ኢትዮጵያን የከዱት የዘመናችን ሔሮድሳውያን

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

😔 ላለፉት ሺህ አራት መቶ ዓመታት ሉሲፈራውያኑ በራችንን እያንኳኩ ሊገድሉን፣ እግዚአብሔር የሰጠንን ፀጋ ሁሉ ሊዘርፉን/ሊነጥቁን ብሎም ብኹርነታችንን ሊወርሱን ተግተው ይሠራሉ፣ የእኛዎቹ ልፍስፍስ 'ልሂቃን' ግን በፍጻሜ ዘመን፤ ከረባትና ሱፍ አጥልቀው፤ “ወልቃይት፣ ራያ ወዘተ እርስቴ!” እያሉ እርስበርስ ይተላለቃሉ። ልክ ሉሲፈራውያኑ ባቀዱላቸውና በሠሩላቸው መንገድ። ለመሆኑ 'ኦሮሞ' እና 'ትግራዋይ' የሚለውን የመከፋፈያና እራስን የማስኪያጂያ መጠሪያ ስም ሉሲፈራውያኑ እንደሰጡን ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?! አዎ! የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያን ሥርወ መንግስት ኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ሉሲፈራውያን አስወግደው ወኪሎቻቸውን ዙፋኑ ላይ ካወጧቸው በኋላ ነው እነዚህ መጠሪያዎች እና ግዕዝን የቀሙ ቋንቋዎች በሤራ የተፈጠሩት። አባቶቻችን እንዴት እንደሚያፍሩብንና እንደሚያዝኑብን ባወቅን!

ምዕራባውያኑ ኤዶማውያን እና ምስራቃውያኑ እስማኤላውያን የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያን ሕዝብ አጥብቀው እንደሚጠሉ ያለፈውም የዛሬውም ታሪክ በግልጽ አስተምሮናል፤ ግን ለመሆኑ “እንደ እስራኤል፣ ሕንድና ሩሲያ ያሉት መንግስታት ለምንድን ነው ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በመጨፍጨፍና በማስራብ ላይ ያለውን ፋሺስት ጋላ-ኦሮሞ እስላማዊ አገዛዝ የሚደግፉት?” ብሎ በግልጽና በድፍረት እራሱን የሚጠይቅ 'ኢትዮጵያዊ' ልሂቅ ሰምተን እናውቃለንን? እኔ እስካሁን ከዲያቆን ቢንያም ፍሬው በቀር ሰምቼ አላውቅም። ምክኒያታቸው? ችግራቸው?

በኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ መንፈስ ሥር ስለወደቁ አይደለምን?

👉 ነጠብጣቦቹን ለማገናኘት...

😇 ነቢዩ ዳንኤል፤ “እጁን በአገሮች ላይ ይዘረጋል፥ የግብጽም ምድር አታመልጥም። በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ፥ በከበረችም በግብጽ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል፤ የሊብያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይከተሉታል።”

ኢትዮጵያን የከዱት የዘመናችን ሔሮድሳውያን 'የኢትዮጵያ ሰዎች' የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹን ኤዶማውያኑን (የሰሜን ንጉሥ) እና እስማኤላውያኑን (የደቡብ ንጉሥ) ተከትለው እና ከጎናቸው ተሰልፈው በአክሱም ጽዮን ላይ መዝመታቸውን አየን አይደል?! ዛሬስ የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያን ወርቅና ብር በባቢሎን ኤሚራቶች በኩል እየዘረፉት አይደል? 

“ንጉሣዊ ድንኳኑንም በባሕርና በከበረው በቅዱስ ተራራ መካከል ይተክላል”

በባሕርና (ሜዲትራኒያን) በከበረው በቅዱስ ተራራ (የሞርያ ተራራ/የጽዮን ተራራ) መካከል የሚገኘው ቦታ ደግሞ ዛሬ የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ እነ ትራምፕ፣ ያሬድ ኩሽነር፣ ኢለን ማስክ እና ፒተር ቲል ሊገነቡትና ማዕከላቸው ሊያደርጉት የሚፈልጉት 'ጋዛ' አይደለምን?

