ጥቅምት 5 | አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ መታሰቢያቸው ነው።



በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ562 ዓመታቸው በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።

ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጎልጎታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ::

"ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ:
ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ:
ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ:
ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ:
ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ::" 
እንዲል::


የጻድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ መጋቢት 5 ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ (ቅያሪ) ሆኖ ነው።

በዚህች ቀን ታላቁ አባት ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዝቋላ ተራራ በሐይቁ ውስጥ ለመቶ ዓመት ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ምሕረት ለምነው ከእግዚአብሔር ዘንድ ቃል ኪዳን የተቀበሉበት በዓል ነው የሚልም ይገኛል።

               ◦🍀◦🍀◦🍀◦
           
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment