ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ
እንዲህ ያለው ሕገ ወጥነት ሀገራችንን ወደ ከፋ ችግር ለመክተት የታለመ አደገኛ እንቅስቃሴ ነው። ችግሩ የጥቂት ወሃቢያ አክራሪዎች ቅዠት ሳይሆን አሁን ስልጣን ላይ ተቀምጠው Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council የእስልምና ጉባዔውን የሚመሩ ሰዎችም መሆኑን እያየን ነው። በሀገሪቱ ሕግ ካለ ይህ ጉዳይ ትክክለኛ እርማት ይፈልጋል።
"መስቀል አደባባይ" የሚለውን ሕጋዊ ስም ወታደራዊው መንግሥት እንዳደረገው በጉልበት የመቀየር መብት ማን ሰጣቸው? በጎ ሕሊና ያላቸው ሙስሊም ወገኖቻችን ሁሉ እንዲህ ያለውን ለሀገር አንድነት የማይበጅ ተግባር እንደማይፈልጉት የታወቀ ነገር ቢሆንም ሕዝቡን ያልሆነ ፉክክር ውስጥ በመግባት የጠላትነት ስሜት እንዲፈጠር በማድረግ ላይ የሚገኙ አጉራ ዘለሎች መኖራቸው የታወቀ ነው::
ሀገራችን የጋራ ናት፣ ሃይማኖታችን ግን የየግላችን ነው። ሀገራችን ባለ ብዙ ቋንቋ እና ባለ ብዙ እምነት መሆኗን ሀገራችንን ለመጉዳት ለሚጠቀሙበት ጠላቶቻችን መጠቀሚያ በመሆን ላይ የሚገኙ ሰዎችና ተቋማት አደብ የሚገዙት መንግሥት ሕግ ማስከበር ሲችል ነው።
በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ማንነት የማቆርቆዝ (undermine የማድረግ) እንቅስቃሴ መዘዙ ብዙ ነው። መንግሥት ከጊዜያዊ የፖለቲካ ዓላማ ወጥቶ ነገሮችን በስፋት ለማየት አለመቻሉ ሁሌም ያስደንቀኛል። በተበላሽ የጎሳ ideology እንዴ በተበላሸ የእምነት አስተምህሮ መነሻ በማድረግ ቤተ ክርስቲያናችንን ለመጉዳት የሚሞክሩ ካድሬዎቹን መቆጣጠር አልቻለም። ጎምቱ ጎምቱ ባለ ሥልጣናቱም ከተራ የካድሬ አስተሳሰብ ወጥተው የሀገር መሪ መሆን አልቻሉም። ባገኙት አጋጣሚ "የሰበሩንን ሰበርናቸው" ከሚል ፉከራ አልወጡም።
ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበት እስልምና ካውንስሉ ከሕጋዊ የሀገሪቱ የቦታ መጠሪያዎች ወጥቶ ወደ መንደር ታሪክ እንዴት ሊገባ ቻለ? ካውንስሉን የሚመሩት እነ ሙጂብ አመኖና እነ አህመዲን ጀበል ናቸው? አቡበከር አሕመድም ለክርስቲያኑ ያለውን ትክክለኛ አመለካከት የገለጸው ዛሬ አለመሆኑን የምናውቅ እናውቃለን። ለብዙኃኑ ግን አሁን የገባው ይመስለኛል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሙስሊሞች እና የክርስቲያኖች አንድነት እንጂ ጠላትነት የለም። መኖርም የለበትም። ይህ ጠላትነት እንዲፈጠር የሚተጉትን ሁሉ በሕግ አምላክ የሚል አካል ግን ያስፈልጋል።
በሕግ አምላክ።
Blogger Comment
Facebook Comment