'ጋዛ' የኢትዮጵያውያን ግዛት ነው! ይህ ትውልድ 'ወልቃይት ርስቴ' ማለቱን ትቶ፤ 'ጋዛ ርስቴ' ማለት ነበረበት፤

📦 የጽዮን ምርኮ ፥ ታቦተ ጽዮን፤

“የእግዚአብሔር እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ በረታችባው፤ ሰዎቹንም በእባጭ ቍስልም መታቻቸው፤ አጠፋቻቸው፡፡ ታቦተ ጽዮንን ወደ አስቀሎና በወሰዷት ጊዜም አስቀሎናውያንንም በእባጭ መታቻቸው፡፡ ምድራቸውም በአይጦች መንጋ ተወረረ፡፡ እጅግ ዋይታና ጩኸት ኾነ፣ ታቦተ ጽዮን በፍልጥኤማውያን ላይ መቅሠፍት እንዳበዛችባቸው ባዩ ጊዜ የእግዚአብሔር ቍጣ በኀይል ወርዶባቸዋልና አምስቱ የፍልስጥኤም ነገሥታት (አዛጦን፣ አስቀሎና፣ አቃሮን፣ ጌትና ጋዛ) ከካህናተ ጣዖትና ከሟርተኞች ጋር እንዲህ በማለት ተማከሩ፤ ‹‹የእስራኤልን አምላክ ታቦት ብትሰዱ የበደል መሥዋዕት መልሱ እንጂ ባዶውን አትስደዱት፡፡ በዚያን ጊዜም ትፈወሳላችሁ፡፡ እጁም ከእናንተ አለመራቁ ስለ ምን እንደኾነ ታውቃላችሁ፤” /፩ኛ ሳሙ. ፮፥፫/፡፡

በዚህ ተስማምተው በአምስቱ የፍልስጥኤም ግዛቶች ቍጥር አምስት የወርቅ አይጦችንና አምስት የወርቅ እባጮችን ቅርፅ አዘጋጁ፡፡ ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞንም ጠምደው በሠረገላ ከተዘጋጀው ወርቅ ጋር ታቦተ ጽዮንን ጫኑ፡፡ ሠረገላውን እየጐተቱ ከፍልስጥኤም ወጥተው ወደ ቤትሳሚስ ሔዱ፡፡ ሠረገላውም ወደ ቤትሳምሳዊው ወደ ኢያሱ እርሻ በደረሰ ጊዜ በዚያ ቆመ፡፡ የዚያ አገር ሰዎችም ታቦቱና ወርቁ የተጫነበትን ሣጥን ሲያወርዱ ወደ እግዚአብሔር ታቦት የተመለከቱ ሰባ ሰዎች በመቀሠፋቸው ምክንያት ቤትሳምሳውያን በፍርሃት ተዋጡ፡፡ የቂርያትይዓሪ ሰዎችም ታቦተ ጽዮንን በአሚናዳብ ቤት አኖሯት፤ አልዓዛር ወልደ አሚናዳብም ታቦቷን እንዲያገለግል ተደረገ፡፡ በዚያም ታቦተ ጽዮን ለሃያ ዓመት ኖረች፡፡

😇 ወንጌላዊው ቅዱስ ፊሊጶስ ወደ ጋዛ በመውረድ ነበር ኢትዮጵያዊውን ጃንረባ ባኮስን ያጠመቀው (የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፰፥፳፮፡፵)

❖[ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፲፩]❖

፵ በፍጻሜ ዘመንም የደቡብ ንጉሥ ከእርሱ ጋር ይዋጋል፤ የሰሜንም ንጉሥ ከሰረገሎችና ከፈረሰኞች ከብዙም መርከቦች ጋር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣበታል፤ ወደ አገሮችም ይገባል፥ ይጐርፍማል፥ ያልፍማል።

፵፩ ወደ መልካሚቱም ምድር ይገባል፥ ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ፤ ነገር ግን ኤዶምያስና ሞዓብ ከአሞንም ልጆች የበለጡት ከእጁ ይድናሉ።

፵፪ እጁን በአገሮች ላይ ይዘረጋል፥ የግብጽም ምድር አታመልጥም።

፵፫ በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ፥ በከበረችም በግብጽ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል፤ የልብያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይከተሉታል።

፵፬ ከምሥራቅና ከሰሜን ግን ወሬ ያውከዋል፤ ብዙ ሰዎችንም ይገድል ዘንድና ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ በታላቅ ቍጣ ይወጣል።


፵፭ ንጉሣዊ ድንኳኑንም በባሕርና በከበረው በቅዱስ ተራራ መካከል ይተክላል፤ ወደ ፍጻሜው ግን ይመጣል፥ ማንም አይረዳውም። 

📖 የስምምነቱ ጥበብ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ በሚያነሱበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣ “የስምምነቱ ጥበብ” ከሚለው መጽሐፋቸው ውስጥ አዲስ ባለሀብቶች “አማራጮችዎን ከፍ እንዲያደርጉ” የሚል አንድ ክፍል እናስታውሳለን።

ትራምፕ በጣም ተስፋ ሰጪ ስምምነቶች እንኳን ሳይሳኩ እንደሚቀሩ ይከራከራሉ፣ ስለዚህ ስኬት ቢያንስ ግማሽ ደርዘን የውድቀት ስልቶችን ማዘጋጀት ይጠይቃል - ምክንያቱም እሱ እንደሚለው፣ ማንኛውም ነገር ይቻላል።

ትራምፕ የሕዳሴው ግድብ ውዝግብ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ተወያይተዋል። ግድቡ ለግብፅ የውሃ ደህንነት ከፍተኛ ስጋት እንደሚፈጥር ያላቸውን ስጋት በድጋሚ በመግለጽ፣ የቀድሞውን የዴሞክራቲክ አስተዳደር ፕሮጀክቱን በገንዘብ በመደገፍ እና በማንቃት ተጠያቂ አድርገዋል። ከካይሮ ጋር ቅንጅት እየተደረገ መሆኑን እና “ረጅም ጊዜ” ስለሚሆን መፍትሔ ግልጽ ባልሆነ መንገድ ተናግረው ነበር - ተጨማሪ ዝርዝሮችን ሳይሰጡ።

ዓባይ እና ጋዛ፡ የግብይት ድርድር?

ከዚህ አንጻር፣ ትራምፕ በግድቡ ላይ የሰጡትን አስተያየት ከሰፋፊ የክልል እድገቶች ጋር ማገናኘት ምክንያታዊ አይደለም - በተለይም ጋዛ። ጉዳዩ በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው በእስራኤል እና በኢራን መካከል ሊፈጠር ከሚችለው የተኩስ አቁም ስምምነት ጋር እስኪዛመድ ድረስ በሕዝብ አጀንዳቸው ላይ አልተካተተም። ብዙም ሳይቆይ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ወደ ዋሽንግተን ጉብኝት፣ የሰብዓዊነት ከተማ ተብላ የምትጠራ ከተማን በተመለከተ የሕዝብ ሀሳቦች እንደገና መነሳታቸው እና የጋዛን የፍልስጤም ህዝብ ወደ ግብፅ ሲናይ ባሕረ ገብ መሬት ለማዛወር ወይም ግዛቱን በግብፅ ቁጥጥር ስር ለማድረግ የረጅም ጊዜ ሀሳቦችን የሚያስተዋውቁ የእስራኤል ደጋፊ ማዕከላት የሚዲያ ተሟጋችነትን አድሰዋል።

ትራምፕ ለአደጋ ተጋላጭ የሆነ የንግድ ልውውጥ መሰረት እየጣሉ ይመስላል፡ የግብፅን ተባባሪነት በመተካት የአባይ ውሃ ደህንነት - የፍልስጤማውያንን ወደ ሲና መፈናቀል በመቀበል፣ በጋዛ ላይ የአስተዳደር ቁጥጥር በማድረግ ወይም ቢያንስ ለኔታንያሁ ተስማሚ በሆነ ውሳኔ ውስጥ የበለጠ ተጠላልፈው መሆን።

እንዲህ ዓይነቱ ውሳኔ ተቃውሞን ለማስወገድ፣ ጋዛን በቋሚነት ለመቆጣጠር ወይም በእስራኤል ቀስ በቀስ እንድትሳብ ለማድረግ ያለመ ሲሆን ይህም በዌስት ባንክ ውስጥ ያሉትን እድገቶች የሚያንፀባርቅ ነው። እነዚህ ሁኔታዎች አስደንጋጭ ቢሆኑም፣ በእስራኤል በጣም ተደማጭነት ባላቸው ደጋፊዎች በተቀበለው የፖለቲካ አስተሳሰብ ዓለም ውስጥ ይቀራሉ።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment