አሳዛኙ ዲያብሎሳዊ ጨዋታ

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

☪ ዓለምን እያናወጠ ያለው የእስማኤል እና የኤሳው ሕብረት ቀጥሏል!

❖ የሥጋ ሰዎች በመንፈስ ያሉትን በማሳደድ አንድ ሆነዋል!

🛑 እንደተለመደው፤ 👉 “ችግር – ምላሽ – መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solution” + Thesis-Antithesis-Synthesis (ተሲስ ፣ ፀረ-ፀረስታ እና ውህደት/መደመር)👈 የሚለውን የሉሲፈራዊውን ጆርጅ ሄገልን ዲያሌክቲክ በመከተል እንደ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኮንጎ፣ ናይጀሪያ ወዘተ ባሉ ሀገራት ሁለቱንም 'ተፃራሪ መሳይ' ኃይሎች በመቆጣጠር ሁከትንና አለመረጋጋትን በመፍጠር በክርስቲያን ሕዝቦች ላይ የጀነሳይድ ጂሃዶችን ያካሂዳሉ፣ መሬቱን፣ ውሃውን እና አየሩን ይበክላሉ፣ የተፈጥሮ ሃብቶችን፣ ታሪካዊ ቅርሶችን ይዘርፋሉ/ያወድማሉ።

ሰይጣን ሁለቱንም ወገኖች ይቆጣጠራል። ልጆቹም ከደቡብ እስከ ሰሜን ያሉትን 'ጠበኞች' የሚመስሉትን፣ የፖለቲካ አካላትን እና ልሂቃንን ሁለቱንም ኃይሎች ይቆጣጠራሉ። ቁጥጥር የሚደረግበት ተቃውሞ በአሁኑ ጊዜ ተስፋፍቷል፣ እናም የታሰበው ብቸኛው ውጤት እኛ ከፈቀድን ክፍፍል መፍጠር ነው። ቁጥጥር የሚደረግበት ተቃውሞ የሚፈለገውን ውጤት ለማግኘት ሁለት ተቃራኒ የሚመስሉ ወገኖችን እርስ በርስ የማጫወት ዘዴ ነው። ክፉው ከዳተኛ ሩሲያዊ ፍሪሜሰን/ነፃ ግንበኛ ቭላድሚር ኢልይች ሌኒን በአንድ ወቅት “ተቃዋሚዎችን ለመቆጣጠር ምርጡ መንገድ ሁለቱንም ኃይሎች ራሳችን ስንመራቸው ነው” ብሏል። የሚያስፈራ ሐሳብ! 

ዛሬ በሀገራችን ኢትዮጵያ የምናየው፤ በሻዕቢያ፣ በህወሓት እና በኦነግ/ብልጽግና መካከል የይስሙላ ክፍፍል በሉሲፈራውያኑ ትዕዛዝና ፍላጎት የተፈጠረ መሆኑን ልብ እንበል። አሜሪካ፣ እስራኤል፣ ግብጽ፣ ኤሚራቶች እና ሳውዲ ዓረቢያ የታቦተ ጽዮን ጠባቂዎቹን የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያን ክርስቲያን ሕዝብ ለመጨረስ፣ ወርቁን፣ ዕጣኑን እና ከርቤውን ለመዝረፍ ብሎም የዓባይንና ተከዜን ውሃዎች እንዲሁም የሕዳሴውን ግድብ ልክ እንደ ጋዛ፣ ግሪንላንድ እና ቬኔዝዌላ በቁጥጥራቸው ሥር ለማድረግ የዘር ማጥፋት ጦርነቶችን ያለማቋረጥ ያካሂዳሉ። ሰሞኑን እንኳን ልክ ፕሬዝደንት ዶላር ትራምፕ፤ “በዓባይ ወንዝ ዙሪያ በግብጽ እና ኢትዮጵያ መካከል የሰላም ድርድርን እጀምራለሁ” ሲሉ፤ የፋሺስቱ እስላማዊ አገዛዝ + ህወሓት + ሻዕብያ + ፋኖ በወልቃይት እና ጸለምት ዙሪያ ውጊያ መሰል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የጀመሩት። ሁሉም እየሠሩ ያሉት የግብጽን እና እስራኤልን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው። አሳዛኙ ዲያብሎሳዊ ጨዋታቸው ይህ ነው! የእኛዎቹ ከሃዲዎችና ልፍስፍሶች በኋላቀር የመንደርተኛ ፖለቲካ ተጠምደው፤ 'ኤርትራ ዓደይ፣ ትግራይ ዓደይ!' እያሉ እግዚአብሔር አምላክ የሰጠነን ታሪካዊቷንና ሃያሏን አክሱማዊቷ ኢትዮጵያን ያሳንሳሉ፣ ያዳክማሉ፣ ይሸጣሉ፣ ሕዝባችንና እራሳቸውንም ለሉሲፈራውያኑ አሳልፈው ይሰጣሉ። ሉሲፈራውያኑ እና አጋሮቻቸው ግን እግዚአብሔር ያልሰጣቸውንና ያልፈቀደላቸውን ግዛት ሳይቀር 'ኬኛ' እያሉ ለመውረስ ይደፍራሉ።

👹 እንዴት ያለ ክፉ እና ግብዝ ዓለም ነው! ከእግዚአብሔር ፍርድ ፈጽሞ አያመልጡም! 
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment