በዚህ ጥቂት ቀናት ሁለት ትልልቅ ክስተቶች ተከስተዋል። ሁለቱም ቦታ ሊሰጣቸው ስለሚገባ የተወሰነ እንዳስሳቸው።
በመጀመርያ የአባይ ግድብ ጉዳይ!
መላው ኢትዮጵያውያን በላባችንና ልፋታችን ከድሃው ጉያችን አዋጥተን በአፍሪካ ትልቁን በዓለምም ትልልቅ ከሚባሉት አንድ የሆነውን ግድብ ለመገንባት ችለናል። ከኢትዮጵያ አልፎ ብዙ ሀገራት ዘንድ ሃይልን በመሸጥ ኢትዮጵያን ታላቅ ሀገር የሚያደርጋትን ፕሮጀክት በብዙ ኢትዮጵያውያን ልፋት ዕውቀት ሃብት እና አስተዋጽኦ እውን አድርገናል። ለዚህም ብዙ የሚመሰገኑ ሰዎች አሉ።
አባይ ላይ ግድብ ለመስራት ጥናት ያደረጉት አጼ ኃይለ ስላሴ፣ ግድቡን ያስጀመሩት እና መሰረት ድንጋይ የጣሉት መለስ ዜናዊ፣ እሳቸው ከሞቱ በኋላም ፕሮጀክቱን ያስቀጠሉት ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ያስፈጸመው ዐቢይ አሕመድ፣ የፕሮጀክቱ መሪዎች ሆነው ያገለገሉት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ እና ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ፣ ከግብጽ ጋር በነበረው ተከታታይ አሰልቺ ድርድር ኢትዮጵያን አርኪ በሆነ መልኩ የተከራከሩላት እና ድምጽ የሆኑላት ኢንጅነር ስለሺ በቀለ። እንዲሁም ድጋፍ በማድረግ እና የተለያየ የመገናኛ ብዙኃንም የማኅበራዊ ሚዲያም ሽፋን በመስጠት የታገሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ምስጋና ይገባቸዋል።
በዚህ ግድብ መጠናቀቅ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘር ብሔር እና ሃይማኖት ሳይለይ፣ ሁሉም እኩል የተደሰተበት ሊደሰትበትም የሚገባ፣ መላ ኢትዮጵያን አንድ ካደረጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነውና።
ነገር ግን መጠናቀቁ ብቻ የመጨረሻው ነገር አይደለም። ገና ከአሁን በኋላ ብዙ ነገር ይኖራል። ብዙ የሚወጣ ሚስጥር፣ ብዙ ሽኩቻ፣ ብዙ ሴራ ብዙ ፖለቲካ፣ ብዙም ጂኦ-ፖለቲካን የምናይበት ነው።
ይህን ያህል ፕሮጀክት የኃይል ማመንጫ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ሃያል ቀጣናዊ ኃል የሚያደርጋት ነው። ታድያ በተለያየ ሴራ የባህር በር እንዳይኖረን እና እንድንደኸይ እንድንከፋፈል ያደረጉን የዓለም ሰርአቱ መሪዎችም አሁን ኢትዮጵያ ያን ኃይል እንድታገኝ ፈጽመው አይፈቅዱም። አጼ ቴዎድሮስ፣ ኦቶማን ቱርክ መካከለኛውን ምስራቅ ይዛ ኢንግሊዞችን መከራቸውን ስታበላቸው፣ ኢትዮጵያን አግዙ እና ቱርኮችን እንድትጥሉ እንርዳችሁ ብሎ ለኢንግሊዞች በተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ነገር ግን ኢንግሊዞች ቴዎድሮስ ያን ያህል ኃይል እንዲኖረው፣ በቀይ ባህር እና ሕንድ ውቅያኖስ መገናኛ በሆነው ቀጠናም እንደኛ አይነት አዲስ ልዕለ ኃያል ሃገር እንዲኖር ስላልፈለጉ ጥሪውን ችላ ብለውት ነበር። ሃያል እንድንሆን ሳይሆን በተቃራኒው ደካማ እንድንሆን ስለሚፈለግ ማለት ነው። ለዚያ ነው ደርግም በቀይ ባሕር ላይ ባሕር ኃይል ከገነባ በኋላ በባአቲስት ዓረቦቹ (ሶሪያ፣ ኢራቅ) እና በሊቢያ ስልጠና እና የመሳርያ ድጋፍ የነበራቸው ታጣቂ "ነጻ አውጪዎች" የባሕር ሃይሉ ወሳኝ ክፍል የሆነውን ቦታ ገንጥለው እንዲወስዱና በዚህ በኩል ስልጣን የያዙትም የባህር በራችንን እና ወደባችንን እንዲወስዱ ፈቅደውላቸው በዚህ መሃል ኢትዮጵያን ዘጋግተው አደኽይተው ያስቀሯት።
እና መጀመርያም ግድቡ ለምን እንዲሰራ ፈቀዱ ታድያ? ያስብላል። ነገሩን ስናየው ግን፣ የዓረብ ስፕሪንግ አመጽ በተነሳበት እና ግብጾች ትኩረታቸው ወደዛ በተሳበበት ወቅት፣ ሁከት ላይ በነበሩበት ወቅት መጀመሩ፣ እነሱም ሁከቱ ቀዝቅዞ ሲነቁ ግድቡ ተጋምሶ የጠበቃቸው ሁኔታ፣ ያም እነሱን እስካሁን ድረስ በጭንቀት እና ቁጣ እንዲሁም ጸጸት ውስጥ ያስቀመጣቸው ሁኔታ መኖሩ ነው። ያም ታድያ አንዳንዶች እንደሚሉት እነ እስራኤል እና አሜሪካ በዚህ ተጠቅመው የግብጽን እጅ ለመጠምዘዝ ፈልገው ነበር ይላሉ። ምክንያቱም ግብጽ ማለት የዓረቡ ዓለም ቁልፍ ናት። የዓረብ ሊግ መስራችና ዋና ናት። ልክ የአፍሪካ ሕብረት በኢትዮጵያ ትልቅ ትጽዕኖ ውስጥ እንዳለው ሁሉ፣ ዓረብ ሊግም የግብጽ ትልቅ ተጽዕኖ አለው። ስለዚህ አሜሪካ እና እስራኤል ግብጽን ከያዙ ዓረቡን ዓለምም መያዝና የፈለጉትን ነገር ማስደረግ ይችላሉ።
ከዚያስ ምን ይፈጠራል? የዓረብ ሀገራት ሁሉ ከአይሁዶች ጋር ያላቸውን ታሪካዊ ጠላትነት ወደጎን ትተው "የአብረሃማዊ ስምምነት" የተባለውን ከእስራኤል ጋር ተፈራርመዋል። በዚህም ምክንያት የእስራኤል ጠላት መሆን ትተው ወዳጇ ሆነዋል። አሁንም ጋዛ እንዲህ ስትወድም እነ ኢራን እና ሊባኖስ የየመን ሁቲዎች ትንሽ ትንሽ ይደክማሉ እንጂ ሌላው አረብ ከዳር ቆሞ ነው የሚያየው። ያ የሆነበት ደግሞ ከግዮን እስከ ኤፍራጥስ ያለውን ህልም ለማሳካት እና ሶስተኛውን የሰሎሞን ቤተመቅደስ ለመገንባት ካላቸው የመጨረሻው ግብ የመጣ ነው። ያንን ሁሉ ለማስፈጸም ደግሞ ዓረቦችን ማሳመን ነበረባቸው። እነሱን ለማሳመን ደግሞ ግብጽን መያዝ ነበረባቸው። ታድያ ግብጽን ለመያዝ ከዚህ በላይ ሌላ ምን መንገድ አለ። ከዚህ ግድብ በላይ ግብጽን ያሸብረ ያስፈራ ነገር አለ?
ታድያ ያ ሁሉ ከሆነ በኋላ ግድቡስ መጨረሻው ምን ይሆናል? መልሱ የኛ አይሆንም የሚለው ነው። እኛ በአንድም በሌላም መንገድ ተቆራርጠን ተከፋፍለን እንበተናለን፣ ከዚያ አንድ አካል የራሱን ወኪል ተጠቅሞ ግድቡን ይቆጣጠራል። ሃሳቡም ከግዮን እስከ ኤፍራጥስ አይደል? ግዮን ማለት ደግሞ ግድቡም አንዱ ወሳኝ ክፍሉ ነው። ኤፍራጥስ ወንዝ ሶርያ እና ኢራቅ ውስጥ ነው ያሉት። እዛ ያላቸውን ስራ ሊያጠናቅቁ ጥቂት ነው የቀራቸው። እኛም ጋ ደግሞ የቀረውን ስራ ይፈጽማሉ።
ሁለተኛው ክስተት ደግሞ የጨረቃ ግርዶሹ ነው። ብዙ ጊዜ በዚህ መገናኛ ብዙኅን ላይ የፀሐይ ወይም ጨረቃ ግርዶሽ ሲፈጠር በዝርግ ምድር ላይ ያለው አረዳድ እንዴት ነው? እንዴት ነው የምታብራሩት የሚል ጥያቄ ይነሳል።
ለዚህ የምንለው። በቂ የሚባል መልስ የለንም ነው። ለምንድነው ወይም እንዴት ነው የሚፈጠረው? ለጊዜው በቂ የሆነ ማብራርያ የለንም። ግምቶች አሉ። ለምሳሌ ዶክተር ሮዳስ በአንድ ወቅት ያነሳው ነገር አለ። በኢትዮጵያ ጥንታዊ መጻሕፍት ላይ "መንጦላዕተ ጸሐይ" የሚባል ማለት ጸሐይን እንደ መጋረጃ የሚሸፍናት አካል አለ ተብሎ እንደተጻፈ የተናገረው አለ። ያ መልስ ሊሆነን ይችላል።
ነገር ግን በቂ መልስ የለንም ማለት ትክክል አይደለንም ማለት አይደለም። እስካሁን ሌሎች ነገሮችን ማስረዳት እንችላለን። ቀን እና ጨረቃ እንዴት እንደሚፈራረቁ፣ ፀሐይና ጨረቃ ብርሃናቸው እንዴት እንደሆነ፣ ወቅቶች እንዴት እንደሚፈራረቁ ወዘተ ማስረዳት እንችላለን። ነገር ግን የግርዶሹ ላይ ለአሁን ማብራርያ የለንም። ነገር ግን ከጊዜ በኋላ መልሱን ልናገኝ እንችላለን።
ሌላው ነገር፣ አንዳንዶች እንደሚያነሱት የዚህ ግርዶሽ መከሰት በተለይም ጨረቃዋ ቀይ መሆኗ አንዳች ክስተት ከዚህ በኋላ ሊፈጸም መሆኑን አመላካች ነው የሚሉ አሉ። ያ እውነት ሊሆን ይችላል። እንደሚታወቀው በዙርያችን የጦርነት ድባብ እያንዣበበ ነው። ስለ አሰብ፣ ስለ ቀይ ባሕር እየተወራ ነው። በዚያም በኩል ሰራዊት ወደ ድንበር አስጠግተው፣ ምሽግ ገንብተው፣ ድሮን ሳይቀር ከዓረቦች ገዝተው፣ ከግብጽና ሶማልያ ጋ በተደጋጋሚ ተገናኝተው አውርተው ጨርሰዋል። ሁለቱም ወገን የሆነ ፊሽካ ነገር እስኪነፋ የሚጠብቁ ነው የሚመስሉት። አሁን ከአውሎ ነፋሱ በፊት ያለው የጸጥታ ጊዜ ይመስላል።
ማንኛውም ጦርነት ከመፈጠሩ በፊት ለወራት ወይም ለዓመታት ወደዚያ የሚያመሩ ክስተቶች አሉ። ከዚያ ደግሞ ጦርነቱን በይፋ ለመጀመሩ ምክንያት የሚሆን ድንገቴ ክስተት አለ። በዚያ ድንገቴ ክስተት ሁለቱም ወገን እርስ በርስ ይካሰሳሉ። ከዚያ እሱ አጠቃኝ እሱ አጠቃኝ እየተባለ ያም ይሄን ይሄም ያን እየወቀሰ መዋጋትን ይቀጥላሉ ማለት ነው። ያም ጦርነት ደግሞ አብሮ ከራያና ወልቃይት ጉዳይ ጋ ሊገናኝ ይችላል፣ በመሃል ሃገርም ጊዜያቸውን የሚጠብቁ አካላት አሳቻ ሰዓት ጠብቀው ይሄን መንግስትም ጥለው ቦታውን ለመያዝ ተዘጋጀተው የጨረሱም አሉ። ስለዚህ አሁን ልንል የምንችለው፣ ከፊት ያለው ጊዜ እጅግ ከባድ እና አስፈሪ ነው፣ ጸልዩ፣ ንስሐ ግቡ ብቻ ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment