ሰሞኑን የተመረጡት የካቶሊክ ጳጳስ እንደ ሁሉም የካቶሊክ ጳጳሳት የህጻናት ወሲብ ትንኮሳ ክሶች ጋር የተተበተቡ እንደሆኑ ታውቋል። ይህ የተለመደ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ወንጀል ሁሉም መሪዎቻቸውን ያጥለቀልቀ እንደሆነ ይታወቃል።
ይህ በንዲህ እንዳለ፣ በዚህ የቀድሞው ጳጳስ ሞት እና የአሁኑ መመረጥ ዙርያ የኢትዮጵያውያን ሁኔታ እጅግ ትዝብት የሚፈጥር ሆኖ አልፏል።
የቀድሞው ፓፓ ሲሞቱ ህዝቡ የሱ አባት የሆኑ ይመስል ቅዱስ አባታችን፣ አባታችን እንዲህ አባታችን እንዲያ ሲሉ ተሰምተዋል። መነሻውና መሰረቱ ምን እንደሆነ የማይታወቅ ፍቅር እና አክብሮት ለዚህ ፖፕ ሲሰጥ ተመልክተናል። ሲመጀር እኛ ምን አገባን? መናፍቅ መሆን ብቻ ሳይሆን የነሱን ምንፍቅና በኛ ላይ መጫን፣ የኛን እምነት ለማጥፋት ለክፍለ ዘመናት የሰሩ ሰዎችን፣ እኛ ዛሬ አክብረን አፍቅረን የምንገኘው ምን ነክቶን ነው? የሆነ ሰው መጥቶ የካቶሊክ አፍቅሮትን መንፈስ ዘርቶአል እንዴ?
በጣልያን ወረራ ያጠፏቸው ገዳማትና ቤተክርስቲያናት፣ በሱስንዮስ ዘመን ያጠፉት ህዝብና ሃገሪቱን ሊሰለቅጧት ቅርብ ድርሰው የነበሩ መሆናቸው። ከዚያም በፊት ራሳቸው ከግሪኮች ሳይገነጠሉ በፊት፣ ከነ ንጉስ መርቅያን ዘመን ጀምሮ፣ የሁለት ባህሪ ምንፍቅና እምነታቸውን በተዋህዶ ተከታዮች ላይ ለመጫን ያደረጉት ድርጊት፣ የግብጽና ሶርያ ክርስቲያኖችን ያሳደዱበት መንገድ፣ ስንት ዋጋ ተከፍሎ ስንት መከራ ታልፎ፣ እነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ እነ ቅዱስ ሳዊሮስ፣ እነ ቅዱስ ያዕቆብ እልበረዲ፣ ተሰደው መከራን ተቀብለው ከባድ ዋጋን ከፍለው ከነሱ ጠብቀው ለዚህ ያደረሱንን።
ዛሬ የኛ ትውልድ ያንን ዘንግቶ ለካቶሊክ ከፍ ዝቅ ሲል ታይቷል። ጠላቱን አባታችን ሲል ተገኝቷል። ምን ጉድ ነን? ቆይ ቅኝ ግዛትን ይህን ያህል እንመኘዋለን እንዴ? አድዋ ላይ ስንት ደም እንዳልፈሰሰ የኛ ትውልድ ጣልያን ቢገዛን ይሻል ነበር ይላል። በእምነቱም በኩል ስንት ዋጋ እንዳልተከፈለ አሁን ትውልዱ ካቶሊኮች የኛ አባቶች ካልሆኑ እንላለን። ምን አይነት ከንቱ ትውልድ ነን በእውነቱ?
Blogger Comment
Facebook Comment