ሙስሊሞች በእስራኤልና ፍልስጤም ጦርነት ፍልስጤምን ሲደግፉ አላህን እና ነቢያቸው መሐመድን ተቃውመው እንደቆሙ ያውቁ ይሆን?

✍ ሚካኤል ዘኢትዮጵ 

በመጽሑፍ ቅዱስ እንደተገለጠው ፍልስጤማዊያን ጣዖት አምላኪዎች ነበሩ። እስራኤላዊያንን በተለያዩ ጊዚያት የሚፈትኑ ጣዖታዊያን። ጥንት የነበሩት ፍልስጤማዊያን ሙስሊም አልነበሩም። እስልምና ከመሐመድ በፊት በየትኛውም ዓለም እምነት አልነበረምና። በርግጥ ጣዖታዊያን ሕዝቦች ነበሩ። በተለይ የመካ ሕዝቦች። እነሱ ዛሬም በእስልምና የሚታመነውን ያምኑ ነበር። የተወሰነ መሻሻል ተደርጎበት ነው እስልምና በመሐመድ የተፈጠረው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠቀሱ የእስራኤላዊያንና ፍልስጤማዊያን ፍልሚያ ለምሳሌነት ብንጠቅስ ፍልስጤማዊይውን ጎልያድና እስራኤላዊይውን ዳዊት ማንሳት እንችላለን። ይህም ኃይለ ቃል በ1ኛ ሳሙኤል 17:​1-54 ተጽፎ ይገኛል።

ፍልስጤማውያን እስራኤላውያንን ለመውጋት መጡ። በዚህ ወቅት የዳዊት ሦስት ታላላቅ ወንድሞች በሳኦል ሠራዊት ውስጥ ነበሩ። ስለዚህ ከዕለታት አንድ ቀን እሴይ ዳዊትን "ጥቂት እሸትና ዳቦ ለወንድሞችህ ይዘህላቸው ሂድ። ደኅንነታቸውንም አጣርተህ ንገረኝ" አለው። ዳዊት ሠራዊቱ ወደ ተከማቸበት ሰፈር ሲደርስ ወንድሞቹን ለመፈለግ ወደ ውጊያው ግንባር ሮጠ። ግዙፉ ፍልስጤማዊ ጎልያድ በእስራኤላውያን ላይ ለማሾፍ መጣ። ለ40 ቀናት በየዕለቱ ጠዋትና ማታ እንዲህ ሲያደርግ ቆይቷል። "ከእኔ ጋር የሚገጥም አንድ ሰው ከመካከላችሁ ምረጡ። እሱ ካሸነፈኝና ከገደለኝ እኛ ባሪያዎች እንሆንላችኋለን። እኔ ካሸነፍኩትና ከገደልሁት ግን እናንተ የእኛ ባሪያዎች ትሆናላችሁ። ከእኔ ጋር የሚገጥም ሰው ምረጡና አምጡ" እያለ ይጮኽ ነበር። ዳዊት "ይህን ፍልስጤማዊ ለገደለና እስራኤላውያንን ከዚህ ውርደት ላዳነ ምን ይደረግለታል?" ሲል ከወታደሮቹ መካከል አንዳንዶቹን ጠየቃቸው። ሳኦል ይህን ለሚያደርግ ሰው ብዙ ሀብት ይሰጠዋል፤ የራሱንም ልጅ ሚስት አድርጎ ይድርለታል" ብለው መለሱለት። ይሁን እንጂ ጎልያድ በጣም ትልቅ ስለነበረ እስራኤላውያን ሁሉ ይፈሩት ነበር። ቁመቱ ከ9 ጫማ በላይ (3 ሜትር ገደማ) ነበር፤ የእሱን ጋሻ ይዞ የሚጠብቀው ሌላ ወታደርም ነበረው። ዳዊት ጎልያድን ሊገጥመው እንደሚፈልግ ወታደሮቹ ለንጉሥ ሳኦል ነገሩት። ይሁን እንጂ ሳኦል ዳዊትን "ይህን ፍልስጤማዊ መግጠም አትችልም። አንተ ገና ልጅ ነህ፤ እሱ ዕድሜውን ሙሉ ወታደር ነው" አለው። "የአባቴን በጎች የወሰዱትን አንድ ድብና አንድ አንበሳ ገድያለሁ። ይህንንም ፍልስጤማዊ እንደነርሱ እገድለዋለሁ። እግዚአብሔር ይረዳኛል" ሲል ዳዊት መለሰለት። በዚህ ጊዜ ሳኦል "ሂድ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን" አለው። ዳዊት ወደ ወንዝ ሄደና አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች ለቀመና በኮሮጆው ውስጥ ጨመራቸው። ከዚያም ወንጭፉን ያዘና ግዙፉን ሰው ለመግጠም ሄደ። ጎልያድ ዳዊትን ሲያየው በጣም ተገረመ። ዳዊትን መግደል በጣም ቀላል ነገር እንደሆነ አድርጎ አስቦ ነበር። ጎልያድ ዳዊትን "ወደ እኔ ና፤ ሥጋህን የወፎችና የእንስሳት እራት አደርገዋለሁ" አለው። ይሁን እንጂ ዳዊት እንዲህ አለው:- "አንተ ሰይፍና ጦር ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ። ዛሬ እግዚአብሔር አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ እገድልህማለሁ።" ከዚያም ዳዊት ወደ ጎልያድ ሮጠ። ከኮሮጆው ውስጥ አንድ ድንጋይ አወጣና ወንጭፉ ላይ አድርጎ ባለ ኃይሉ ተጠቅሞ ወረወረው። ድንጋዩ ተወርውሮ ሄደና ጎልያድን ግንባሩን አለው፤ ጎልያድም ወደቀና ሞተ! ፍልስጤማውያን ይዋጋላቸው የነበረው ኃይለኛ ሰው እንደሞተ ሲያዩ ሁሉም ወደ ኋላ ሸሹ። እስራኤላውያን ፍልስጤማውያንን አሳደዱአቸውና በውጊያው አሸነፉ።

ፍልስጤማዊው ጎልያድ የእግዚአብሔር ሰው አይደለም፡፡ የሕዝበ እስራኤላውያንን ደም ለማፍሰስ የሚፈጥን እጅ የያዘ ግፈኛ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ የሕዝቡን ደም ከእጁ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የጎልያድ ዛቻ፣ የጦር መሣሪያ፣ ማስፈራራት፣ ኃይልና ጉልበት ሁሉ በእስራኤላውያን ዘንድ ቦታ የለውም፡፡ ምክንያቱም እስራኤላውያን የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸውና፡፡

ፍልስጥኤማውያን ወደቁ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ጭነው ዝም አሉ፡፡ እስራኤላውያንም የድል ዝማሬን ዘመሩ፡፡ ዳዊት በጠጠር ከጣለው ጎልያድ ላይ ሰይፉን መዘዘና ቸብቸቦውን ቆረጠው፡፡ ከእስራኤላውያን ዘንድም ስድብን አራቀ፡፡ ዳዊታዊ ጠጠር እንዲህ ያለ ኃይል አለው፡፡

አሁን ሙስሊሞች ጥንት ጣዖታዊያን የነበሩትን ፍልስጤማዊያንን ደግፈው ሲቆሙ እናያለን። ዛሬ ላይ ፍልስጤማዊያን አብዛኛዎቹ  ሙስሊሞች ስለሆኑ side ይዞ መቆም ግን ከእስልምና መጽሐፍትና ፈጠረን ከሚሉት አላህ ጋር ያጣላቸዋል። እየተቃወሙ ያሉት የሚያመልኩትን አምላክ አላህንና የሚከተሉትን ቁርዓንን ነውና።

እስራኤላውያን መሬታቸው ስለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ  ብቻ ሳይሆን ቁርዓናዊ ድጋፍም አላቸው። ሙስሊሞች እስራኤላውያን ሀገር የላቸውም ወራሪ ናቸው ብለው የሚናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ የታሪክ ትንታኔ ውስጥ ሳንገባ ከሚያውቁትና ከሚመሩበት ቁርዓን አላህ ያን ምድር ለእስራኤላውያን እንደሰጣቸው አያውቁም ይሆን?

ሱረቱል አልማኢዳህ (5:21)

يَا قَوْمِ ادْخُلُوا الْأَرْضَ الْمُقَدَّسَةَ الَّتِي كَتَبَ اللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَرْتَدُّوا عَلَىٰ أَدْبَارِكُمْ فَتَنقَلِبُوا خَاسِرِينَ

«ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ፡፡ ወደ ኋላችሁም አትመለሱ፡፡ ከሳሪዎች ኾናችሁ ትመለሳላችሁና፡፡»

ይህን ከላይ ያለውን ንግግር እየተናገረ ያለው ነብዩ ሙሳ ለእስራኤላውያን ነው። እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ በኃላ ያንን ምድር እንዲወርሱ ያደረጋቸው አላህ ነው። ያ ምድር አስቀድሞ ሰው ይኑረውም አይኑረውም አላህ ለእስራኤላውያን ሰጥቷቸዋል።  ስለዚህ አላህን ትከሱት ይሆን? ምን ብላችሁ? Democrat አይደለም ብላችሁ? እንደማትሉ እገምታለሁ።

የሚገርመው በዛ ወቅት ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ጊዜያትም ጭምር እስከ ዓለም ፍጻሜ በዚያ በሰጣቸው ምድር እንዲኖሩ፣  የተበተኑትም እስራኤላውያን ሳይቀር ከተበተኑበት በዚያ ምድር ሳይሰበሰቡ የዓለም ፍጻሜ እንደማይሆን አሁንም ቁርዓን ይናገራል።

ሱረቱል አልኢስራዕ (17:104)

وَقُلْنَا مِن بَعْدِهِ لِبَنِي إِسْرَائِيلَ اسْكُنُوا الْأَرْضَ فَإِذَا جَاءَ وَعْدُ الْآخِرَةِ جِئْنَا بِكُمْ لَفِيفًا

ከእርሱም በኋላ ለእሰራኤል ልጆች «ምድሪቱን ተቀመጡባት የኋለኛይቱም (ሰዓት) ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትኾኑ እናመጣችኋለን» አልናቸው። ይላል።

ስለዚህ የመሬቱ ባለቤት ያደረጋቸው (የሰጣቸው) አላህ ነው። እስራኤላውያንን ሀገር አልባ ወራሪ ብላችሁ ዛሬ ፍልስጤማውያን ማጆሪቲው በሃይማኖት ስለሚመስሏችሁ ጥብቅና የቆማችሁላቸው ቢመስላችሁም  በሌላ በኩል ደሞ ቁርዓንን ኮንናችኋል። አላህ የሰጣቸውን ምድር አይገባቸውም በማለት እየተቃወማችሁ ያላችሁት አላህን ነው።

ይህንን የቁርዓን አንቀጽ የምጠቅሰው እኔ አምኜበት ሳይሆን እናንተ እያመናችሁበት እንዴት መልሳችሁ ትቃወሙታላችሁ በሚል እንደሆነ ታሳቢ ይደረግልኝ። መሐመድ ከአላህ ተወረደልኝ ያለውን ቃል እንዳልተቀበላችሁም ለማመላከት ነው።

ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስም በቁርዓንም ብትሄዱ ያ ቦታ ለእስራኤላውያን በአምላክ የተሰጠ ነው። ይሄ እዚህ በየዜና አውታሩና ሶሻል ሚዲያ የሚራገበው its politics. ቁርዓንን በማያውቁ ሙስሊም extremists የሚራገብ anti Israel propaganda ነው።

04/02/16 ዓ/ም
ደብረዘይት፤ ኢትዮጵያ

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment