተጠምጥመው ይዘዋት ይገኛሉ።
አመጋገባቸው #በፀጉራቸው ሲሆን... ብሔሞት የየብስ ፍጥረታትን (በድን) ከሰው በስተቀር በፀጉሩ በኩል ይመገባል።
ሌዋታን የባህር ፍጥረታት (በድን) በፀጉሯ በኩል እየተመገበች ትኖራለች።
ስለ አኗኗሯቸውና ምን #ይመስላሉ የሚለውን እንደነ ሄኖክ፣ ዘርዓ ብሩክ፣ ዕዝራ ሱቱኤል፣ ገድለ ዑራኤል፣ የመሪራስ አማን በላይ መፅሐፍና አክሲማሮስ የተባለው የፍጥረታት መፅሐፍ ላይም ተገልፆ ይገኛል።
ዓለም ሲፈጠር የተፈጠሩ የሐሙስ ፍጥረታት ናቸው።
አፍ'ለአፍ የገጠሙ ዕለት ተፍፃሜተ አለም እንደሆነ አባቶች ይናገራሉ።
በቅድስት ቤተክርስትያናችን አስተምህሮ መሰረት ብዙ አንድምታ አላቸው:: አንደኛው ከዚህ በፊት እንደነገርኳችሁ ምድር አራት መዓዘን ናት:: #ውሃ ምድርን ለሰባት ሲከፍላት መሬት አሁን ያለችበትን ክብ ቅርፅ ይዛለች:: እንደ መጸሐፈ አክሲማሮስ ምንጭነት ከሰባቱ የምድር ክፍል አንዱ ሌዋታን ነው:: ሁለተኛው ደግሞ ብሔሞት ነው:: #እነኝህ የምድር ክፍሎች ብዙ ያልተገለፁ ምስጢሮች አሏቸው:: ግዙፉና የሰው ልጅ በታሪኩ ያላያቸው ግዙፍ አራዊት እንደሚኖሩበት የብራና መዛግብት ይናገራሉ አበውም ይናገራሉ:: ከዚህ ጋር በተመሳሳይ AVATOR የተሰኘ ፊልም በጀምስ ካሜሮን ተሰርቶ መመልከታችን ይታወሳል::
እነኝህ የምድር ክፍሎች ከመሬት መጥፋት ጋር ተያይዞም የራሳቸው ንግርት አላቸው:: ቅዱሳን አባቶች እነኚህ ስድስቱ የምድር ክፍሎች ላይ የማዘዝ ስልጣን አላቸው:: ለምሳሌ ባህርና ንፋስ አንዱ የምድር ክፍል ነው:: ከዚህ የምድር ክፍል ንፋሳትን የማዘዝ ስልጣን አበው አላቸው:: #ስለዚህ_ለማሳጠር ያህል እነኚህ የሌዋታን እና ብሔሞት የምድር ክፍሎች በግዙፍ አራዊት ስለሚመሰሉና በነርሱ ላይ የሥልጣን የበላይነት ስላለን ብሎም ሌሎችንም ተያያዥ ምስጢሮችን ለማመሳጠር መሪ አባቶች ይይዙታል::
አንድም ደግሞ ሌዋታን እና ብሔሞት ምድርን ከበው የሚገኙ ግዙፍ ሁለት ዘንዶዎች እንደሆኑና ምድርን የማጥፋት ሀይል እንዳላቸው ነገር ግን በቅዱሳን አባቶች ተገዝተው እንደሚገኙ ይናገራሉ:: ግዝቱን ለማፅናት በተፈጥሮ ላይ ያለንን የገዥነት ሀይል ለማመሳጠርም ሌዋታን እና ብሔሞት ይጠለሰማሉ:: ብዙ ምስጢር አለው:: ሌላው ደሞ ይህ ጠልሰም በመጽሐፈ ቱላዳን እንዲሁም በሌሎች መፃሕፍት ውስጥ ይገኛል። ቱላዳን የተሰኘው መፅሐፍ የኢትዮጵያውያን አባት ታላቁ ሊቀ ሰማእት ቅዱስ ጊዮርጊስ አረማውያን ፈተና ሲያፀኑበት ፈተናውን ለመታገስ፣ ለመቋቋም፣ ለማሳለፍ እንዲሁም ታላላቅ ተአምራትን ለመፈፀም ወደ አምላኩ ያቀረበውን ፀሎትና ምስጋና እንዲሁም ሌሎች ጥበባትን የያዘ መንፈሳዊ መፅሐፍ ነው።
ጠልሰሙ ላይ የሚታዩት ሁለት ዘንዶዎች ሌዋትን እና ብሔሞት ይሰኛሉ። እነዚህ ሁለት ዘንዶዎች እስከ ምፅአት ምድርን ከበው እንደሚገኙ አባቶች ያስተምራሉ። በተጨማሪ ሌዋታን እና ብሔሞት ከምድራችን ጋር ስላላቸው ቁርኝት በመጽሐፈ አክሲማሮስና በስነፍጥረት አንድምታ መፅሐፍት ላይ ሰፊ እውቀት ስላለ እነርሱን እንድታነቡ እመክራለሁ።
በክብ ቅርፁ መሀል ያሉት የእግዚአብሔር እስከዛ ግን ይህን ምልክት ባያችሁ ቁጥር አትደናገጡ::
Blogger Comment
Facebook Comment