ራፋኤል ሌምኪን | 'ጀኖሳይድ'” የሚለው ቃል ፈጣሪ

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ራፋኤል ሌምኪን ከመቶ ስምንት ዓመታት በፊት ኦቶማን ቱርኮች በአንድ ሚሊየን ተኩል አርሜኒያውያን ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ የፈጸሙትን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተከትሎ ይህን የዘር ማጥፋትን በመጥቀስ፤ “የዘር ማጥፋት ወይንም 'ጀነሳይድ'” የሚለው ቃል ፈጣሪ ነው።

ራፋኤል ለምኪን እ.አ.አ በ 1949 ዓ.ም ነበር 'የአርመን የዘር ማጥፋት' የሚለውን ቃል የተጠቀመው።

የፖላንድ-አይሁዳዊው ጠበቃ ራፋኤል ሌምኪን (1900 - 1959) በየካቲት 1949 በ "ዩ.ኤን. ኬዝቡክ" በሲ.ቢ.ኤስ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር  ላይ ስለ የተባበሩት መንግስታት አሰራር ተናግሯል። ይህ የአሜሪካው ሲ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ልዩ መርሐግብር ስለ የዘር ማጥፋት (Genocide) እና “ዘር ማጥፋት” የሚለውን ቃል ከፈጠረው ሰው ራፋኤል ሌምኪን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ነው። ሌምኪን ስለ የዘር ማጥፋት እንዴት ፍላጎት እንዳደረበት ሲጠየቅ የአርሜንያውያንን መጥፋት ጠቅሷል።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment