✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ አውታር
የፈውስ አገልግሎት በመስጠት ሰዎችን ከእርኩስ መንፈስ እስረኝነት የሚፈውሱ አባቶችን "ሐሰተኛ አጥማቅያን" ብለው በመፈረጅ ስተው ምእመንን እያሳቱ ያሉት አባ ገብረ ኪዳን ፡ አሁን ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ከስጋ ደዌ ለመፈወስ 'ሆስፒታል ልሰራ ነውና አግዙኝ' እያሉ ነው። መቼም ጊዜው አሳዛኝ ነገሮች የምናይበትና የምንሰማበት ነውና፡ አኚህ አባት መንፈሳዊው ፈውስ ተቃውሞው ፡ ለምን ይሆን ስጋዊው እና ሰነ-ዕውቀት/ሳይንስ መሰረት ያደረገ ፈውስ የመረጡት?
አባ ገብረ ኪዳን ድንገት ደርሰው ሰው የሚታከምበት ሆስፒታል ካላስገነባሁ እያሉ ነው። ይሄንን ሐሳብ ከማሰባቸው በፊት ግን ድርሳነ ሚካኤልን አንብበውታል? ያምኑበታል? ይቀበሉታል? ወይስ እንደ ተረት እና እንደ ልብ ወለድ ነው የሚያነቡት።
ድርሳነ ሚካኤል የጥር ላይ፣ "በዚህ ዓለም ውስጥ ሁሉም ደዌ የሚሆኑት አጋንንት ናቸው፣ ያለ አጋንንቶቹ በቀር በዚህ ዓለም በሽታ የሚሆን የለም" ይላል።
እና አባ ገብረ ኪዳን እነዚህን አጋንንት ነው ሆስፒታል ገንብተው ለመዋጋት ያሰቡት፣ ሆስፒታል ውስጥ ያሉት ዶክተሮች ናቸው ያለ ምንም መንፈሳዊ እውቀት እነዚህን አጋንንት እንዲያስሩ እና ከሰዎች ላይ አስወግደው ወደ ሲዖል እንዲያባርሩ ያሰቡት .... ወይስ ጭራሽ በመጽሐፉ ላይ እንዳለው በሽታ የሚሆኑት አጋንንት እንደሆኑ አያውቁም... መቼም ሊቀ ሊቃውንት ሆነው ይሄንን ነገር አያውቁም ማለት ያስቸግራል፣ የተጻፈውን ነገር አያምኑበትም ማለት ይሻላል።
ለመንፈሳዊያን ለሆኑ አጋንንት መፍትሄ የሚሆነው መንፈሳዊ አሠራር ነው... ጠበል፣ እምነት፣ ጾም ፣ ጸሎት በነዚህ ነው አጋንንት መዋጋት የሚቻለው። ከአንድ መነኩሴም እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ምንም አይጠበቅም .... በገድላት ላይ ያሉ መነኮሳት ሰው ታሞ ሲያዩ የሚፈውሱት ጠበል አፍልቀው እንጂ ሆስፒታል ገንብተው አልነበረም ።
ዘመናዊው ህክምና እንዴት ተጀመረ
ሮክፈለር የሚባለው በአሜሪካ ውስጥ በነዳጅ ማውጣት በጣም ሃብታም ሰውዬ (በጊዜው የአሜሪካ 1ኛ ሐብታም ነበረ ) ከነዳጅ ማውጣት እና ማጣራት ሥራው ተጨማሪ ወደ ኬሚካል እና ሕክምና ሥራዎች መስፋፋት ጀመረ... እና በሕክምና እና በመድኃኒት ቅመማ ሥራዎች ላይ ከነዳጁ የበለጠ ትልቅ የገቢ ምንጪ እንደሚሆኑለት ተመለከተ ሕክምና ላይም ትልልቅ ሥራዎችን መሥራት ጀመረ።
መጀመሪያ ያደገረው ነገር በጣም ብዙ ገንዘብ በመበጀት የሕክምና ኮሌጆችን እና መካነ አዕምሮ/ዩኒቨርስቲዎችን መክፈት ነበር... በነዚህ መካነ አዕምሮ/ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት ዶክተሮቹ የበሽታውን ምንጭ እንዲያክሙ ሳይሆን የተለያዩ መድኃኒቶችን በመጠቀም በሽታውን የማዳፈን ሥራ እንዲሠሩ ነው... ከጥቂት ጊዜ በኃላ በሽታው አገርሽቶ ሲነሳ እንደገና ሌላ መድኃኒት ደግሞ ያዙ እና ለትንሽ ጊዜ እንዲታገስ ያደርጉታል ፣ በዚህ መልኩ ታካሚው መድኃኒት ላይ ብቻ ጥገኛ እንዲሆን ማድረግ ነው የትምህርቱ ዓላማ።
ይሄንን መድኃኒት የሚያመርተው ደግሞ እራሱ ሮኬፌለር ድርጅት ብቻ ነው። ይሄንን ነው በተወሳሰበ የትምህር አሰጣጥ ዶክተሮቹ እንዲማሩ የሚደገረው። በቀላሉ የሚድነውን በሽታ ራሱ መድኃኒት በማዘዝ ሰው የመድኅኒት ጥገኛ እንዲሆን እና ዕድሜ ልኩን መድኃኒት የሚውጥ ህዝብ በመፍጠር ከመድኃኒት ሽያጭ የማይቋረጥ የገቢ ምንጭ መፍጠር ነበር የጆን.ዲ.ሮኬፌለር ዓላማ።
ይሄም በሽታውን ሳይሆን ምልክቱን ብቻ በመድኃኒት የማስታገስ አሠራር ከአሜሪካ ወደ አውሮፓ ከዛ በዓለም ሁሉ ተሥፋፍቶ የዘመናዊ ሕክምና እየተባለ የሚጠራው። አሁንም ድረስ የነ ሮከፈለር ድርጅት ብቻ ነው በተለያየ ስያሜ በዓለም ላይ ያለውን መድኃኒት የሚያመርተው የሚያከፋፍለው።
አዎ ሆስፒታሎች፣ እና ፋርማሲዎች በጣም አትራፊ ድርጅት ናቸው ለዚህም ነው ልክ እንደ ዳቦ ቤት በየቦታው ተከፍተው የሚታዩት... በሽተኛ ስለበዛ ፣ በሽተኛም እንዲበዛ የሁል ጊዜ ጸሎታቸው ነው... የነሮኬፈለር ዓላማ ተባባሪዎች ናቸው ማለት ነው፣ ለነሮኬፈለር ከሚገባው ገንዘብ በጥቂቱ ለፋርማሲዎች እና ለሆስፒታሎች ይደርሳቸዋል።
በሽታን ከስር መሠረቱ ነቅሎ የሚጥል መፍትሔ ለሆስፒታሎች እና ፋርማሲዎች ጠላታቸው ነው ምክቱም የገቢ ምንጫቸው ስለሚቋረጥ። ይሄንንም የምታደገው ቤተክርስቲያን ናት።
በቤተክርስቲያን የበሽታ ስረ መሰረቱ ምን እንደሆነ ይታወቃል። ሰው ከእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሲወጣ፣ አታድርግ የተባለውን ሲያደርግ፣ አድርግ የተባለውን ሳያደርግ ለምሳሌ ጹም ሲባል የማይጾም ከሆነ፣ አትብላ የትባለውን ሲበላ... አጋንንት ውስጡ ገብተው እንደሚያድሩ... እነዚያም አጋንንት በሽታ እንደሚሆኑ ይታወቃል። ስለዚህ ቤተክርስቲያን ሰው ከታመመ በኃላ ሳይሆን መጀመሪያ እንዳይታመም በስርዓት እንዲኖር የሚነገረው።
ከመቶ ዓመት በፊት በሀገራችን ደም ብዛት፣ ኩላሊት በሽታ አይታወቁም ነበር፣ አሁን ክህደት እና ምንፍቅና ሲበዛ፣ ሰው ከቤተክርስቲያን ትምህርት ሲወጣ ነው በሽታውም የበዛው። ጤነኛ ትውልድም የሚበዛው የቤተክርስቲያን ስርዓት ሲጠበቅ እንጂ ሆስፒታል ስለበዛ አይደለም፣ በሆስፒታል ብዛት ጤናን ማግኘት ቢቻል አሜሪካዊያን እና አውሮፓውያን ጤነኛ ይሆኑ ነበር ነገር ግን ከህዝባቸው ውስጥ በመድኃኒት ጥገኛ ያልሆነ፣ መድኃኒት ሳይውጥ የሚያድር ሰው በሀገራቸው የለም።
Blogger Comment
Facebook Comment