አሞኛል ፣ ታምሜአለሁ ወይስ የሆነ ነገር አለ?

በ ዘአዲስ

ብዙ ነገሮች ግራ እየገቡኝ ነው፡፡ አንዳንዱ ከሕሊናዬ በላይ ስለሆነ ገርሞኝ ልጽፍላችሁ ወደድኩ፡፡ እስኪ አግዙኝ፡፡

ጳጳስ ሲኖዶስን ካልከፈልኩ ብሎ “ እባክህ ተው”  እየተባለ በምዕመን የሚለመንበት ግዜ ግ 
ን የጤና ነው፡፡ ጳጳስ ኑፋቄ እያስተማረ ፣ ተራው ምዕመን እርማት የሚሰጥበት ፣ የሚሳቀቅበት ግዜ ግን  የጤና ነው?፡፡ ጳጳስ ንግግሩን ማረም አቅቶት ፣ አዳማጭ ምዕመን ( ጎጋው)  የሚሳቀቅበት ግዜ ምን አይነት ነገርና ግዜ  ነው? ምንድነው የተበላሸው? የሆነ ነገርማ አለ፡፡ 
"ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡ፣ ውሃ ቢያንቅ በምን ይውጡ "እንደተባለው ያለ ነገር ሆነ ኮ? 

ሳምንት አልፎ ሳምንት ሲተካ ፣የሚሰማው የኦርቶዶክሳውያን ሰቆቃ ነው፡፡ ምዕመናን ያታረዳሉ፣ ካህናት ከነቤተሰባቸው ይጨፈጨፋሉ፡፡ አብያተ ክርስትያንት ይወድማሉ፡፡ አልፎ ተርፎም፣  አለም በቃኝ ብለው ገዳም የገቡ መነኮሳት በተደጋጋሚ ገዳማቸው ድረስ እየተገባ ይጨፈጨፋሉ፡፡ ጭፍቸፋውንም ለማስተባበል፣ "ገዳማት ማሰልጠኛ ሆነዋል" እየተባለ ውሸትና መርዝ አብሮ ይረጫል፡፡ ያው ገዳይን ለመከላከል መሆኑ ነው፡፡ በኢኮኖሚም፣ የቤተ ክርስትያኑቱንም አቅሟን ለማሽመድመድ “ ታክስ “ ተብሎ ብሯ ይዘረፋል፡፡ 

ሚደንቀውን ግን 

ቤተ ክህነቱ ምንም እንዳልተፈጠረ እንቅልፍ ላይ ነው፡፡ የቤተ ክርስትያን ክብር ያስጠብቃሉ የተባሉቱ አፋቸው ተለጉሟል፡፡ “ ተገደሉ” እንኳን ለማለት ግዜ የላቸውም፡፡ ቄሳር እንዳይቀየም ይፈራሉ፡፡ የሃጭሉን ሙት አመት ግን ቪድዮ እያስቀረጹ ይለጥፋሉ፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? ለጳጳሳት ከዝቋላ መነኮሳት ሀጫሉ ይቀርብ ነበርን? 

በዚህ ልክስ ግን የገዳዮች ጥላቻና የበተ ክህነቱ አድርብዬነት  ከየት የመጣ ነው? ግራ ይገባል
ይህ በንዲህ እንዳለ፣ 

የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ተብለው የተሾሙ ዲያቆናት፣ ራሳቸውን ለቄሳር አቅርበው “ እኔ እበልጥ እኔ አበልጥ “ የወዶ ገብ ካድሬንት ፉክክር የያዙበት ነገርስ የጤና ነው፡፡ጳጳሳቱ፣ ለሾማቸው አምላካቸው ሳይሆን ለቄሳር በዚህ ልክ “ ምን ልሁንልህ” ብሎ ቤተ ክርስትያንን እንደ ጭዳ እና የባለስልጣን መታያ አድርጎ ማቅረብ ምስጢር የጤና ነው?  የምዕመኑንስ ዝምታ የጤና ነው? 

ፊደል ቆጥረዋል፣ ያመዛዝናኑ የምንላቸው ሰዎች፣ ትናንትና የቆሙለትን ዓላማ ባንድ ለሊት ክደው የተገላቢጦሹን ሲሰሩና ሲናገሩ ማየት የጤና ነው፡፡ እንዴት ሰው እንዲህ ጭንቅላቱን ለሆዱ ይሸጣል፡፡ ፊደል የቆጠረ ሰው ፣ አፉን ለሆዱ አከራይቶ መኖር አይደብርም?፡፡ ሰው እንዴት ራሱን ማከበር ያቅተዋል? እውነትን በመሸቀጥና እንደ ፔንዱለም በአቋም መወዛወዝስ የጤና ነው፡፡ ለከፈለ ሁሉ ማሽቃበጥ ፣ የህሊና ሴተኛ ዳሪነት አይደለምን? የአዕምሮ ዝሙት!
ውሸት ብሔራዊ ባህል የሆነበት ነገር የጤና ነው? “ ወደብ አገኘን እንኳን ደስ አላችሁ” ተብሎ የተነገረን በብሔራዊ ሚድያ ነው፡፡ በታላላቅ የሀገር ባለስልጣናት ጭምር ነው፡፡እሱን ለማስተባበል ይመስላል” ጣናነሽ “ ያሏትን ጀልባ “ መርከብ እያሉ በየብስ ላይ ማዞርስ? የጤና ነው ግን? ይህች ጀልባ ስንት ወጭ ወጥቶ በየወረዳው የምትዞርበት አመክንዮስ ምንድነው? 

“ ብር አቅሙን አዳከምንላችህ፡” እንኳን ደስ አላችሁ”  የሚለው ነገርማ በተለይ ሁሌ ካይምሮዬ አይጠፋም፡፡ ይህም ብሔራዊ ውሸት በብሔራዊ ሚድያና በታላላቅ ባለስልጣናት የተነገረ ነው፡፡ አሁን የገንዘቡ የመግዛት አቅም ተዳክሞ መግዛት ስላቃተው” ብዙ የቢሮ ሰራተኛ በየሆቴሎቹ ትራፊ ምግብ ለመግዛት እንደሚሰለፍ እተነገረ ነው፡፡” እንኳን ደሳላችሁ፣ እንዲህ ሕዝቡን ለማኝ ማድረግ ነበር፡፡  ይህ በተነገረ በጥቂት ቀን “ ትራፊ የሚሸጡ ሆቴሎች ይህን እንዲያቆሙ አሊያ ፈቃዳቸው እንኳን ሊነጠቅ እንደሚችል በመንግስት ታወጀ፡፡ የጤና ነው ግን? ሲጀምር፣ ብር በዛ ደረጃ አቅሙ ሲዳከም ይህ እንደሚመጣ ግልጽ ነበር፡፡ ሕዝብን አደከየን ብሎ እንኳን ደስ አላችሁ ምንድነው ግን? በአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም ጫና የተደረገ ትልልቅ ጫናዎችን “ ሀገር በቀል ሪፎርም ማለት ማንን ማታለል ይባላል? ውሸት በቃ ብሄራዊ ሆነ ? 

እንቃወማለን የሚሉ አካላትም ያስደንቃሉ፡፡ እንፋለመዋለን ያሉት አካል ላይ ፣ ሀይላቸውን አስተባብረው ይታገላሉ ብሎ የሚጠብቅ ደጋፊ ምስኪን ነው፡፡ ዋናው ትግል እርስ በርስ ሆኗል፡፡እንፈለመዋለን ያሉትን አካል ትተው፣ የጎኞሽ ትግልስ የጤና ነው?  ስንቱ ተቃዋሚ እንደ አሜባ ተከፋፈለ? ጠላት ማነው? እርስ በርስ? የጤና ነው ግን ? 

“ መብረቃዊ ጥቅት” ብሎ ሰሜን ዕዝን በመተንኮስ የተጀመረው የህወሀት እብሪት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ሕዝብን  በማስፈጀት ፣ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ካለፈ አምስት ዓመት እንኳን ሳይሞላው ፣ አሁንም “ አሁን እንደ ድሮው አይደለንም፣ ድሮን ታጥቀናል፡ “ አይነት ንግግር እያሰሙ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም የጤና ነው? ወዲ እምበይተይ ይሄን መናገሩ ላይገርመኝ ይችላል፣ ተቀባዩ የካድሬ ስብስብ ግን እንዴት? አሁንም ከተወሰነ ወራት በኋላ “ አዬ ተጋዳላይ” በሚል የማኅሌት ዘፈን እየታጀቡ ሕዝብን ለመርዶ ለመጥራት? ከአንድ ሚሊዮን ሰው ሞት በላይ ምን መምሕር ነበር? 

“ ኢሳያስ ፣ ህግደፍ ናዚ ነው ለፍርድ ይቅረብ”  ሲሉ የነበሩ አካላት፣ አስመራ ድረስ በመሄድ የ"ብጻይ" ኢሳያስን እግር ስሞ መምጣት የጤና ነው? በተለይ ስታሊንን ጤናውን ደህና ነው? የኤርትራ ሰራዊት ያን ያህል ሴቶችን ደፈረ ሲሉን የነበሩ አካላጽ ከህቶቻቸው ደፋሪዎች ጋር የጤና ነው? 

ግን የሆነ በመሰረታዊ ነገር የተዛነፈ ነገር አለ፣ ወይስ ችግሩ እኔ ጋ ነው? ከሆነ ንገሩኝ፡፡ ታምሜአለሁ ብዬ ሀኪም ልይ
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment