የጨለማው ድንኳን!!
የአራቱ_አለማት ምስጢር!!
በአዳም እጅ የተፃፈው መፀሀፈ-ራዝኤል!!
የአለማትን የሳይንሱን ዘረፍ የፈተነዉ ፍንጩ እንኳ ለመስጠት የሚያስቸግረዉ የጨለማ ድንኳን ምንድን ነዉ?
የጥንት መዛግብቶቻችን ስለ አለማት ምን ይላሉ ምን ብለዋል?
ብራናወቻችን አለም ተመራምሮ ስላልደረሰበት የሚስጥራት ሁሉ ሚስጥር ስለሆነዉ ስለ አለማት አፈጣጠርና አመሰራረት እንዲሁም ጥንተ ተፈጥሮ ምን ይላሉ?
ቀደምት ኢትዮጵያዉያን አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ጥበብና ሚስጥር ተመግበዉ በዘመኑ ለሳይንስ ለቴክኒዎሎጂ እንቆቅልሽ የሆነ ምስጥራዊ እዉቀቶችንና ጥበቦችን ትተዉልን አልፈዋል፡፡
እንዲሁም መለስ ብለን ታሪክን ስንመረምር፤ የተፃፉ ዶሴወችን ስናገላብጥ የብራና መፃሆፍቶቻችንን ስንመረምር አሁን ድረስ አለም ያልፈታቸዉ በረቀቀና በመጠቀ መልኩ ተብራርተዉና ተቀምጠዉ የሚገኙ አያሌ እዉቀቶች አሉ፡፡
ከነዚህም መካከል በምላትና በስፋት ተብራርቶ የምናገኛቸዉ የአለማት አፈጣጠር ሚስጥራትን ነዉ፡፡
በዚህም የተነሳ የሚስጥር ማህበረሰብ የሚባሉት የምዕራቡ አለም ነገስታት አለምን አንድአድርጎ ለመግዛት ካላቸዉ ጉጉት የተነሳ የአዳም ልጆች ከሰለጠኑባት ከኢትዮጵያ ምድር ዉስጥ የሚገኙትን የአራቱን አለማት አፈጣጠር ሚስጥራትና ጥበባት ለመበዝበዝ ያላሰቡት ሀሳብ ያለፈነቀሉትም ድንጋይ አልነበረም፡፡
ከሰማያዊዉ ህብረት ሃይላት ጋራ ህብረት መፍጠር የቻሉት ኢትዮጵያዉያን በየዘመኑ ከአራቱም አለማት ሚስጥራትና በመረዳታቸዉ በዘመናቸዉ ብርቱና ሀያል ሁነዉ ከማለፋቸዉ ባሻገር በመንፈሳዊ ፅናትና አቋማቸዉ ምክኒያት ወደ ሀገራቸወ ሲመጡ ለነበሩት ቅዱሳን ይህኔን ጥበባት አስተምረዋል፡፡
በምዕራባዉያን ሳይንስና ቴክንሎጂ የህዋ ምርምር ተቋማት ሚስጥራቸዉ አልፈታም ብለዉ ከተዘረዘሩት አንዱና ዋናዉ አለማት እና ይዘታቸው ሲሆን ስለዚህ ሚስጥራዊ ቦታ የተለያዩ ተመራማሪወች ሀሳባዊ መላምቶቻቸዉን አስቀምጠዋል ሁኖም ግን ከመላምታዊ ድምዳሜ የዘለለ አንዳችም ተጨባጭ ነገር ለመናገር አልቻሉም፡፡
ነገር ግን ቀደመት ኢትዮጵያዉያን ምሁራን በሚደንቅ እና በሚረቅ ትንታኔ አስቀምጠዉልን አልፈዋል፡፡
በአጠቃላይ አለማት 20 ሲሆኑ 14ቱ የእሳትና የምድር ሲሆኑ 6 ደግሞ የነፍስና የዉሃ ናቸዉ፡፡
የእሳት፣ የምድር፣ የነፋስ፣ እንዲሁም የዉሃ አለማት በመባል የሚታወቁ ጠቅለል ሲሉ አራት አለማት በመባል ይታወቃሉ፡፡
የእሳት አለማት የሚባሉት 9 ሲሆኑ የምድር አለማት ደግሞ 5 ናቸዉ፡፡
በ14 አለማት ዉስጥ የሚገኙት ፍጥረታት አንዳቸዉ ከአንዳቸዉ ግንኙነት የሚፈጠርባቸዉ ህቡዕ መንገዶች የሀይላቸዉ ማረፊያና ማደሪያ የሆኑ 12 የተለያዩ ቦታወች አሉ፡፡
እነዚህ የአለም ሀገራት Blackhole ብለዉ የሚጠሯቸዉ ከእነዚህ የተለያዩ ቦታወች 6ቱን ነዉ፡፡ የእሳት አለማት የሚባሉት እጂግ በሚያንፀባርቅና በነበልባል በተከበበ ከፍተኛ በሆነ የሃይል መጠን የሚገኙባቸዉ አለማት ናቸዉ፡፡
እኝህ 20 አለማት በዝርዝር እንደሚከተለዉ ተቀምጠዋል፡፡
ዘጠኝ የእሳት፣ አምስት የመሬት፣ አራት የውሃና ሁለት የንፋስ ዓለማት ናቸው።
ሀ. የእሳት ዓለም (በቁጥር 9 ዘጠኝ ናቸው) ከላይ ወደ ታች ሲቆጠሩ፦
፩/ ጽርሐ አርያም ( የእግዚአብሔር የምስጋናው አዳራሽ )
፪/ መንበረ መንግሥት/ስብሐት (የጌታ ዙፋን ያለባት)
፫/ ሰማይ ውዱድ (በአራቱ እንስሳዎች ክንፎች ላይ የተዘረጋ ሰማይ)
፬/ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት/ ዛዶር (በመጀመሪያ
ሳጥናኤል የተፈጠረባት በኋላም ከእሱ ተነጥቃ ለአዳም ልጆች የተሰጠች )
፭/ ኢዮር ( የአርባው ነገድ የመላእክት ከተማ )
፮/ ራማ ( የሠላሳው ነገድ የመላእክት ከተማ )
፯/ ኤረር ( የሠላሳው ነገድ የመላእክት ከተማ )
፰/ ምጽናተ ሰማይ (ባህረ እሳት)
፱/ ገሀነመ እሳት ናቸው።
#አዳም አባታችን በዚች እኛ በምንኖርባት ምድር ከመሰልጠኑ አስቀድሞ ምድር ለሰባት ተቆርሳ ወይንም ተከፍላ ነበር። ይህ ማለት እንግዲህ ከምድራችን ጋር ተመሳሳይ የሀይል የጊዜና የግዝፈት መጠን ያላቸው ነገር ግን የማናውቃቸው ስድስት የመሬት ክፍሎች አሉ። እነዚህ በስድስት የተከፈሉ ሰባት የምድር ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው:፡
1. መሬት(እኛ አሁን የምንገኝበት)
2. ብሔሞት
3. አራዊት ብቻ የሚገኙበት
4. እሳት ብቻ የሚገኝበት
5. በረድ ብቻ የሚገኝበት
6. ሌዋታን
7. በርባኖስ(ጨለማ ስፍራና እስርቤት)
ስነፍጥረት አንድምታ መፅሐፍ እንደሚያስረዳው ኢዮር ራማና ኤረር አሰራራቸዉ አራት ማዕዘን ሲሆን ሰባት የእሳት ቅፅርና ሰባት የሳት መጋረጃ የጋረዳቸዉ የሳት አለማት ናቸዉ፡፡ እኒህ አለማት ከሰዉ በተሰወረና ከመላእክት እንኳ በረቀቀ መልኩ ይገናኛሉ፡፡
አራት ማአዘን ቅርፅ ይዛ የተፈጠረችው ምድር ለሰባት ከተከፈለች በኃላ ውሃ መላት። አንዳቸውን ከአንዳቸው እንዲሁ ውሃ ለያቸው።
በዚህ የተነሳ መሬትን እኛ የምንገኝባትን ውሃ ከበባት በዚህ የተነሳ መሬት ክብ ናት የሚል ግንዛቤ ኖረን።
ከአራቱ አለማት አንዱ የሆነው መሬት አምስት ሰማያትን ጠቅልሎ ይዟል እነርሱም ሲዖል፣ መሬት፣ ብሔረ ብፁአን፣ ብሔረ ሕያዋን፣ ገነት ናቸው። ለዚህም ነው ገነት ምድር ላይ ናት የምትገኘው የሚባለው.....
ከነዚህ መካከል መሬት ከላይ እንዳየነው የሰው ልጅ በቅጡ ያልተረዳቸው ስድስት ክፍሎችን ይዛለች።
ከነዚህ አንዱ የሆነው በርባኖስ እስር ቤት ነው❗ በዚህ ጥልቅ እስርቤት ሁለት መቶዎቹ የስማዝያ ጭፍሮች ታስረዋል።
በአለመ እሳት ከሚገኙት ሶስቱ ማለትም ኢዮር፣ ራማና ኤረር፣ ቅዱሳን መላዕክት የሚኖሩባቸዉ የመላእክት ከተሞች ናቸዉ፡፡
ኢዮር በተሰኘዉ የመላእክት ከተማ 4 የመላእክት ነገዶች ይኖራሉ፡፡ እነርሱም፦ ኣጋእዝት፣ ኪሩቤል፣ ሱራፎፌል፣ እንዲሁም ሃይላት በመባል ይታወቃሉ፡፡
የኣጋእዝቱ መላክት አለቃ ሳጥናኤል ይባላል፡፡ እንዲሁም የኪሩቤል አለቃ ገፀ ሰብና ገፀ አንበሳ ሲሆን፣ የሱራፌል ደግሞ ገፀ ንስር ነዉ
የሃይላት ቅዱስ ሚካኤል ነዉ፡፡
በራማ ደግሞ 3 ነገደ መላእክት ይገኛሉ ስማቸዉም መናብርት፣ አርባብ፣ ስልጣናት ይባላሉ፡፡
የመናብረቱ አለቃ መላኩ ቅዱስ ሩፋኤል ሲሆን የአረባብ ደግሞ ቅዱስ ገብረኤል ነዉ፡፡ የስልጣናት ደግም ሱራኤል ነዉ፡፡
በሶስተኛዉ የእሳት አለም ዉስጥ የሚገኘዉ ኤረር ደግም 3 ነገደ መላዕክት ይገኛሉ፡፡ የነገዳቸዉም ስም መኳንት፣ ሊቃናትና፣ መላእክት ይባላሉ፡፡ የመኳንት አለቃ መላኩ ቅዱስ ሳዳካኤል ሲሆን የሊቃናት አለቃ ደግሞ መላኩ ቅዱስ ሳላታኤል ይባላል፡፡
የመላእክት ደግሞ መላኩ ቅዱስ አናንያኤል ነዉ፡፡ ምድራዊ ሰማያት ገነት ብሄረ ሄዋን፣ ብሄረ ብፁሀን፣ መሬትና፣ ሲኦል ናቸዉ፡፡
#እኛ የምንኖርባት ምድር በማእከል ስትገኝ ገነት በስተምስራቅ ብሄረ ሄዋን ደግሞ በስተሰሜን ብሄረ ብፁሀን እንዲሁ በስተደቡብ እንዲሁም ሲኦል በምዕራብ በኩል ነዉ፡፡ ቀደም ሲል ለመግለፅ እንደተሞከረዉ 14 የእሳት እና የምድር አለማት እርስ በርሳቸዉ ግንኙነት የሚፈጥሩባቸዉ እና የሀይላቸዉ ማደሪወች ከ12ቱ 6ቱ በርባኖስ ወይም blackhoel የአጋንንት የክፉ መናፍስት ማደሪያ ሲሆኑ፤ የቀሩት 6 ደግሞ ቅዱሳን መላእክት የሚወጡና የሚወረዱባቸዉ የሀይላቸዉ ማደሪያ ነዉ፡፡
ይህንን blackhole ለመረዳት በብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች እና መላምቶችን ተደርገዋል፡፡ ለዚህም የመጀመሪያዉን ፍንጭ ለመስጠት የሞከረዉ እዉቁ ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ነዉ፡፡ ይህንንም ምርምሩን ደግሞ E=mc2
በሚል ፎርሙላ ነዉ የብረሃንን ፍጥነት በመጠቀም የጊዜና የሰአት ግዝፈቱን ለማወቅ ሞክሯል፡፡ በዚህም የተነሳ ሳይንሳዊ ትንታኔወችን እንዲህ ሲሉ አስቀምጠዋል፡፡
ነገር ግን ከሳይንቲስቶች ንድፈ ሃሳብ በተሻለ መልኩ ታላቁ የሂወት መፀሀፍ በመባል የሚታወቀዉ ራዛኤል የተባለዉ የብራና መፃህፍ በሰፊዉ አስቀምጦታል፡፡
ይህ መፃህፍ በአራቱ ሰማያት ወይም አለማት ያለዉን የሀይል የጊዜና የግዝፈት ልዩነት ያስረዳል፡፡
ይህ ታላቅ መፅሐፍ የተፃፈዉ በአዳም ሲሆን አዳምን ያስተማሩት ሚስጥሩንም የገለጡለት በእሳት አለማት ዉስጥ የሚገኙ መላእክት ሲሆኑ አሁን ላይ የዚህ መፃህፍ መገኛ ከአዲስ አበባ 47 km እርቃ ከምትገኘዉ ቢሾፍቱ ደብረ ዘይት በታላቁ የረር ተራራ በሚገኙት ገዳማት በሚስጥረ ተጠብቆ እንደሚገኝ ቅዱሳን አባቶች ይናገራሉ፡፡ አዳም በገነትና በምድር ላይ ኑሩዋልእና፡፡
ስለዚህ ሰማያዊት በሆነችዉ ገነትና በምድር መሃከል የጊዜ የሃይል የግዝፈት ልዮነት አለ ማለትነዉ፡፡ ነገር ግን አዳም በገነትና በምድር ያለዉን የጊዜ ልዩነት አስማምቶ ይኖር ዘንድ መላኩ ቅዱስ ገብረኤልና መላኩ ቅዱስ ኡራኤል ጥበብን አስተማሩት፡፡
ለብዙ ሰወች ጥያቆ የሚሆነዉ አዳም 7 አመት በገነት ኖረ ከዛም በምድር 930 አመት ኖረ ጥያቄ የሚሆነዉ ግን በገነትና በምድር ላይ የጊዜ ልዮነት አለ ካልን ይህም ማለት አንደ ቀን በገነትና አንደ ቀን በምድር የሚኖራቸዉ የጊዜ ክፍተት ብዙ ሊሆን ይችላል፡፡
ስለዚህ አዳም በሰማይ 7 አመት ከኖረ በምድር የጊዜ ስሌት ላይ ስንት አመት ኖረ ማለት ነዉ❓❗
ከዚህ ጋ ልብ በሉልኝ በቅዱስ መፀህፍ ላይ በሰማይ 1 ቀን በምድር 1 ሺ አመት ነዉ ይላል፡፡
ይህም ማለት 7 አመት የአዳም የሰማይ ኑሮዉ በምድር ላይ ሲሰላ 7,365=2555, 2555 ቀናትን በሰማይ ኑሩዋል ማለት ነዉ ይህም በምድር የጊዜ ስሌት አዳም በገነት የኖረዉ 2555,1000=2555000 ቀናት ነው ነዉ፡፡ 2.5 ሚሊየን ቀናት በላይ ማለት እኮ ነው..... ይህ ማለት የዘመኑ የሳይንስ ምርምር time travel በጊዜ ውስጥ የመጓዝን ጥበብ አያሳየንም❓❗
በዚህ ሃይማኖታዊ ፍልስፍና ውስጥ በሌላ ጊዜ የምንገለጠዎ እጂግ ረቂቅ የእግዚአብሔር ስራ እንመለከታለን...❗
ስለዚህ ነጮች እንደሚሉት ምድር ከተፈጠረች ሚሊየን አመት ሁኗታል ማለት ያስችለናል???
ነገር ግን አዳም ገነት ላይ በኖረበት 7 አመትና በምድር ያለዉን የሃይል የጊዜና የግዝፈት መጠን አመጣጥኖ መኖር ችሏል ማለት ነዉ::
ስለዚህ አዳም ምድር ላይ ሲመጣ የግዝፈት መጠኑ 7 አመት እንዳሳለፈ ሰዉ እንጂ በርካታ ሚሊዮን አመታት እንዳሳለፈ ሰዉ ሁኖ ወደ ምድር አልመጣም የሚል መላምት ይሰጣል፡፡
ወደቀደመዉ ነገሬ ልመለስና ከላይ ከተመለከትናቸዉ 6ቱ BlacK hole(የጥልቁ ጨለማ ሀገር) እና 6ቱ white hole (የቅዱሳን መላእክት ሀገር) በአራቱም አለማት ዉስጥ ከሚገኙት ማለትም ከመሬት ከሳት ከዉሃና ከነፋስ አለማቱ ጋር የጊዜ የግዝፈት እና የሃይል ተፅኖ ዉጭ ነዉ፡፡ ለዚህም ይህ black hole በርባኖስ ብዙ አስደንጋጭ ክስተቶችን የሚያሳይ አስደናቂ ቦታ ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment