መጽሐፈ መግረሬ ፀር ወይም በትርጉሙ "የጠላት መከላከያ" ይባላል! አያቶቻችን እንደ ዓድዋ ባሉ ውጊያዎች ላይ ተጠቅመውበታል።
ይህ መግረሬ-ፀር የተሰኘ ጥንታዊ መፅሀፍ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአስራ ሁለቱ ሐዋርያት የሰጣቸው ጠላትን መከላከያ ሰማያዊ ጥበብ ነው። የቀደሙት አባቶቻችን እነዚህን ሰማያዊ ጥበባት በመጠቀም ነበር እራሳቸውን ቤተሰባቸውን እንዲሁም የሀገርን ዳር ድንበር ከጠላት ይከላከሉ እና ይጠብቁ የነበረው። መጽሐፉ በሰይጣናዊ ኃይላት የሚመጡ ማንኛውም አይነት ጥቃቶችን መርታት የሚያስችሉ የእግዚአብሔር ስሞች የሰፈሩበት ነው። ይህና መሰል መፅሐፍት በፈረንሳይኛና በጀርመንኛ ቋንቋዎች በስፋት ተተርጉመዋል።
አባቶቻችን እኮ የጨለማው አለምን ገዢን ጨምረው እኮ ነው ዓድዋ ላይ ድል የነሱት።
አባቶቻችን እኮ ብርሀናዎቻቸውን በገናዎቻቸውን እና ዳዊታቸውን ይዘው እኮ ነው የዘመቱት! የጨለማውን የጥልቁን መንግሥት ከስራቸው ያንበረከኩት እኮ በግራና በቀኝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን እና የታላቁን ሠማእት የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦትን ይዘው ዘምተው እኮ ነው። ንቃተ ህሊናቸው ይህን ያህል የመጠቀ እኮ ነው። በስጋም በመንፈስም እኮ ነው ውጊያውን በድል ያጠናቀቁት። ለዛውም ሰባት መቶ ዘመናት ደም የተገበረለትን የበርሊኑን የጨለማ ገዢን ነው ከእግራቸው ስር ያንበረከኩት። ውጊያውን በስጋም በመንፈስም ነበር ድል የነሱት። ሰራዊታቸውን በስጋም በመንፈስም ነበር የመሩት!!!
Blogger Comment
Facebook Comment