ዘር አጥፊዎቹ ባቢሎን የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች እና የግራኝ ዐቢይ አሕመድ አገዛዝ የሱዳንን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) ተዋጊዎች በድብቅ እያሰለጠኑ ነው
✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ አውታር
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሥልጠና ካምፕ መገንባቱን የሮይተርስ የምርመራ ዘገባ አሳየ።
የእርስ በስር ጦርነት ውስጥ ከምትገኘው ሱዳን ጋር በሚጎራበተው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የአማጺው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሥልጠና ካምፕ መገንባቱን ከምንጮች እና ከሳተላይት ምሥሎች ማረገጋጡን የዜና ወኪሉ ሮይተርስ አስታወቀ።
የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ሥልጠና ትሰጥበታለች በተባለው በዚህ ካምፕ ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ ምልምሎች ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ ምንጮች መናገራቸውንም የዜና ወኪሉ ዘግቧል።
ሮይተርስ ማክሰኞ የካቲት ፫/3 ፣ ፳፻፲፰/2018 ዓ.ም. ያወጣውን የምርመራ ዘገባ ያጠናቀረው የኢትዮጵያ መንግሥት እና የዲፕሎማቲክ ምንጮችን በመጠቀም እንደሆነ ጠቅሷል። ከኢትዮጵያ የደኅንነት ተቋም እና ከዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ የተገኙ የመረጃ ልውውጦች እንዲሁም ካምፑን የሚያሳዩ የሳተላይት ምሥሎችም በዘገባው ውስጥ ተካትተዋል።
የሮይተርስ ዘገባ እንደሚያመለክተው ከ፳፻፲፭/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከሱዳን ጦር ጋር እየተዋጋ ያለው አማጺ ኃይል ሥልጠና ይሰጥበታል የተባለው ካምፕ የሚገኘው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል "መንጌ" በተባለ ስፍራ ላይ ነው።
ካምፑ የሚገኝበት ስፍራ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን የሚያዋስን እንደሆነ እንዲሁም ከድንበር ያለው ርቀት ሰላሳ ሁለት/32 ኪሎ ሜትር እንደሆነም ዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
የሮይተርስ ዘገባ፤ "አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣንን ጨምሮ ስምንት ምንጮች፤ የተባበሩት አረብ ኤምራቶች የሰፈሩን ግንባታ በገንዘብ እንደደገፈች፣ እንዲሁም ለቦታው የወታደራዊ አሠልጣኞችን እና የሎጅስቲክስ ድጋፍ ማቅረቧን ገልጸዋል" ይላል።
ካለፈው ዓመት ሚያዝያ አንስቶ የደን ምንጠራ እንዲሁም የብረት ጣሪያ ያላቸው ሕንጻዎች መገንባታቸውን እንደተረዳ ዘገባው አመልክቷል። ጥቅምት ላይ ደግሞ ካምፑ ውስጥ ድንኳኖች መተከላቸው ተጠቅሷል።
ኅዳር ላይ የተነሱ የሳተላይት ምሥሎች ላይ ስድስት መቶ አርባ/640 ድንኳኖች መመልከቱን የጠቀሰው ሮይተርስ፤ ካምፑ በአጠቃላይ አስር ሺህ/10,000 ተዋጊዎችን የመያዝ አቅም እንዳለው የሚያሳይ የዲፕሎማቲክ መልዕክት ልውውጥ መመልከቱን ገልጿል።
በርካታ ላንድ ክሩዘር እና ከባድ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አሃዶች እንዲሁም የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አሠልጣኞች ጥር ላይ ወደ ካምፑ መግባታቸውንም ይህ ዲፕሎማሲያዊ መልዕክት ልውውጥ ጠቅሷል ተብሏል።
"ጥቅምት ላይ የኤሚሬቶች የሎጅስቲክስ ኩባንያ 'ጎሪካ ግሩፕ' አርማ ያለባቸው የጭነት መኪናዎች በአሶሳ ከተማ አድርገው ወደ ካምፑ ሲጓዙ መመልከታቸውን ሁለት ባለሥልጣናት ገልጸዋል" የሚለው ዘገባው ላይ ሰፍሯል።
ኅዳር ላይ ደግሞ አዲስ ምልምሎችን የያዙ መቶ ሃያ ስድስት/126 ተሽከርካሪዎች በቀናት ልዩነት ሲጓዙ የተመለከቱ ባለሥልጣናትን ማናገሩን የዜና ወኪሉ ጠቅሷል። ተሽከርካሪዎቹ እያንዳንዳቸው ከሃምሳ/50 እስከ ስልሳ/60 ተዋጊዎችን ይዘው እንደነበረም ዘገባው ያመለክታል።
በዚያው በኅዳር ወር የተነሳ የሳተላይት ምሥል ላይ ቢያንስ አስራ ስምንት/18 ትልቅ ተሽከርካሪዎች ካምፑ ውስጥ መታየታቸውን ሮይተርስ ገልጿል።
የሮይተርስ ትንታኔ እንደሚያመለክተው፤ የተሽከርካሪዎቹ መጠን፣ ቅርጽ እና ዲዛይን የፋሺስቱ ጋላ-ኦሮሞ እስላማዊ አገዛዝ ሠአራዊት እና አጋሮቹ ወታደሮችን ለማጓጓዝ ከሚጠቀሙባቸው ሞዴሎች ጋር ይመሳሰላሉ" ሲልም ዘገባው ላይ ጽፏል። ይሁን እንጂ እነዚህ ተሽከርካሪዎች በአሶሳ በኩል ሲያልፉ የታዩት ስለመሆናቸው በገለልተኝነት አለማጣራቱን አስረድቷል።
"ከኢትዮጵያ የደኅንነት አገልግሎት" የውስጥ ማስታወሻ ተገኘ የተባለ መረጃ ደግሞ አስከ ጥር ወር መጀመሪያ ድረስ አራት ሺህ ሦስት መቶ/ 4,300 የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ተዋጊዎች በስፍራው ወታደራዊ ሥልጠና እየወሰዱ እንደነበር አሳይቷል ተብሏል።
የተዋጊዎቹ "የሎጅስቲክስ እና የወታደራዊ አቅርቦት ትጥቅ የሚቀርበው በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ" እንደሆነ ከውስጥ ማስታወሻው መመልከቱን የዜና ወኪሉ አስታውቋል።
ሮይተርስ [የሥልጠና] ካምፑን የማቋቋም ኃላፊነትን የወሰደው የፋሺስቱ ጋላ-ኦሮሞ እስላማዊ አገዛዝ ሠአራዊት ደኅንነት መምሪያ ዋና ኃላፊ የሆነው ቆሻሻው 'ጄነራል' ጌታቸው ጉዲና መሆኑ በዘገባው ሰፍሯል።
አንድ የአገዛዙ ከፍተኛ ባለሥልጣን እንዲሁም አራት የዲፕሎማቲክ እና የደኅንነት ምንጮች ይህንኑ እንዳረጋገጡለትም የዜና ወኪሉ ገልጿል።
ሮይተርስ ከስድስት ባለሥልጣናት አገኘሁት ያለው መረጃ እንደሚያሳየው በካምፑ ውስጥ ከሚገኙት ምልምሎች ውስጥ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዜጎችም ካምፑ ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።
ሱዳን ውስጥ የተወሰኑ ግዛቶችን የሚቆጣጠረው አማጺው 'SPLM-N' ተዋጊዎችም ካምፑ ውስጥ እንደሚገኙ ዘገባው ላይ ተጠቅሷል። ቡድኑ ግን ኃይሎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛሉ መባሉን አስተባብሏል።
ሮይተርስ ካምፑ በሚገኝበት ስፍራ ላይ የሚደረገው ግንባታ በጥር ወርም መቀጠሉን ከሳተላይት ምሥሎች እና ከምንጮች ማረጋገጡን ዘግቧል።
እንደ ዜና ወኪሉ ዘገባ፤ ከካምፑ በሃምሳ ሦስት/53 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው አሶሳ አየር ማረፊያም ካለፈው ነሐሴ ጀምሮ አዲስ ግንባታዎች እየተከወኑለት ነው።
በአየር ማረፊያው የሚደረገው ግንባታ ስፍራው የድሮን ማዘዣ ማዕከል እንዲኖረው የሚያደርግ መሆኑ ካደረገው የሳተላይም ምሥል ምርመራ እንዲሁም ከአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን የተገኘ መረጃ መረዳቱን በዘገባው አካትቷል።
ሮይተርስ በምርመራው የደረሰባቸውን ግኝቶች በተመለከተ ከፋሺስቱ ጋላ-ኦሮሞ አገዛዝ እና ከሱዳን ጦር ኃይሎች መረጃ ለማግኘት ያደረጋቸው ሙከራዎች እንዳልተሳኩ ገልጿል።
Blogger Comment
Facebook Comment