እኔስ ድል ለማን ልበል?



✍ ፕሮፌስር ሄኖክ አረጋ

የመካከለኛው ምሥራቅ አየር በባሩድ ሽታ የሰላም ጠረኑን ለውጦታል። የምስራቅ አፍሪካ ቅድስት ሀገር ሕዝቦችም ጎራ ከፍለው ያለምንም ሒሳብ ድል ለጽዮናውያን፤ ድል ለፍልስጤማውያን እያሉ ነው እኔስ ድል ለማን ልበል?

ብዙዎች ሠዓታቸውን 1948 ዓ.ም የእስራኤል ምሥረታ ላይ አድርገው እስራኤል የገጠማትን ፍልስጤምን ወራለች ሲሉ ይወግናሉ። እስኪ ሠዓታችንን ወደኋላ እንጠምዝዝና 1516 ዓ.ም ላይ እንውሰደው። የዛሬ 507 ዓመት ገደማ ወቅቱ ደግሞ አሁን ፍልስጤም እና እስራኤል በጋራ የሚጠቀሙበት ቦታ ላይ ኦቱማን ቱርኮች ወረራ ፈፅመው ለ400 አመታት (1516-1918) የቆዩበት ዘመን ቦታው ላይ ክርስቲያኖች፣ አይሁዶች እና ሙስሊሞች ያለምንም ግጭት ይኖሩበት የነበረ ስፍራ ነበር።

ኦቱማን ቱርኮቹ ሙስሊም ይሁኑ እንጂ ዝርያቸው ከአረብ የሚመዘዝ አልነበረም። በአገዛዝ ዘመናቸውም አራት ቦታ ማዕከላዊ መንግሥታቸውን  በመክፈል እየሩሳሌም ፣ ጋዛ ፣ ናብለስና ሳፌድን ያስተዳድሩ ነበር። በዚህ ሥርዓት ውስጥ ሙስሊም ያልሆኑት (ክርስትያን እና አይሁዶቹ(ማንነት ነው)) ከፍተኛ ግብር እና ታክስ እንዲከፍሉ፣ ከፍተኛ የሥራ ጫና ፣ የሰዶ ማሳደድ ዘመቻዎች ፣ እስሮች ፣ ግድያዎች  ይፈፀምባቸው ነበር። በቦታው እኚህ አይሁዶች በቁጥር ከክርስትያኖቹም ያንሱ ነበር። በ1901 እንደውም አይሁዶቹ መሬት መግዛት ስላልቻሉ በሚጣልባቸው የግዢ ዋጋ ብሔራዊ ተቋም መሥርተው ገንዘብ ከተለያየ ቦታ እየለመኑ fund በማስደረግ ለመግዛት እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመሩ።

በዚህ ወቅት ጥቂት የማይባሉ አይሁዶች ተበታትነው በተለያየ የዓለም ክፍል ይኖሩ የነበር ሲሆን ባሉበት አካባቢ ራሱ ጭፍጨፋ ይፈፀምባቸው ነበር። ምክኒያቱ ደግሞ ዘመኑ ትንሽ ሕዝቦችን እንደባሪያ ሊያሠራ መፈለጉ እና ሰዎች በዘር ሐረጋቸው ተቧድነው የሚኖሩበት ዘመን መሆኑ ነበር። አይሁዶች በጀርመን ብቻ ግፍ አልተፈፀመባቸውም። የ1881 የኪዬቭ የሶቪየት ኅብረት የአሁኗ ራሺያ ጭፍጨፋ የሚረሳ አይደለም።

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ይህንን አካባቢ ሙሉ በሙሉ ፖለቲካውን ሲቀይረው ታላቋ ብሪታንያ ይህንን ስፍራ ከፈረንሳይ ጋር በመሆን ተቆጣጠረች። ኦቱማን ቱርኮቹ መንግሥታቸውም ወደቀ። በነዚህ ማዕበሎች ሁሉ መሃል ግን ቴዎዶር ሄርዝ የተባለ ግለሰብ ለጽዮናውያኑ ማረፊያ የሚሆን ቋንቋ ሲያበጅ ፣ መሬት ሲፈልግ (ኡጋንዳን ሁላ ሳይቀር ሊሰፍሩ አስበው ነበር) ፣ ጽዮናዊ መጽሐፍቶችን ሲያሳትም ንቅናቄዎችን ሲያቋቁም ነበር። ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተጀመረ።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በተጀመረ በዓመቱ በእጅጉ ትከሻው እየሰፋ የመጣው የጀርመኑ ናዚ ቡድን አውሮፓን ያዳረሰ በመሰላቸው ወቅት ኅዳር ወር ላይ 1941 ሀጂ አሚን አልሁሴን ወደ በርሊን በመጓዝ  ሂትለርን እና ሌሎች ከፍተኛ የናዚ አመራሮችን ካገኙ በኋላ አይሁዳውያንን ከፍልስጤም እንዲጠፉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ እና ለዚህም ከናዚ ወታደሮች ጋር የቦስኒያ ሙስሊሞች እንዲዋሐዱ ተነጋገሩ። ሁለተኛውም የዓለም ጦርነት ከተጠበቀው በተቃራኒ ነበር። ውጤቱ የሆነባቸው ናዚ የተባለው ጨካኝ ለአይሁዶች በሚሊዮን ሞትን ያስታቀፈው ሥርዓት እነሱን ሳያጠፋ ቀደማቸው።

1945 መስከረም ላይ ያበቃው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዓለም ለባሩድ ሽታዎች አፍንጫዋ የተዳፈነ ቢመስልም ጽዮናውያኖቹ ግን መሬታቸውን በባለቤትነት ለመያዝ እንግሊዝ ላይ ጫና ማሳደራቸውን ቀጠሉ። ይባስ ብለው በወቅቱ ዝነኛ የነበረውን የ king david ሆቴልን በቦምብ አጋዩት። ከዚህ ሁሉ ተብሎ አካባቢውን ለቀው የወጡት እንግሊዞች በUN በተባበሩት መንግሥታት አማካኝነት ቦታውን ለአይሁድ እና ለአረቦቹ አካፈሏቸው።

በዚህ ደስተኛ ያልነበሩት አረቦቹ ከተለያየ ሀገር በመሰባሰብ ያልተመሠረተችውን ሀገር ጽዮናውያንን ለማጥፋት ተረባረቡ። አዲሶቹ ነፃነት አዋጂዎቹ ግን አይደለም ለመግፋት ለመደገፍ እንኳ የሚቀመስ አልሆኑም። በሚያዚያ 9 1948 ዴር ያሲን በተባለ ዘመቻ እስራኤል 120 የሚጠጉ ንፁሃንን ስትገል ለሱ አፀፋ ነው የተባለው 129 አይሁዶችን በግንቦት 13 እየሩሳሌም እና ሄብሮን መካከል የተፈፀመው ግድያ ማግስት በጭፍጨፋዎች ተበታትነው የት እንኑር ብለው መሬት ሲመርጡ የነበሩ ጽዮናውያን ግንቦት 14 1948 ነፃ ሉዓላዊ ሀገር ሆነው በአሁኑ የእስራኤል ቦታ ላይ ሀገር መሠረቱ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ያለፈውን መቀበል ያልቻሉ ጎሮቤቶቻቸው ከተለያዩ በእምነት ከሚመስሏቸው ሀገራት ጋር በመሆን ብዙ ወረራ እና ጦርነት ቢከፍቱባቸውም በምሬት የተመሠረተችው ሀገር ግን ልትሸረፍ አልቻለችም።

🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱

ምዕራፍ ሁለት ወቅታዊ

የእስራኤልና የፍልስጤም ጦርነት ታሪካዊ ነገርን ከተመለከትን እስራኤል እንደ ሀገር ከተመሠረተች 1948 በኋላ ባሁኑ ካርታ ጋዛ በግብፅ ስር ይተዳደር የነበረ ግዛት ሙሉ ለሙሉ ፍልስጤማውያን ሲኖሩበት ቦታውም የፍልስጤም ነፃ አውጪ ነኝ ርስቴን አስመልሳለሁ የሚለው የሀማስ ሽፍቶች መፈልፈያ ግዛት ነው። በምስራቅ በኩል ደግሞ በጋራ የሚጠቀሙበት ኢየሩሳሌም ከተማ የነበረ ቢኖርም በዶናልድ ትራምፕ ጊዜ ፍልስጤሞች በተደጋጋሚ ባደረጉት ጥቃት ከተማዋን ለእስራኤል ዋና ከተማ ብቻ እንደሆነች እውቅና ተሰጥቶ ነበር።

አሁን ላይ የተቀሰቀሰው ጦርነት ከበፊቶቹ የተለየ ውጤት የማያመጣ እና መጨረሻው በእስራኤል አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ቢሆንም ይህንን ለማለትም፦

1- ጦርነቱ ፍልስጤሞች ሲጀምሩት ከራስ በመጣ በመተማመን፣ በዕቅድ እና በዓላማ ሳይሆን ኢራንን በመተማመን መሆኑ የጓደኛህን እጅ ተማምነህ ለድብድብ ቡጢ እንደማይሰነዘር ሁሉ የሌላ ሀገርን ተማምኖ ጦርነት መጀመር አዋጭ አይደለም።

2- ከከዚ በፊቱ የተለየ ጥቃት አለመፈፀሙ ሃማስ 200 ሮኬት ወረወረ የሚለውን ዜና 200 ቁጥሩ መብዛቱ እንደ ትልቅ ድል ከአንድ ወገን (ፍልስጤም) ዜናውን ቢቀባበሉትም ወደኋላ ሠዓታችንን አስተካክለን ግንቦት 11 እና 12 ማለትም ማክሰኞ እና ረቡእ ምሽት 2021 የዛሬ ሁለት ዓመት ብንመለስ ማክሰኞ ምሽት 1050 ሮኬቶችን ረቡዕ ምሽት ደግሞ 550 ሮኬቶችን አጠቃላይ በሁለት ቀናት ውስጥ 1600 ሮኬቶችን ወርውረው ምንም አለመፍጠራቸውን ስታይ ደስታቸው የግል አነቃቂ ነገሮችን ከመፈለግ ነው ያስብላል።

3- የፍልስጤሞች ድንገተኛ ነው የተባለው ማጥቃት ከእስራኤሉ የነብር ጆሮ እና የንሥር ዓይን ከሆነው የደኅንነት ድርጅቱ ሞሳድ (MOSAD) ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሳይኖር እንዲህ ዓይነቱ ጥቃት በእስራኤል መፈፀሙ አይደለም እስራኤላውያን ዓለም በዝናው እና በብቀላው የሚያውቀውን ይህን ድርጅት ከጥቃቱ መፈፀም በላይ ሊያሳካው የፈለገው ለጊዜው ያልታወቀ ነገር ግን ትልቅ ዓላማ ምንአልባትም እስራኤል ሙሉ በሙሉ መሬቱን 100% የጽዮኖቹ የማድረግ ያልተጠናቀቀ የቤት ሥራዋን መሥራት አስባ ሊሆን ይችላል ያስብላል።

ትላንትና ምሽት ይህንን ጥያቄ ከCNN ጋዜጠኛ የተጠየቀው የደኅንነት ቃል አቀባይ ግለሰብ (ስሙ ስለተዘነጋኝ ነው)

ጋዜጠኛዋ : ዓለም የሚኮራበት ሞሳድ የት ነበር?
ቃለ አቀባዩ : "እሱ አሁን የሚገለፅ አይደለም አሁን ትኩረታችን ድል ማድረጉ እና አካባቢዎችን መያዙ ላይ ነው" ማለቱ።

4- የእስራኤሉ አየር ኃይል IAF (Israel Air Force) በራስ መተማመን በፌስቡክ ገፃቸው ሳይቀር በlive የፍልስጤም ወታደሮች ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ የአየር ምስላቸውን እየለቀቁ መሆኑ በራስ መተማመናቸው።

5- እስራኤል አረቦችን መጠበቂያ  መካከለኛው ምስራቅ እንደልብ ማሽከርከሪያ ስፍራ መሆኗን ተከትሎ በፖለቲካ ኃይል ከፍተኛ ዋጋ ይሰጣታል። ይህች ሀገር እንደ ዩክሬን የቅንጦት ምርጫ ሳትሆን የህልውና ሀገር መሆኗን ተከትሎ ምዕራባውያን አውሮፓን ጨምሮ ሚከፈለውን ከፍለው ፍልስጤምን ረግጠው ጨምቀው አስጥተውም ቢሆን እስራኤልን ወደቀደመ ገናናነቷ ይመልሷታል።

ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ሁሉ ሲገጣጠሙ እስራኤል ይህንን ጦርነት ቢበዛ በሳምንት ውስጥ ወደቦታው ትመልሰዋለች የሚል ውጤት ሲሰጠኝ ፍልስጤምን በልቶ አላየሁም የሚለው ሞሳድ ግን በቀጣይ ከኢራን ጋር ተከትሎ የሚፋጠጡት ፍጥጫ ይበልጥ የምጠብቀው ነው። መጪው 2024 ደግሞ ትራምፕን ወደፊት ሲያመጣ ለእስራኤል ትልቅ ትከሻ ሲሆን የጓደኛቸውን ቡጢ ተማምነው በጥፊ ተማተው የጠፉ ሁለት አገራት ውስጥ ፍልስጤም ከዩክሬን አጠገብ ስሟን ማፃፏ እጅግ የሚሳዝነኝ ነገር ነው ይሄን ጦርነት ልምምድ በሉት።

ማጠቃለያ የነዚህ ሁለት ሀገራት የርስበርስ ግጭት ሀገራቱ ርስበርስ ለዓለም ከሚያበረክቱት ትልልቅ ምርቶች እና ተፅእኖዎች አለመኖራቸውን በእኛ ላይ ቀጥተኛ የሆነ ተፅእኖ የማያመጣ እና ሃይማኖታዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ጦርነታቸው ከእኛ ጋር የሚያገናኘው ነገር አለመኖሩን ተከትሎ ድል ለራሳችን ብለን ብንመለከት ይሻላል።


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment