ዛሬም ሆነ ላለፉት ሺህ ዘመናት ሁሌ እየተጨፈጨፈ ያለው እኮ የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ክርስቲያን ሕዝብ ነው። እኔን በጣም የሚያሳዝነኝ እና የሚያስቆጣኝ ሕዝበ ክርስቲያኑ እንደሚሳደድ፣ እንደሚራብ እና እንደሚጨፈጨፍ በግልጽ ተናግሮ ተገቢውን ክርስቲያናዊ አንድነትና እርምጃ ለመውሰድ ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳየው የዚህ ትውልድ ጉዳይ ነው። እንዲያውም በተቃራኒው ብዙ 'ኢትዮጵያዊ ነኝ' የሚል የወደቀ ወገን ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ቀንደኛ ጠላቶች ጋር አብሮ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለመጨፍጨፍ፣ ለማስራብ፣ ለማፈናቀልና ለማሳደድ ወደ አክሱም ጽዮን ዘመተ። ይህ እጅግ በጣም አስገራሚና አሳዛኝ የሆነ ታሪካዊ ስሕተት ደግሞ ጠላቶቻችንን እንኳን ሳይቀር ያስገረመና ያበረታታ ነው። በዳዮቻችን ዛሬም ግፋቸውንና በደላቸውን ያለምንም የፍትሕ እና ተጠያቂነት ሥራ በስላቅና በድፍረት የቀጠሉበት እኮ ይህን ስላዩ ነው። የበዳዮቻችን ድምጽ ከእኛ ተበዳዮቹ ከፍ ብሎ በመላው ዓለም ሊሰተጋባ የቻለውም ዓለም ከንቱ ስለሆነች ብቻ ሳይሆን እንደዚህ ዓይነት በጭራሽ መፈጸም የሌለበት ከባድ ስህተት “ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ክርስቲያን ነኝ!” በሚለው ወገን ዘንድ በመፈጸሙ ነው። “ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?” ብሎ እራሱን በመጠየቅ ከስህተቱ ለመማርና ኃላፊነቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰነፍና ወንድ ያልሆነ ትውልድ በመብዛቱ እኮ ነው። ይህ ከንቱ ዓለምም እኮ መኖራችንን እስከመርሳት ድረስ ዝም ያለንም በዚህ ምክኒያት ነው። ታዲያ ይህ ሁሉ የማን ጥፋት ነው? ለራሱ የማያስብ ሌላ ማን ሊያስብለት? በደሉ በግል ወደ ቤተሰባችን እስካልመጣ ድረስ የማንተነፍሰውና የወገናችን ስቃይ እና መከራ ብዙም የማያሳስበን፣ የማያስቆጣን እና በተገቢው መልክ ለበቀል የማየነሳሳን የእኛ ትውልድ ድክመትና ስሕተት ስለሆነ አይደለምን?! በደንብ እንጂ!
'ክርስቲያናዊ አንድነት' የመንፈስ ማንነታችንና ምንነታችን/ክርስትናችን ጥንካሬ ሙቀት መለኪያ ነው!
❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፩]❖❖❖
- ፩ አቤቱ፥ አድነኝ፤ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።
- ፪ እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ።
- ፫ የሽንገላን ከንፈሮች ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፥ ታላቅ ነገርን የምትናገረውን ምላስ፤
- ፬ ምላሳችንን እናበረታለን፤ ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።
- ፭ ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት እግዚአብሔር። አሁን እነሣለሁ ይላል፤ መድኃኒትን አደርጋለሁ፥ በላዩም እገልጣለሁ።
- ፮ በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር። የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።
- ፯ አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን።
- ፰ በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ።
- ፩ ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።
- ፪ የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ፤ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
- ፫ ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።
- ፬ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤
- ፭ ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤
- ፮ ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።
- ፯ ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
- ፰ በዚያ በታላቅ ፍርሃት እጅግ ፈሩ፥ እግዚአብሔር በጻድቃን ትውልድ ዘንድ ነውና።
- ፱ የድሆችን ምክር አሳፈራችሁ፥ እግዚአብሔር ግን ተስፋቸው ነው።
- ፲ ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።
Blogger Comment
Facebook Comment