የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አሜሪካ በኢትዮጵያም ሆነ በሱዳን እየተፈጸመ ላለው የዘር አጥፊ ጭፍጨፋ ደንታ አይሰጣቸው | በዚህም ምስጢራዊቷ ባቢሎን፣ የጋለሞታዎች ሁሉ እናት ባቢሎን/አሜሪካ እና የተባበሩት መንግስታት አብረው ይወድቃሉ። በ ፳/20 ኛው ክፍለ ዘመን ቀጣዩ ልዕለ ኃያል ሀገር እንድትሆን እድል ሰጡ።
ታላቋ ብሪታንያ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃ የግዛታቸው መጨረሻ ነበር። ያኔ ነበር የብሪታንያ ኢምፓየር ያበቃው። ነገር ግን ከመጋረጃው በስተጀርባ ምን አደረገች? ለዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ኃይሉን፣ ኃብቱንና መብቱን ሁሉ አስረከበች።
ስለዚህ አሜሪካ የተሰራችው በእንግሊዝ ሰዎች ነው። ከዚያም ታላቋ ብሪታኒያ እና አሜሪካ ምን አደረጉ? የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን አቋቋሙ።
የተባበሩት መንግስታት የለም፤ የተባበሩት መንግስታትን የምትቆጣጠረው አሜሪካ ናት። በዓለም ሁሉ ፊት ስም እና ጥሩ ስም ብቻ ነው። ግን አንድነት የለም።
ለምንድነው አንድነት የሌለው? ምክንያቱም እነዚህ ብሔራት ከእግዚአብሔር ክበብ ውጭ አንድ ስለሆኑና የጥንቷ ባቢሎን ሰዎች ተሰብስበው የባቢሎን ግንብ የሚባል ነገር ለራሳቸው ለመሥራት ስለሚሞክሩ ነው።
ከዚህ ግንብ ጀርባ'ሰብዓዊ መብቶች' የሚል ዓላማ ነበረው። ለእግዚአብሔር፤ “ሕግህን አንጠብቅም እኛ የራሳችንን ሕግና ሥርዓት እንከተላለን ስለዚህ ይህን ግንብ እንሠራለን አንተን በመጻረርና በአንተም ስም ፈንታ ለራሳችን ስም እናስጠራለን!”
በጥንቷ ባቢሎን የአሕዛብ መሰብሰቢያ አንድ ነገር ሰብዓዊ መብት ሳይሆን የእግዚአብሔር መብት ይናገር ነበር። የባቢሎን ግንብ በ፳/20 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ታላቋ ብሪታንያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ይህንን ሲመሰርቱ የመንግስታቱ ድርጅት (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ/ ጣልያን በኢትዮጵያ ላይ በሠራችው ወንጀል ሳቢያ ነው የፈረሰው) ተብሎ ይጠራ የነበረ ሲሆን፣ ስሙም በማንሃተን ኒውዮርክ ወደ ሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ግንብ ሆኖ ተቀይሯል።
አንድ ላይ ሆነው የእግዚአብሔር አምላክን መብቶች ሳይሆን ሰብአዊ መብቶችን ለማስፈጸም ምን እየሞከሩ ያሉት።
ከተባበሩት መንግስታት ጀርባ ያለችው አሜሪካ ናት። እነዚህ መንግስታት/ሀገራት የተባበሩት፤ የእግዚአብሔርን መብቶች ለመጠበቅ ሳይሆን ፥ “ሰብዓዊ መብቶችን” ለመጠበቅ ነው ተሰባስበናል የሚሉት። እራሷን ከእግዚአብሔር በመነጠልና ከስይጣንም ጋር እንዳዛመደችው ልክ እንደ ሴቲቱ (ራዕይ ዮሐንስ ፲፫፣ ፲፯ እና ፲፰) በአሜሪካ የሚመሩት የተባበሩት መንግስታትም በተመሳሳይ አካሄድ ለማጽደቅ እየሞከሩ ያሉት ሕግጋት ለ እግዚአብሔር አስጸያፊ የሆኑትን ዲያብሎሳዊ ሕግጋትን ነው።
አሜሪካ በትዕቢት፤ “ሀብታም፣ ኃያል ነኝ እና ማንም ሊያቆመኝ አይችልም!” እያለች ነው።
አሜሪካ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጭ ሆነሽ በግብዝነት፤ “አሜሪካ! አሜሪካ! አሜሪካ! እያልሽ በመመጻደቅ ላይ ነሽና መውደቅሽ አይቀርም። ግሩም የሆኑ፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላቸው ብዙ አሜሪካውያን አሉ፤ ነገር ግን ሥርዓቱ ባቢሎናዊ የክርስቶስ ተቃዋሚ ሥርዓት ነውና ይገረሰስ ዘንድ ግድ ነው።
አሜሪካ ፍጻሜሽ እንደ ግብጽ ኢምፓየር ይሆናል። የአሦር መንግሥት፣ የባቢሎን ግዛት፣ የፋርስ ከዚያም የሜዲስ ኢምፓየር፣ የታላቁ እስክንድር የመቄዶንያ የግሪክ ኢምፓየር እና የሮማ ኢምፓየር የት ናቸው? አሜሪካ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በማመጽሽ ትወድቂያለሽ! ወዮልሽ! አሜሪካ በአንድ ሰአት ውስጥ በድንገት ትሄጃለሽ፣ የተፈጥሮ አደጋ ሊሆን ይችላል… ከአሁን በኋላ ልዕለ ኃያሏ ሀገር አለመሆንሽን እና በንፋስ እንደምትጠፊ እወቂው! ከአንቺም ጋር እርስበርስ የሚጠላሉትና ፍቅር የሌላቸው አጋሮችሽ ሁሉ አብረው ይጠፋሉ!
❖[የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ ፲፯]❖
፩ ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ። ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤
፪ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ።
፫ በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።
፬ ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤
፭ በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም። ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።
፮ ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።
፯ መልአኩም አለኝ። የምትደነቅ ስለ ምንድር ነው? የሴቲቱን ምስጢርና የሚሸከማትን፥ ሰባት ራሶችና አስር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እኔ እነግርሃለሁ።
፰ ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።
፱ ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥
፲ ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል።
፲፩ የነበረውና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል።
፲፪ ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
፲፫ እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።
፲፬ እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።
፲፭ አለኝም። ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።
፲፮ ያየኃቸውም አስር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፥ ሥጋዋንም ይበላሉ ፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል።
፲፯ እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አግብቶአልና።
፲፰ ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።
❖[የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ ፲፰]❖
፩ ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።
፪ በብርቱም ድምፅ። ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤
፫ አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሳ ወድቀዋልና፥ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሳ ባለ ጠጋዎች ሆኑ ብሎ ጮኸ።
፬ ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል። ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤
፭ ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፥ እግዚአብሔርም ዓመፃዋን አሰበ።
፮ እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፥ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤
፯ ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ኀዘን ስጡአት። በልብዋ። ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ ባልቴትም አልሆንም ኀዘንም ከቶ አላይም ስላለች፥
፰ ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ኀዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፥ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።
፱ ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፤
፲ ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው። አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን፥ ወዮልሽ፥ ወዮልሽ፥ በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና እያሉ ይናገራሉ።
፲፩ የመርከባቸውንም ጭነት ከእንግዲህ ወዲህ የሚገዛ የለምና የምድር ነጋዴዎች ያለቅሱላታል ያዝኑላትማል፤
፲፪ ጭነትም ወርቅና ብር የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር ቀይም ሐርም ሐምራዊም ልብስ የሚሸትም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት ከናስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥
፲፫ ቀረፋም ቅመምም የሚቃጠልም ሽቱ ቅባትም ዕጣንም የወይን ጠጅም ዘይትም የተሰለቀ ዱቄትም ስንዴም ከብትም በግም ፈረስም ሰረገላም ባሪያዎችም የሰዎችም ነፍሳት ነው።
፲፬ ነፍስሽም የጎመጀችው ፍሬ ከአንቺ ዘንድ አልፎአል፥ የሚቀማጠልና የሚያጌጥም ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፥ ሰዎችም ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አያገኙአቸውም።
፲፭-፲፯ እነዚህን የነገዱ በእርስዋም ባለ ጠጋዎች የሆኑት እያለቀሱና እያዘኑ። በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ይቆማሉ። የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፥
፲፰ የመቃጠልዋንም ጢስ ባዩ ጊዜ። ታላቂቱን ከተማ የምትመስላት ምን ከተማ ነበረች? እያሉ ጮኹ።
፲፱ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ። በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከባለ ጠግነትዋ የተነሣ ባለ ጠጋዎች ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና እያሉ ጮኹ።
፳ ሰማይ ሆይ፥ ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ፥ በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፥ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።
፳፩ አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንስቶ ወደ ባሕር ወረወረው እንዲህ ሲል። ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።
፳፪ በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፥ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥
፳፫ የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፥ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፥ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።
፳፬ በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።
Blogger Comment
Facebook Comment