ወሃቢይ ኢትዮጵያን የአሸባሪ ምድር ሊያደርጋት ነው!


✍ ሚካኤል ዘኢትዮጵ

በኢትዮጵያ ውስጥ ለዘመናት የቆየው የእስልምና እሴት በመቻቻልና በሰላማዊ አብሮነት ላይ የተመሠረተ ነበር። ሆኖም ከቅርብ አሥርት ዓመታት ወዲህ የወሃቢያ አስተሳሰብ መስፋፋት ይህንን ነባር እሴት እየተጫነው መሆኑን ብዙ የዘርፉ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ። ይህ አስተሳሰብ ለጽንፈኝነት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርና ወጣቶች በቀላሉ ለሽብር ቡድኖች እንዲማረኩ በር እንደሚከፍት ይነገራል። በተለይም በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ታዋቂ ግለሰቦችና ሰባኪያን የሚያስተላልፏቸው መልእክቶች ወጣቱን ከመካከለኛውና ሰላማዊው መስመር አውጥተው ወደ አክራሪነት እየገፉት መሆኑ ለሀገር ደህንነት ትልቅ ስጋት ሆኗል።

በፑንትላንድ የተካሄደው ዘመቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሽብር ቡድኖች (እንደ ISIS እና አልሸባብ ያሉ) የሰው ኃይል ምንጫቸውን እያሰፉ መሆኑን ያሳያል። በፑንትላንድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 42  የISIS ታጋዮች መካከል 23ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው አሳዛኝ ነው። ከዚህ የሚከፋው ኢትዮጵያውያን በእንዲህ ዓይነት ድርጊት ላይ ተሰማርተው መገኘታቸው በዲፕሎማሲው ረገድ ሀገሪቱ ያላትን የፀረ-ሽብርተኝነት ቁመና ጥላሸት ሊቀባው የሚችል ሆኗል። በተለይም ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም አስከባሪ በመሆን የምትታወቅ ሀገር እንደመሆኗ፣ ዜጎቿ የጥፋት ተላላኪ ሲሆኑ ማየት ለሀገራዊ ክብር የሚመጥን አይደለም። ይህ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን በውጭ ሀገራት ያላቸውን ተቀባይነትና እንቅስቃሴ ሊገድብ የሚችል የደኅንነት ስጋትም ይፈጥራል።

እንደ አህመዲን ጀበል እና አብዱጀሊል ዓሊ ያሉ ግለሰቦች በማኅበራዊ ሚዲያና በተለያዩ መድረኮች የሚያሰራጩት ትምህርት ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባለፈ ፖለቲካዊ እና ርዕዮተ-ዓለማዊ ቅስቀሳዎችን የሚያካትት ከሆነ ሰነባብቷል። አክራሪነት ወደ ሽብርተኝነት ከመቀየሩ በፊት፣ በመሃል ሀገር የሚካሄዱ የጽንፈኝነት እንቅስቃሴዎችን በንቃት መከታተልና የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ የኢትዮጵያን አንድነት ለማስቀጠል ወሳኝ ነው።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment