ከቫቲካን የወጣ የ፱፻/900 አመት የትንቢት መፅሃፍ እንደሚለው 'የፍርድ ቀን' በቅርቡ ሊመጣን ይችላል እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የመጨረሻው የቤተክርስቲያኑ መሪ ሊሆኑ ይችላሉ።
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሞት የ፱፻/900ዓመት ዕድሜ ያለው “የጳጳሳት ትንቢት” (“Prophetia Sancti Malachiae Archiepiscopi, de Summis Pontificibus” - ወይም “የቅዱስ-ሊቀ ጳጳስ ማላቺይ ስለ ሊቀ ጳጳሳት ትንቢት ፣)” በመባል የሚታወቀው መጽሐፍ እንደገና በሰዎች ላይ ፍላጎት አሳድሯል።
ቅዱሳት መጻሕፍቶቻችሁን በደንብ መፈተሽ ለምትፈልጉ፣ የፍርድ ቀን ፤ “የመጨረሻው ፍርድ” ወይም “የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት” በመባልም የሚታወቀው ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው ልጆች ላይ ለመፍረድ እና ምድርን እና ሰማይን ለማጥፋት ወደ ምድር የሚመለስበት ቀን ነው።
በዋናነት ማን እንደሚድን እና ማን እንደሚኮነን የምናውቅበት ቀን ነው።
ለአይራላንዳዊው ጳጳስ ቅዱስ ማላቺይ በተሰጠው የ፲፪/12ኛው ክፍለ ዘመን መጽሐፍ መሠረት፣ ይህ "የመጨረሻው ፍርድ" እ.አ.አ በ2027 ይካሄዳል።
Blogger Comment
Facebook Comment